Bete Amhara

Bete Amhara

Monday, November 30, 2015

አማራ ነኝ እንጅ!!!!!
ከማረሻው ግርጌ፣ ከቀንበሩ ገመድ፣
ከበሮቼ ጋራ፣
ከጥቁር አፈር ጋር፣
አብሬ እምወጣ፣ አብሬ የምወርድ፣
አንበሳን ታግዬ፣
እንደ ፈረስ ወገብ፣ ቼ ብዬ የማለምድ፣
ሰማዩን አምኜ፣
ስለት የማስገባ፣ ለታቦቴ እምሰግድ፣
አማን አርገኝ ብዬ፣ ለጀማው እማረግድ፣
ምጣድ ያመሰውን፣
የጋመ ባቄላ፣
እንክክ እንክክ ብዬ፣ እጄ ላይ የማበርድ፣
አማራ ነኝ እንጅ፣
መንገድ ሰፋኝ ብዬ ፣
መንገድ ከገባ ጋር፣ ተነስቼ እማልነጉድ።
አማራ ነኝ እንጅ፣
መሬቱን አምኜ፣
አማን ኢማን ብዬ፣
ባንተው ይሁን ብዬ፣
ባንተው መጀን ብዬ፣አይኔን የማቀና፣
የጎረቤት ማጀት፣
ለምን ሞላ ብዬ፣ በሰው የማልቀና፣
ከወንድሞቼ ጋር፣
ከዘመዶቼ ጋር፣
በሌማት የምጎርስ፣ ንጣይዋን እንጀራ።
አማራ ነኝ እንጅ፣
አባይ ባጠገቤ፣ አቅፎ የሚስመኝ፣
ጣና በትንፋሹ፣ ባይኑ የሚጠቅሰኝ፣
ጎተራ እንደሁ እንጅ፣
ለወንድሞቼ ራብ፣ ማዴ የማያንሰኝ።
ልጄን በወገቤ በአንቀልባዬ አዝዬ፣
በአገልግል በሰንሰል፣
የሻገተ እንጀራ፣ ጣቢታ አንጠልጥዬ፣
ጎጆዬን ያቀናሁ፣
ቀን ከቀበሮ ጋር፣
ማታ ከጅብ መንጋ፣ ከድብ ጋር ታግዬ።
መታመን የሚሉት፣
መዋደድ የሚሉት፣
የጥቁር አፈር ቃል፣ ልቤ ላይ ተሰርቶ፣
በወንድሞቼ ላይ፣
የተጣደው በደል፣
የሚያብረከርከኝ፣
የሚያብሰከስከኝ፣ ጉልበቴ ስር ገብቶ።
አንበሳ ከጅብ ጋር፣
እኔ እበላ እበላ፣ በሆድ ሲታገሉ፣
አሞራና ውሻ፣
እኔ እግጥ እኔ እግጥ፣
እየበጣጠሱ፣ እየዘለዘሉ፣
በአጥንት ተናጭተው፣ በስጋ ሲጣሉ፣
አንተም ስጥ፣
አንተም ስጥ ፣
ብየ የማስታርቅ ፍቅር የሚርበኝ፣
እኔ ነኝ አማራ፣
እንኳንስ ወንድሜ፣
አራዊት ጫካውን፣
ድካውን ሲነጥቁት፣ የሚያንገበግበኝ።
አኔማ አማራ ነኝ፣
ሰማይ ከዳ ብዬ፣
ምድር ጦፈች ብዬ፣
የከሳው በሬዬን፣ አርጀ እማልበላ፣
ነገ አለልኝ ብዬ፣
የዘር ጃምዮየን፣
ላንዲት ርሃብ ብዬ፣ በእሳት የማልቆላ፣
በቂጣ የማልሽር፣
የአባቶቼን ግዝት፣የአባቶቼን ማላ።
አዎን አማራ ነኝ፣
ስሜ የጠገበ፣
ማርና ነጭ ጤፍ፣ ጮማና ብርንዶ፣
ባልበላም በልተሃል፣
ባልተኩስ ገድልሃል፣
ተብዬ እምጠራ፣
ተብዬ እምፈለግ፣ ፍርደኛ አጋሚዶ፣
አቤት ባይ ባተሌ፣
በሸንጎ በቀዬው፣ ስሜ ፍርድ ለምዶ።
አማራ ነኝ እኔ፣
ደብረ ግሸን ከርቤ፣
ረጅም መቋሚያ፣
እጀን ተደግፌ ታቅፌ እምወጣ፣
እንኳን የገዛ እጄን፣
አሳልመኝ ያለኝን፣
አይዞህ እያልኩኝ፣ ደግፌ እማመጣ።
አማራ ነኝ ጓዴ፣
ከጥማድ እርሻዬ፣
አምላክ የሰጠኝን፣
ጥንቅሽና ውልቢኝ፣
አሻግሬ እያየሁ፣ ማማ ተቀምጬ
አላፊ አግዳሚውን፣
ቅመሱልኝ የምል፣ ከእርሻዬ ቆርጬ።
አማራ ነኝ አዎ፣
በደረቅ ባቄላ፣በእንኩሮ መቀጣ፣
ጣዬ ሲበዛብኝ፣
ገብስ ቆሎዬ ላይ፣
ጉሮሮየን ላረጥብ፣ጠላ የምጠጣ፣
ባልበላሁት ዝልዝል፣
ባልጠጣሁት ማር ጠጅ፣ ሰክሬ እምወጣ።
በኩርማን እንጀራ፣
በድሪቶ ጋቢ፣
በእራፊ መቀነት፣ አንጀቴ ተሳስራ፣
በልቶብናል አሉኝ፣
የወንዙን እንጎቻ፣ ያገሩን እንጀራ።
ምነው ሆዴን ባዩት፣
ምነው ጎተራዬን፣ባዩት ወንድሞቼ፣
ይገባቸው ነበር፣
እነሱን ያቀናሁ፣
እነሱን ያጠገብኩ፣እኔ ተራቁቼ።
ከቶ ምን በድዬ፣ምን አድርጌያቸው ነው፣
ኧረ መጥተው ይዩኝ፣
እህል የጓሸበት፣
ወንድም የተራበ፣ ሆዴ እኮ ባዶ ነው።
ውሃ ጠማኝ ብዬ፣
ሃሩር በላኝ ብዬ፣ ከመንገዴ አልወጣ፣
እኔ አይደለሁም ወይ፣
እፍኝ ውሃ ጠምቶኝ፣
ለእኒያ ወንድሞቼ፣ ባህር የማጠጣ።
በጭብጨባ ብዛት፣
በምርቃት ግሳት፣
ሞቅ ሞቅ አይለኝ፣ወደላይ አልወጣ፣
በእርግማን ውርጅብኝ፣
በስድብ ነበልባል፣
ተሰደብኩኝ ብዬ፣ ወደ ታች አልመጣ።
ከላይ ነኝ አላልኩህ፣
ከታች ነኝ አላልኩሽ፣ አለሁ በእኩሌታ፣
ማነው የሚሰፍረኝ፣
ማነው የሚያጉድለኝ፣
ከባንዲራው ቀለም፣ ከባቶቼ ቦታ።
አዎን አማራ ነኝ፣
ጦቢያ የምትባል፣
የነፃነት ሰንደቅ፣
ያኔ ስትበጃጅ፣ ያኔ ስትሰራ፣
አንድ ላይ ሲማገር፣ የቤቷ ወጋግራ፣
እኔ አይደለሁም ወይ፣
ውሃ ልኳን ያቆምኩ፣ ወንድሞቼ ጋራ፣
እንዴት እጎድላለሁ፣
ካስቀመጡኝ መንበር፣ ካስቀመጡኝ ስፍራ።
አዎን አማራ ነኝ፣
የፈረሰ ማገር፣
የፈዘዘ ወራጅ፣
የዛለ ምሰሶ፣
እንደገና እንስራ፣
እንትከል እያልኩኝ፣
የደለቅኩት ድቤ፣
ከተሰማ ባገር፣
ከሞቀ በዃላ፣
በጅጌ በደቦ፣ በቀየው ታውጆ፣
አዳ ምን ዋጋ አለው፣
ሁሉም ሳር ይመዛል፣
ያድርበት ይመስል፣
በገፈፈ ክዳን፣ በዘመመ ጎጆ።
እረ እኔ አማራ ነኝ፣
የቦዘኔ ቃሪያ፣
የጤፍ ዱቄት ቂጣ፣
የሳማ ነጭ ወጥ፣"
የማሽላ ቆሎ፣
እንጀራ ነው ብዬ፣
እየገረገረኝ ቆርሸ፣ እምበላ፣
ጮማ ነው እያሉኝ፣
ቅቤ ነው እያሉኝ፣
ማጀቴን ያላዩ፣ ሰምቶ አዳሪ ሁላ።
አዎን አማራ ነኝ፣
አሳድረኝ ብሎ፣
ቁራሽ ስጠኝ ብሎ፣ከመጣ ከኔ ቤት
አልጋዬን የምለቅ፣
ቁልፍልፍ ብዬ፣
መደብ እምተኛ፣ በታበሰ ማጀት፣
ጦሜን የምተኛ፣
በባዶ ማድጋ፣ በተቋጠረ አንጀት።
ታዲያ እኔ ነኝ ባዳ??
እኔ ነኝ ባይተዋር???
በወንድሞቼ ደጅ፣
ሚዛን ያጎደለኝ፣ ለአይናቸው ቀልዬ፣
በአባቶቼ ማጀት፣
ሰርክ የምገፈተር፣
ና ውረድ ና ግባ፣ ና ውጣ ተብዬ።
የአባቶቹን ሃገር፣
የአርበኞቸን ርስት፣
ያንተ ቤት አይደለም፣
እያሉ ዘበቱ፣
በሽሙጥ አይናቸው፣ አባረሩኝ በቃ፣
ባዶ እጄን ሰደዱኝ፣
ያለ ስንጥር አፈር፣ ያላንዲት ጦሪቃ፣
ገፈተሩኝ ጓዴ፣
ሰው አላየም ብለው፣
በጠቆረው ሰማይ፣ ሌት በጠፍ ጨረቃ።
ይስሙ ንገሯቸው፣
ከነ ሻሾ በረት፣
ከነ ላሎ ማጀት፣
ሺ ጊዜ ቢታለብ፣ ማለቢያው ቢሞላ፣
ለስሙ ነው እንጅ፣
ፈርዶብኝ ነው እንጅ፣
በአዋዜ አይደለም ወይ፣
በእሬት አይደለም ወይ፣
ከወንድሞቼ ጋር፣ ፈትፍቼ እምበላ፣
አዎን፣
ከባዶ ሌማት ላይ፣
ከዱባ መረቅ ላይ፣
ዘመን የሚሻገር፣
እንቅብ የሚሞላ፣
ጣቢታ እየጋገርኩ፣ ተአምር የምሰራ፣
እኔ ነኝ ባንዲራው፣
እኔ ነኝ ሰንደቁ ፣
እኔ ነኝ፣ እኔ ነኝ፣ እኔ ነኝ አማራ።
ገጣሚ:- መንግስቱ ዘገዬ (ጃኖ መንግስቱ)
ከ ደሴ

https://www.facebook.com/permalink.php?story_fbid=923622881018470&id=808909555823137

ቤተ አማራ ሁለት ሶስተኛ አይኖችን ስለመክፈቱ:- ተከዜ ማዶ ባፍንጫችን ይውጣ

ቤተ አማራ ሁለት ሶስተኛ አይኖችን ስለመክፈቱ:- ተከዜ ማዶ ባፍንጫችን ይውጣ
******************************************************************
የተከዜ ማዶና ማዶ ሰዎች ለሽህ ዘመናት በወደረኝነት ገመድ ታስረው እርስ በእርስ ሲጓተቱ ኖሩ፡፡ ከመጀመሪያው መቆራኘታቸው አስፈላጊ አልነበረም፡፡ ለምን መቆራኘት እንዳስፈለገ ራሱ ግራ ነው፡፡ ቁርኝቱ አስፈላጊ ካለመሆኑ የተነሳ ለመቀራረብ ሳይሆን የተቆራኙበትን ገመድ ለመበጠስ ነበር ሳብ ጉተት ሲሉ የኖሩት፡፡ በእርግጥ ጉዳዩ የክርስትናና የንግስና ጉዳይ ነው፡፡ ከእስራኤል መጣ የተባለው ቅዱስ እቃ ለሀይማኖታዊ ጉዳይና ለንግስና ህጋዊ ተረገጥነት ማግኛ ሆኖ አገልግሏል፡፡ የዚህም ቦታ ተከዜ ወዲያ ማዶ ሆነ፡፡ ወዲህ ማዶ ያሉትም ያችን ሀይማታኖዊና ንግስናዊ ቦታ ላለማጣት፤ ከዛ ማዶ ያሉትም ያለ እነሱ ህይወት የምታቆም እየመሰላቸው ሲመጻደቁ ይሄው ለዘለአለም በወደረኝነት ገመድ ሲጓተቱ ኖሩ፡፡ የሚጓተቱት ገመዱን ለመበጠስ አልነበረም፡፡ ከገመዱ ጫፍ ያለውን ሰው ለመጣል እንጅ፡፡ በተለይ የተከዜ ሰሜን ማዶው ወገን ሁልጊዜ የደቡቡን ለመጣል ነበር ገመዱን ሲጎትት የኖረው፡፡ ገመዱ በጊዜ ተበጥሶ ቢሆን ኖሮ ያ ሁሉ ወደረኝነት እስከዛሬ ድረስ ባልቀጠለ ነበር፡፡ በብዛት በዚያ ወደረኛ ገመድ እየታነቀ ሲወድቅ የኖረው የታችኛው ማዶ ሰው ነው፡፡ ሁሉ በጁ ሁሉ በደጁ ሆኖለት ሳለ የንግስናና የዘውድ ህጋዊነትን ለመቀዳጀት ተከዜን ተሻግሮ ይሄዳል፡፡ በዛም ጦስ ተተብትቦ ታንቆ ሲወድቅ ታሪክ እልፍ ጊዜ መሰከረ፡፡ ያ እንግዲህ በአሁኑ ዘመን ስሌት ሞኝነት መሆኑ ነው፡፡ ያው ሞኙ የተከዜ ደቡብ ማዶ ሰው ነው፡፡ እምነት አስቸጋሪ ነውና ልብ በእምነትህ ማእከል ይኖራል፡፡ የተከዜ ደቡብ ሰዎችም በገሀዱ አለም የትም መሄድ ሳያስፈልጋቸው እዛው በበአታቸው መኖር ይችሉ ነበር፡፡ ግን እምነት ወደማዶ ይወስዳቸዋል፡፡ በእምነት ወንዝ ይሻገራሉ፤ በሸፍጥ ይታነቃሉ፡፡ እምነት መሞኘትን ወለደችላቸው፡፡ ሞኝነትም መታነቀን አተረፈችላቸው፡፡ የእጃቸውን እውነት ዘንግተው የሩቅ ነገርን በማመናቸው በየዘመኑ በራሳቸው የዋህነት እየተጠለፉ ሲወድቁ ኖሩ፡፡ በዚህም ተደጋጋሚ የመጠለፍ ድርጊት ያሰቡት ሳይደርሱ ህልማቸው ሳይሳካ መና ሆነው ቀሩ፡፡
አንድ ጊዜ አንዱ አንዱን ትግሬ “ትግራይን አስገድዶ መገንጠል ነበር” ይለዋል፡፡ ትግሬውም ራሱን ሲያዋድድ “ትግሬ ከተገነጠለ እኮ ኢትዮጰያ የምትባል ታሪክ የላትም፤ ምንም ናት” ይለዋል፡፡ ያኛውም “ታሪክ የምትሉትን ይዛችሁ ሂዱ፤ ከጥቅማችሁ ጉዳታችሁ ነው የባሰብን” ይለዋል፡፡ ትግሬውም “የተቋጠረ ስልቻ ሙሉ ጤፍ ከወደጫፉ ስልቻውን ብትቆርጠው ጤፉ ይፈሳል፤ ለትግራይ ከተገነጠለችም እንደዛ ነው” ይላል፡፡ ያኛውም “አይ ችግር የለውም፤ የተወሰነውን ጤፍ አፍስሰን ዝቅ አድርገን እንቋጥረዋለን” አለው፡፡ አሁን እንግዲህ የተወሰነውን ጤፍ አፍስሶ ስልቻውን ዝቅ አድርጎ ማሰር የተባለው ዘዴ ላይ ደርሰናል፡፡
ዋናው ነገር የተከዜ ደቡብ ሰው ዝንተ አለሙን ትግራይ ለምትባል አገር መስዋእት ሲሆን ነው የኖረው፡፡ በያንዳንዱዋ የትግራይ ቋጥኝና፤ ጎጥ፤ ተራራና ሸጥ ስር የአማራ አጥንት ይገኛል፡፡ ታሪክ ምስክር ነው፡፡ አማራ ለትግራይ ያልሆነው እና በትግራይ ያልደረሰበት ችግር የለም፡፡ በታሪክ ካመጡልን ያመጡብን ይበልጣል፡፡ አብዛኞቹ ያሳላፍናቸው የመከራ ጊዜያት እና አሁን የምንኖርበት የጨለማ ዘመን በትግራይ የተበረከቱልን ስጦታዎች ናቸው፡፡ ከወደ ትግራይ በኩል ለአማራ የመጣለት ጦርነት፤ ሽፍጥና ክህደት፤ በተለይ አሁን ደግሞ የዘር መጥፋትና ሁሉም አይነት የሰው ልጅ ሊሸከመው የማይችለው ስቃይ ብሎም አማራ ራሱ በፈጠራት አገር ዜግነትን ተቀምቶ እስከመዋለል ነው፡፡ ከወደ ትግራይ ጨው አልመጣለት፤ ጤፍና ባቄላ አልተጫነለት፤ ሙዝና ብርቱካን አልተላከለት፤ ማርና ወተት አልፈሰሰለት፡፡ ምንም፡፡
በዚህም ሁኔታ ውስጥ ታዲያ አማራ ጨቆነን ይላሉ፡፡ በእርግጥ ይህን ሲሉ አማራም እግዜሩም ይታዘባቸዋል፡፡ አማራ ጨቆነን የሚለው የአማርኛ ክስ ወድትግርኛ ሲመለስ “አማራ ከእግዚአብሔር ጋር በመመሳጠር ትግራይ ላይ ዝናብ እንዳይዘንብ አድርጓል” የሚል ይዘት ያለው ነው፡፡ በአለም ላይ ዝናብ እንዳይዘንብ አድርገሀል ተብሎ የተከሰሰ ብቸኛው ህዝብ አማራ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ለእግዜሩ ሊሰጥ የሚገባን ክስ አላግባብ የተቀበለ አሳዛኝ ህዝብ፡፡ እንጅማ ለምኑ ብለው አማሮች ትግራይን ጨቆኑት ይባላል፡፡ ከጥንት እስከ ዛሬ በመላ አገሪቱ በጣም አነስተኛው የአማራ ቁጥር የሚገኘው ትግራይ ውስጥ ነው፡፡ አሁን በግድ የያዙትን የወሎና የጎንደር አማራ ሳይጨምር፡፡ ይሁንና አባቶቻችን ያንን ምንም የሌለው ምድር የራሳቸው መንግስት አካል አድርገው አቆይተውታል፡፡ ለአማራ ከከፈሉት መስዋእትነትም ለትግራይ የከፈሉት ይበልጣል፡፡ በተለይ ትግሬና ትግራይን ከጣልያን መንጋጋ ለማስጣል የከፈሉት መስዋእት በመላ ኢትዮጵያ እንኳ ተደርጎ የማይታወቅ ነው፡፡ ለምንድነው ይህን ሁሉ መስዋእት ያደረጉት ስንል መልሱ ሁለት ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ አንዱ አንደተጠቀሰው የታሪክና የእምነት አካላችን ነው፤ የንግስና ማእከላችን ነው ብለው ስለሚያምኑ ነው፡፡ ሌላው ያለ ጥርጥር ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚገለጽ ለህዝቡ ፍቅር ስላላቸው ነው፡፡ አስቤ አስቤ እንዲሁም አንብቤ አባቶቻችን በትግራይ ላይ የጨከኑበትን ጊዜ ላገኝ አልቻልኩም፡፡ በተጻራሪው ከዛ አገር የሚመጣልን ግን የተጠቀሰው ህጸጽ እና ያልተጠቀሰው ብዙ ሳንካ ነው፡፡ ምን ምን እንደደረሰብን ወደታሪኩ አልገባም፡፡ ምናልባት ሌላ ጊዜ እመለሰብት ይሆናል፡፡
ከዚህ ተነስተን ቁርኝቱ መጀመሪያውንም ፍትሀዊ አልነበረም እንላለን፡፡ ከዛ ምድር የሚመጣብንን ሳንካ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት የሁለቱንም ሶስተኛ አይኖች መግለጥ የግድ የሆነበት ጊዜ ላይ ደረስን፡፡ የአማራ ሶስተኛ አይን ለዘላለም ተሸብቦ የኖረ እና ብቻውን ለመኖር የተሻለ እድል፤ ብቃት፤ ምክንያትና ሀብት ያለው መሆኑን አለመገንዘቡ ነው፡፡ አሁን አማራው የመጣባቸውን ታሪካዊ ሂደቶች ገልብጦ ማየት ጀምሯል፡፡ ያለፈባቸውን መንገዶች ጥቅምና ጉዳት፡ የአሁኑን ሁኔታና መጭውን ተስፋና እንቅፋት አንድ ላይ ገምግሞ የመንገድ ለውጥ ማድረግ እንዳለበት አምኗል፡፡ ያልታሰበውና ያልተሞከረው መንገድ አሁን ታስቧል፤ ሊሞከርም ነው፡፡ ከጊዜ ወደጊዜ ብዙው አማራ እየተቀበለው ነው፡፡
“ሰፊ አገር ሀያል አገር ይፈጥራል” የሚለው የአማራ የቆየ አመለካከት ብቻውን እውነት እንዳልሆነም ዘመኑ ራሱ ምስክር ሆኗል፡፡ በርግጥ በድሮው ዘመን ሰፊ ምድር፡ ሰፊ ከብትና ሌላም ሀብት የአንድ አገር ትልቅነት መሰረቶች ስለነበሩ አስተሳሰቡ ስህተት አልነበረም፡፡ አሁን ግን የቆዳ ስፋት ብቻውን ሀያል አገር እንደማያደርግ ታውቋል፡፡ ከዛ ይልቅ አንድን አገር ትልቅ የሚደርገው የሀዝብ ስነልቡናዊ እና ሁለንተናዊ አንድነት፤ ሳይንስና ትምህርት ናቸው፡፡ ለዘመናት ስናልመው የነበረውን ሀያልነት በዚህ መልኩ ከመቀዳጀት የሚከለክለን ነገር የለም፡፡ ስለዚህ ይህ ሶስተኛ አይን ማንም “እገነጠላለሁ” እያለ እኛን እያስፈራራ የሚኖርበትን ጊዜ በጠሰው፡፡ “እንዳይገነጠሉብን፤ አገር ይፈርሳል” እያልን በመፍራት ምንድነው የፈጠርነው? የመብት፤ የደህንነት፤ የልማት፤ የዜግነት መብቶቻችን በዚህ ፍርሀት ውስጥ ሟምተው ቀሩ፡፡ እነኝህን ሁሉ አስፈላጊ ነገሮች ለፍርሀታችን አሳልፈን ሰጠናቸው፡፡ ይባስ ብሎ አሁን እንደህዝብ ባለመኖርና በመኖር መሀል ሆነን እያጨበጨብን እንገኛለን፡፡ ይህ ሁሉ የመጣብን ሲወርድ ሲዋረድ ከመጣው የአባቶቻችን የታላቅ አገርነት ህልም አደራ ነው፡፡ በእርግጥ ብንታደልና ቢሳካ ኖሮ ሀሳቡ ባልከፋም ነበር፡፡ ግን አልሆነም፤ አይሆንምም፡፡ ሁኔታውን ለገመገመው ከደረሰብን የሚደርስብን ይበልጣል በጊዜ መፍትሔ ካላበጀን፡፡ እና ለዚህ መፍትሄ የሚሆነው ሶስተኛው አይን ከፋም ለማም ተገልጧል፡፡ ክብር ለአምላክ ይሁን፡፡ ሶስተኛው አይን ኢትዮጵያ የአማራ ሸክምና አደራ ብቻ ሳትሆን የሁሉም እንደሆነችና አማራ ብቻውን ፍዳ የሚከፍልበት ምክንያት አለመኖሩን ያሳየ መሆኑ ነው፡፡ እናፍርሳት ለሚለው ውትወታማ ተባባሪ ሆኖ ቢያፈርሳት በመፍረስዋ የተሻለ ተጠቃሚ እንጅ የባሰ ተጎጅ አይሆንም፡፡ ከዚህም በመነሳት የቤተ አማራ ልደት የግድ መሆኑን ያሰምራል፡፡
ሌላው ሁለተኛ አይን የትግሬ አይን ነው፡፡ ትግሬ በተለይ ወያኔ ሁሌ እያቆላመጥነው በአፉ “አገነጥላለሁ፤ እገነጠላለሁ፤ አስገነጥላለሁ” እያለ እያስፈራራ በልቡ ግን እየዘረፈ መኖር ነበር አላማው፡፡ እኛን በራሳችን የአንድ አገርነት ቆፈን ውስጥ አስቀምጦ መፏለልና መዝረፍ ነው አላማው፡፡ እያደረገው ያለውም ያንኑ ነው፡፡ አሁን ግን ሳያስቡት ሶስተኛው አይን ተከፍቷል፡፡ ይህም ሶስተኛ አይን ይህን አየ፡፡ አማራ እነሱን የሚያቆላምጥበት እና እሽሩሩ የሚልበት ጊዜ ማብቃቱን፡፡ አማራም ለጋራ አገር ብሎ እንጅ የዚህ የዚህ ራሱ ለብቻው መኖር እደሚችልና የተሻለ እድል እንዳለው አውቆ የራሱ ሶስተኛው አይን መገለጡን፤ ጥንትም፡ አሁንም፡ ወደፊትም የትግራይ እጣ ፋንታ አማራ ትከሻ ላይ የተወሰነ መሆኑን እና ብቻቸውን ለመቆም የማይችሉ መሆናቸውን እና ወዘተርፈ አወቀ፡፡ አሁን የተገለጠው ሶስተኛው አይናቸው የአማራ “ከትከሻየ ላይ ውረዱ፤ ሸክም ከበደኝ” ማለት ለእነሱ ወድቆ መፈጥፈጥ መሆኑን አሳይቷቸዋል፡፡ ዝንተ አለም በ “እገነጠላለሁ” እና “አገነጥላለሁ” ሰበብ እያስፈራሩ ተፈርቶ መኖር አይገኝ መቸም፡፡
የእነዚህ ሁለት ሶስተኛ አይኖች መገለጥ ታዲያ ቀድሞም ቁርኝቱ ሳብ ጉተት እንጅ “አንሳኝ ላንሳህ” ብቻ እንዳልነበረ አሳየ፡፡ በተለይ በምንም መልክ ላብራራው የማልችለው የሆነ ከጥንት ጀምሮ ገመዱን ጎትቶ አማራን የመጣል ጥረት እንደነበረ ነው፡፡ እስካሁን እንዴት በተደጋጋሚ እንደሆነ ሊገባኝ አለቻለም፡፡ ንባቤ እስከዛሬ 400 አመት ድረስ ወደኋላ ተጉዠ ይህ ጥረት እንደነበረ አሳይቶኛል፡፡ በእውነት ለምን ተደጋጋሚ የመጎተትና የመጣል ጥረት እንደተደረገ አልተገለጠልኝም፡፡ ይሁንና ቁርኝቱ የሆነ ችግር እንዳለበት እና እሱም አሁን መፈታት እንዳለበት ሶስተኛው አይናችን ገልጦ አሳይቶናል፡፡ ተፈጥሮም ራስዋ በትልቅ ወንዝ እና በረሃማ መሬት የከፈለችን ነን እኮ፡፡ የተፈጥሮውን መስመር ሰው ጥሶ ቁርኝት የፈጠረ ሁሉ ይመስለኛል፡፡ ተከዜ ወዲህ እና ወዲያ ማዶ እኮ የማይገናኝ ነገር ነበር ከድሮውም፡፡ ግድ የላችሁም የተፈጥሮ ህግ ጥሰናል፡፡ ተፈጥሮን መካስ አለብን፡፡ ራስዋ ያሰመረችውን መስመር እኛም እናክብረውና ድንበራችን ይሁን፡፡
የተፈጥሮን ድንበር በማክበራችንም ከተከዜ ሰሜን የሚጠቅመንና የሚቀርብን አንዳች ነገር የለም፡፡ በብዙዎቻችን ልብ ውስጥ ያለው የህዝቡ ፍቅር ነው የሚቀርብን፡፡ ያም ቢሆን የአንድ ወገን ፍቅር ነው፡፡ እኛ እንወዳቸዋለን እንጅ እነሱ አይወዱንም፤ እንዲያውም ይጠሉናል፡፡ የመጥላታቸው ምልክትም አማራ ላይ የሚያካሂዱት የዘር ማጥፋት እና ሌላ ከባባድ ወንጀል እነሱ መሆናቸው ነው፡፡ እስካሁን ድረስ አማራ ላይ የሚደረገውን የዘር ማጥፋት ሲቃዎሙ ያየኋቸው የተከዜ ማዶ ሰዎች 4 ብቻ ናቸው፡፡ ከዛ ውጭ ያለው ገና እናጠፋችኋለን እያለ የሚዝት እና እንደገና ስጦታ እንኳን ደስ አላችሁ የሚባባል ነው፡፡ በእውነት የትግራይ ህዝብ አማራ ባይጠላ ኖሮ አንድ ጊዜ አይደለም አምሳ ጊዜ አማራ ወንድማችን ነው አታጥፉት ብሎ የተቃውሞ ሰልፍ ያደርግ ነበር፡፡ እኔም አማራን እንደህዝብ ይጠሉታል ስል የራሳቸውን ልበ ደንዳናነት እንደምስክር በመቁጠር ነው፡፡ መቸም ከራሳቸው በላይ ሌላ ምስክር ልጠራላቸው አልችልም፡፡ እኛ ግን እንወዳቸዋለን፡፡ ወይም አልጠላናቸውም፡፡ እንግዲህ መለያየቱ ብቸኛ መፍትሄ እየሆነ መጥቷልና ለእነሱ ያለንን ፍቅር እንደምንም ችሎ መለያየት ነው፡፡ ጠንከር ብሎ መቻል ነው እንግዲህ፡፡ እና በሰላም እንፋታ፡፡ አለን የሚሉትን ታሪካቸውን ይዘው ይሂዱ፡፡ ቋንቋቸውን ያበልጽጉ፡፡ ሁሉንም ነገር እኛ ከቶ የምንነካባቸው ነገር አይኖርም፡፡ አለን ከሚሉት ታሪክ አንድም መስመር አንወስድም፤ የእኛን የራሳችንን ታሪክ እንመርቅላቸዋለን፡፡ የዘረፉትን ሀብትም ይዘው ይሂዱ፡፡ አንጠይቃቸውም፡፡ ያለንን ሁሉ ተጨማሪ ሰጥተናቸው ብንለያይ ለእኛ በጣም ጥሩ ነው፡፡ እኛን ከማጥፋት እናድን እና እንሸኛቸው እንጅ ሀብትን እንደገና ሰርተን እናፈራዋለን፡፡
“ጨቋኝ ብሄር” ከሚሉት አማራ ተነጥለው ለራሳቸው “በፍቅርና በተድላ ይኑሩ”፡፡ እኛም ለራሳችን እንኑር፡፡ ይሄን ለዘመናት እየጎተተ ሲጥለን የኖረ አጉል ገመድ እንበጥሰው፡፡ በርግጥ መበጠሱን መደበኛ እናድርገውና እውቅና እንስጠው ይባል እንደሁ እንጅ በዚህ 24 አመት ውስጥ ሲመነምን ከርሞ አሁን ፈጽሞ ተበጥሷል፡፡ ከአንግዲህ የሚኖረን ግንኙነት ከወንዝ ማዶ እና ማዶ እንጅ “እንዲህ አደረግከኝ”፤ “እንዲህ በደልከኝ”፤ “ፈለጥከኝ” “ቆረጥከኝ” መባባሉ ያቆማል፡፡ ፍቅር ጥሩ ነገር ቢሆንም እስኪያጠፋህ መሆን ግን የለበትም፡፡ ለፍቅር ብሎ አንድ ወይም ብዙ ሰው ሊጠፋ ይችላል፡፡ ያንን በማለትም በየዘመናቱ ስንሞትላቸው ኖረናል፡፡ ስለፍቅር ብሎ ግን መላው የራስ ዘር እንዲጠፋ መተባበር ወንጀል ነው፡፡ በተለይ የሚወዱትና ስንት የሆኑለት ሰው አንቆ ሲገድል እና ዘር ሲያጠፋ እያዩ መፍትሄ አለመፈለግ የባሰ ሀጢአት ነው፡፡ ፍቅርም የሚያምረው ሁለቱም ሲደጋገፉ ነው፡፡ አንዱ ለመጣል፤ ሌላው ለማንሳት በሆነበት ግንኙነት ውስጥ መኖር ግን ፍቅር ሳይሆን ነዝናዛ ትዳርን ይመስላል፡፡ የነዝናዛ ትዳር ደግሞ መፍትሄው ፍች ብቻ ነው፡፡ አለበለዛ በነዝናዛ ትዳር ውስጥ ከሁለት አንዱ የአንዱን አንገት በቢላ ሊቆርጠው ይችላል፡፡ ይህንንም እያየን መሰለኝ፡፡
የአማራ የመከራ ቀንበር የከበደው በውኑ ከሰማይ በወረደ እርግማን ነውን? አይደለም፡፡ የአማራ የመከራው ሁሉ ምንጭ የተከዜ ማዶ አገር ነው፡፡ የተከዜ ማዶን ሰው አብረን እንኑር ባልን፤ አንድ አገር እንሁን ባልን አይደለም ወይ ይህ ሁሉ የመጣብን? እነሱ ሄዱልን ማለት እኮ ዛሬ የምናየው ስቃይ አይኖርም ማለት ነው፡፡ ከተከዜ ማዶ አገር ህዝብ ጋር መፋታት እና ከአማራ ጀርባ ላይ ወርዶ ራሱን ችሎ እንዲኖር ማድረግ እኮ ለአማራ የመፍትሄዎች ሁሉ መፍትሄ ነው፡፡ እንዲህ የምንሆነው እኮ ለዩጋንዳ ወይም ለቱኒዚያ ህዝብ አይደለም፡፡ እንዲህ የምንሆነው እኮ ለአማራ ለራሱ ብለን አይደለም፡፡ እንዲህ የምንሆነው በተከዜ ማዶ አገር የተነሳ ነው፡፡
አባቶቻችን ከአጋም የተጠጋ ቁልቋል ሲያለቅስ ይኖራል አሉ፡፡ እያወቁ ግን ማለያየት ሲገባቸው የበለጠ አጠጋግተውን ሄዱ….
(ማሳሰቢያ፡- በራሱ የወራሪው ህገመንግስ አንድ የፌደራል መንግስቱ አባል መንግስት ተከፋሁ ተገፋሁ (ለአማራ በተለይ ደግሞ ተደፋሁ) ካለ መለየት መብት ነው፡፡ ስለሆነም ከላይ የተጻፈው የመብት ጥያቄ እንጅ የወንጀል ወይም የአድማ ድርጊት አይደለም፡፡)
From
https://www.facebook.com/permalink.php?story_fbid=926245850756173&id=808909555823137

Wednesday, July 22, 2015

“አንች እየኮሰተርሽ እኔን ታሸክሚያለሽ”

“አንች እየኮሰተርሽ እኔን ታሸክሚያለሽ” ------የበላይ አማት
ከረጅም ጊዜ በፊት ካነበብኩት እንድ ምንነቱን የረሳሁት ጋዜጣ ላይ ይህንን አስታውሳለሁ፡፡ ጋዜጣው ላይ የቀረበው ጽሁፍ የበላይ ዘለቀ ጓደኛ እና አርበኛ የነበሩ ሰው የተናገሩት ነው፡፡ በላይ ዘለቀ ለምን አባ ኮስትር እንደተባለ ከዛ ጊዜ ጀምሮ ነው የማውቀው፡፡ ሙሉ በሙሉ ባላስታውሰውም ልቤ ውስጥ የቀሩት ታሪኮች እኒህ ናቸው፡፡ በላይ የጎጃምን ጦረኞች እየመራ ጸረ ጣልያን ፍልሚያ ሲያደርግ ከጓደኞቹ ጋር ብቻ አልነበረም፡፡ በባህላችን አንቱታ የሚቸራቸው እና የልጅ ባል የሚንቀጠቀጥላቸው ሰው አብረውት አርበኝነት ላይ ነበሩ፡፡ አማት ከልጃቸው ባል ጋር፡፡ እና በሶማ በረሀ ይመስለኛል ሰሳ (ድኩላ) እያደኑ ይመገባሉ፡፡ አማትና አማች፡፡ በመጀመሪያ አማት ይተኩሳሉ፡፡ ይስታሉ፡፡ ከዛ በላይ ይተኩሳል፡፡ ይገድላል፡፡ አሁንም እንደገና አማች ይተኩሳ፡፡ ይስታሉ፡፡ ከዛ በላይ ይተኩሳል፡፡ ይገድላል፡፡ በኋላ የሚገደሉት ሰሳዎች ሲበዙ አማት መሸከም ይጀምራሉ፡፡ በላይ ግን አሁንም ተኩሶ ይጥላል፡፡ አማት ይሸከማሉ፡፡ ከዛም እንዲህ አሉት “አንች እየኮሰተርሽ እኔን ታሸክሚያለሽ፤ ከዛሬ በኋላ ኮስትር በላይ ብየሻለሁ” አሉት፡፡ ከዛ ወዲህ አባ ኮስትር በላይ ዘለቀ ተብሎ ቀረ፡፡

እኒህ አርበኛ ይቀጥላሉ፡፡ ከአራቱ የእንግሊዝ ጀኔራሎች የቱ እንደሆነ አላስታውስም (ምናልባት ጀኔራል ዊንጌት ሳይሆን አይቀርም)---በበላይ የሚመሩት አርበኞች እና በዚህ እንግሊዛዊ ጀኔራል የሚመሩት የእንግሊዝ ወታደሮች ጣምራ ዘመቻ ያካሂዳሉ፡፡ በላይና ጀኔራሉ ኢላማ ተኩስ ይሞካከራሉ፡፡ በላይም ጀኔራሉን ያስከነዳዋል፡፡ በዚህ መሀል የበላይ አርበኞች የጣልያን ወታደሮችን እየገደሉ ሲጨፍሩ ያያል፡፡ በጣም ደነገጠ፡፡ እኒህ አባት አርበኛ ታዲያ የእንግሊዙን ጀነራል ሁኔታ ሲገልጹት “ነጭ ሲደነግጥ የበለጠ እንደሚነጣ የዛን ጊዜ ነው ያየሁት” ይላሉ፡፡

አምሐራ ማለት ነጻ ህዝብ ነው የሚለው መጠሪያችን የተፈተነበት እና ተፈትኖ ያለፈበት ጊዜ ቢኖር የአምስት አመቱ የጣልያን ወረራ ነው፡፡ ብዙ የአፍሪካ፤ የእስያ፤ እና የአሜሪካ ጎሳዎች (ህንድን እና ቻይናን ይጨምራል) በአውሮፓዊያዊያን ግዛት ስር ሲወድቁ በጠበመንጃ፤ በብርድ ልብስ፤ በሳህን፤ በስኒና ብርጭቆ፤ በመጋረጃና ምንጣፍ እንዲሁም በሰአት እየተታለሉ ነበር አገርና ህዝባቸውን የሸጡት፡፡ ወደ እኛ አገር ሲመጡ ግን ነገሩ የተለየ ሆኖ ነበር የጠበቃቸው፡፡ ስለሀገሩና ወገኑ ሞትን የማይፈራ፤ ጥቅም የማይደልለው ህዝብ አጋጠማቸው፡፡ መላው አማራ በነቂስ ለክብርና ለነጻነቱ ተዋደቀ፡፡ ከእነዚህ እልፍ ጀግኖች መካከል አንዱ የዛሬው ታሪካችን ዝክር በላይ ዘለቀና እና የጎጃም አርበኛ ሰራዊቱ ነው፡፡ ቤተ አማራ በጎጃም ሳምንት የነጻነታችን ፈርጥ አድረጎ ከሚያስቀምጣቸው አንዱ አባ ኮስትር በላይ ዘለቀ ነው፡፡

ይህ በላይ ዘቀ እና ጓደኞቹ የአምሐራ ልጆች ናቸው፡፡ የታሪክና ህዝብነታቸው ማንነት እርሱም በማንም የማይወረር (The Unconqourable) ነጻ ህዝብነት ፈተና ላይ በወደቀበት ክፉ ጊዜ የተገኙ፡፡ አምሐራ ነጻ ህዝብነቱ ይረጋገጥና ከነሙሉ ትርጉምና ክብሩ ይቀጥል ወይስ ይወረርና ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ነጻ ህዝብነቱ ይቋረጥ የሚል ሞትን የሚጠይቅ ውሳኔ መጣባቸው---በዘመኑ ለነበሩ መላው አማራ እናት እና አባቶቻችን፡፡ ከእነዚሁ አንዱ በላይ ነውና በዚህ አጣቂኝ ፈተና ውስጥ የወደቀው ቁርጥ ውሳኔ ማድረግ ነበረበት፡፡ በበኩሉ የአምሐራ ነጻ ህዝብነት በእርሱ ዘመን ሊገረሰስ እንደማይገባ ከጓደኞቹ ጋር መክሮ ዘክሮ ወሰነ፡፡ የአማራ ነጻ ህዝብነት መቃብራችን ላይ ብቻ ይገረሰሳል፤ ክንዳችንን ሳንንተራስ ምድራችንን ነጭ አይፈነጭባትም፤ ህዝባችንም ወደ ባርነት አይወርድም ብለው ተማምለው በረሀ ወረዱ፡፡ ይህም በላይ እልፍ የጎጃም ፋኖዎችን አስከትሎ ለአምሐራ ነጻ ህዝብነት ተዋደቀ፡፡ አባቶቻችንም በደማቸው የአማራን አይበገሬነት እና አይነኬነት አረጋገጡ፡፡ በማንም የማይወረር መሆኑን አረጋገጡ፡፡ ያች ከጥንት የነበረች የነጻ ህዝብ ደም ከትውልድ ወደ ተውልድ ስትሸጋገር የበላይ የደም ስር ውስጥ ተገኘች፡፡ እርሱም አላሳፈራትም፡፡ ልክ ሌሎች አቻዎቹ እና ጓደኞቹ እንዳደረጉት ሁሉ እርሱም ነጻ ህዝብነታችን ሳይቋረጥ ለእኛ እንዲደርስ አደረገ፡፡

በላይ ዘለቀ በአለም ታሪክ ያልተንበረከከው የአማራ ህዝብ ልጅ ነው፡፡ እኔም የማይንበረከክ ህዝብ ልጅ ነኝ እና በደሜ ውስጥ የበላይ የአምሐራ ነጻ ህዝብነት ደም አለች፡፡ ለእርስዋ መቀጠልም ዛሬ ወገኔን በማንቃት እየተጋሁ ነው፡፡ ነገ ደግሞ ለአማራ ነጻ ህዝብነት ስል እገብራታለሁ፡፡ እኔ መለክ ሐራ የነጻ ህዝብ ልጅ ነኝ ስል የጎጃም፡ የሸዋ፡ የወሎ፡ እና የጎንደር አባት እና እናቶቸ ደም ሰጥተውኛል ማለት ነው፡፡ ደም የተከፈለብኝ የመስዋእትነት ልጅ ነኝ ማለት ነው፡፡ ወይም በደም ውል የተፈረመ ነጻነት የተቀበልሁ ሰው ነኝ ማለት ነው፡፡ ከእነዚሁም በላይ ዘለና እና ጓደኞቹ የከፈሉልኝን ደም ዛሬ የምዘክረው ነው፡፡ እኔ እንድኖር ሌላ ሰው ሞቶልኛል፡፡ እኔም ነገ ልጀ እንዲኖር አድክምለታለሁ፤እሞትለታለሁ፡፡ እኔም ነገ ልጀ እንድትኖር እድክምላታለሁ፤ እሞትላታለሁ፡፡ ክብርና ነጻነቱን በሞቱ የሚገዛ ህዝብ ልጅ ነኝ፡፡ ከዚህም ተነስቸ ትምክህተኛና ኩሩ መሆኔን በአደባባይ አውጃለሁ!

ሰማይና መሬት ሙሉ ምስጋና ለበላይ ዘለቀ! ሰማይና ምድር ሙሉ ክብርና ምስጋና ለጎጃ አርበኞች! ሰማይና ምድር ሙሉ ክብርና ምስጋና ለመላው አርበኛ አማራ ህዝብ ይሁንልኝ፡፡ እኔን ትምክህተኛ ያደረጋችሁኝ ለእኔ በከፈላችሁት ደም ነው፡፡ የደም ዋጋየ ትምክህትና ኩራት ናት፡፡ ማንም የትምክህትን ትርጉም ባለማወቁ ትምክህተኛ ብሎ ሊያሸማቅቀኝ ቢሞክርም እኔ ግን ለእኔ ትምክህተኛነት የሰውነት ምልክቴ ናት፡፡ ምን እንደተከፈለልኝ ጠንቅቄ የማውቅ ነኝ እና ደም የተከፈለባትን የዘለአለም ቃል ኪዳኔን ትምክህቴን በከንቱ አልጥላትም፡፡

ሁላችሁም የነጻ ህዝብ ልጆች የበላይ አደራ አለባችሁ…….
ጎጃም ቤተ አማራ

Tuesday, July 21, 2015

ያልገባንን እንጠይቃለን!

ያልገባንን እንጠይቃለን!
(የትነበርክ ታደለ)
የትግራይ ክልል ዞኖች እንዴት በአቅጣጫ ብቻ ተሸነሸኑ? ሌሎች ክልሎችስ እንዲሁ ደቡብ ኦሮምያ፣ ምስራቅ ኦሮምያ....መካከለኛው ደቡብ ክልል...ላይኛው አማራ....ደገኛው አማራ...ቆለኛው ምናምን መባል አይችሉም ነበር? ለምን ሌሎች ክልሎች በተጨማሪ የብሄረስቦች ክልል ሲከፋፈሉ ትግራይ ብቻ እንዲህ ጥርት ብሎ ቀረ? ነው ወይስ ትግራይ ውስጥ ፍጹማዊ የቋንቋ፣ የባህልና የሀይማኖት አንድነት በመኖሩ ነው?
የእነ ኩናማ ፣ ኢርሮብ ፣ አገው እና የመሳሰሉት ባሀለ ቋንቋ ለምን ይደበቃል ሁሉን በዘር ከከፋፈሉት አይቀር?


ጎጃም፡ አማርኛ፡ ቅኔ፡ ሙዚቃ፡ ፍቅር እስከ መቃብር

ጎጃም፡ አማርኛ፡ ቅኔ፡ ሙዚቃ፡ ፍቅር እስከ መቃብር

አማርኛ ከ51 የአለም ዋና ዋና ቋንቋዎች አንዱ ሲሆን በ45ኛ ደረጃ ተቀምጦ ይገኛል (http://www.assam.org/)፡፡ አማርኛ የራሱን (የወላጅ እናቱን ግእዝን) ፊደል በመጠቀም ዘመናዊነትን የተቀላቀለ ሰፊ ቋንቋ ነው፡፡ ከአረብኛ ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ የሚገኝ ትልቁ የሴሜቲክ ቋንቋ ነው፡፡ ማለትም አማርኛ ከአረብኛ ቀጥሎ ትልቁ የሴማዊያን ቋንቋ ነው ማለት ነው፡፡ የአማርኛ ቋንቋ በስነ ጽሁፍ ረገድ በጣም ያደገ ነው፡፡ ይህም የአማራ አስተዋጽኦ ነው፡፡ በራሳቸው ፊደልና ቋንቋ ከሚጠቀሙ ጥቂት አገራት አንዷ ኢትዮጵያ እንድትሆን ያስቻለ ነው፡፡ ታዲያ በዚህ ዘመን የአማርኛ ስነጽሁፍ የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው ጎጃም ነው፡፡ በጠቅላላው አማራ በተለይ ደግሞ በጎጃም ሀሳብን በጽሁፍ መግለጽ ትልቅ ልማድ ነው፡፡ የዚህም ማህበራዊ ልማድ አማርኛችን የጽሁፍ ቋንቋነቱ እንዲዳብር አድርጓል፡፡ ይህንንም ስንል በቁጥር ከፍተኛ ዘመናዊ ጸሀፍት የወጡት ከጎጃም ነው፡፡ እናመሰግናለን፡፡

ቅኔ ትልቁና ጎጀም በተለይ ጠብቃ ያቆየችልን እና ያበረከተችልን የአማራነታችን ጸጋ ነው፡፡ ሰምና ወርቅ የሆነው አማራ ትክክለኛ መገለጫው ቅኔ ነው፡፡ ቅኔ ለረጅም አመታት መማርን እና ልዩ የመረዳት ጸጋን የሚጠይቅ ነው፡፡ በቅኔ ረቂቅ የሆነ እሳቤን የምንኖርበት ነው፡፡ በአለም ላይ የኛን ያህል የዳበረ ሰምና ወርቅ ግጥምና ንግግር ያለ አይመስለኝም፡፡ የማገኛቸው የውጭ አገር ሰዎች ስለ ቅኔ ስነግራቸው መጀመሪያ ግር ይላቸዋል፡፡ ቆይተው ግን በጣም ይደነቃሉ፡፡ ይህ እንግዲህ የምናብ እድገትን የሚያመለክት ነው፡፡ በቅኔ ነገራትን እያመሰጠሩና እየተራቀቁ ለጥበብ መኖርና በጥበብ መኖር የአማራ ባህል ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ አማርኛ በጣም ጥልቅ ቋንቋ እንዲሆን አስችሎታል፡፡ አሁን አሁን እየተረሳ በተራ ንግግር እየተተካ መጣ እንጅ በድሮ ጊዜ ንግግርን በቀጥታ መናገር ብዙም ጥሩ አልነበረም ይባላል፡፡ የንግግር ብስለት የሚለካው ነገርን በምስጢር በመነጋገር ነበር፡፡ ካልተሳሳትኩ ትልልቆች እንደ ነገሩኝ ይህንን የድሮ ንግግር ዘዴ ሰለመን ብለው ይጠሩታል፡፡

በሙዚቃም ጎጃም ትልቁን ድርሻ ይወስዳል፡፡ በእርግጥ ጎንደር በዚህ በጣም የታወቀ ይመስላል፡፡ አንዲት አሜሪካዊት ፕሮፌሰር ያጠናችውን ጥናት (“The Musician and Transmission of Religions Tradition: The Multiple Roles of the Ethiopian Dabtara”, 1992) እዚህ ላይ እጠቀማለሁ፡፡ ወጣቶች የሚማሩት አንዱና ትልቁ እውቀት የዜማ እውቀት ነው፡፡ ከሶስቱ በአንዱ ዜማ ቤቶች ይማራሉ፡፡ ዋናውና በጣም የታወቀው ዜማ ቤት በደቡባዊ ጎንደር፤ ከደብረታቦር 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ቤተልሄም የዜማ ትምህርት ቤት ነው፡፡ ከጥንት ጀምሮ ታዋቂነት የነበረውና በግራኝ ጦርነት ጊዜ የያሬዳዊ ዜማን ከመጥፋት ያዳነልን ዜማ ቤት ነው፡፡ ሁለተኛውም ዜማ ቤት እዚሁ ደቡባዊ ጎንደር የሚገኘው ቆማ ፋሲለደስ ገዳም ነው፡፡ ይህም በ17ኛው መቶክፍለ ዘመን መጀመሪያ ማለትም በአጼ ፋሲለደስ እርዳታ መሆኑ ነው እንደተመሰረተ ይነገራል፡፡ ሶስተኛው ደግሞ አቻበር የሚባለው ሲሆን ከብሩር ማርያም ገዳም ጋር የተያያዘ ነው፡፡ መገኛውም በሰሜናዊ ጎጃም ነው፡፡ የዜማ ስልቱም ከቆማ ፋሲለደስ ጋር ተቀራራቢ ነው፡፡

ከቅኔ ወደ አማርኛ ስንመጣ ይህን እናገኛለን፡፡ Job Ludophus (1682) በጻፈው የኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነ የምእራባዊያንን አካደሚያዊ ስልት የተከተለ ታሪክ ስለ አማርኛ እና የአማራ ግዛቶች የቋንቋ አንድነት የሚከተለውን ብሏል፡፡ “To the Amharic Language, those of the Neignbouring Kingdoms come the nearest; though their Dialects are different one from another; for that of Bagemeder is peculiar: Angota, Hata, Gojam, and Shewa, use a Dialect common to one another” (ገጽ 80):: Hata ያለው የትኛውን አካባቢ እንደሆነ ማወቅ አልቻልኩም፡፡ ይህ ጸሀፊ የኢትዮጵያ ታሪክ ብሎ ሲጀምር በአማራ ግዛት ትልቅነት እና ስልጡንነት ነው የሚጀምረው፡፡ “Amhara is now the most noble kingdom of Ethiopia” (ገጽ 13) በማለት:: ይህም ከዚህ ጸሀፊ ቀድሞ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው አባ ጀሮሜ “The inhabitants of the Kingdom of Amhara are the most civilized and polite” ካለው ጋር የሚጋጠም ምስክርነት ነው፡፡

ስለጎጃም ስንጽፍ እንግዲህ የቅኔ ቤቶችን እንጠቅሳለን፡፡ ከዚህም ዲማ ጊዮርጊስ ዋናው አድባራችን ነው፡፡ አለም ያወቀው ስለሆነ ዛሬ ስለዲማ ብዙ አልልም፡፡ ከዚህ ይልቅ ከዲማ ስለመነጨው ፍቅር እስከ መቃብር ነው ትንሽ ማለት የወደድኩት፡፡ ፍቅር እስከመቃብር ከዘመነ መሳፍንት ጀምሮ በአማራ ላይ ስለደረሰው አስተዳደራዊ በደል እንዲሁም ፍቅርና እሴት ቁልጭ አድርጎ ያሳየ መጽሀፍ ነው፡፡ ፍቅር እስከመቃብር በወጣበት ዘመን የነበሩ የአማራ ጥላቻ አቀንቃኞች አማራ ጨቆነን ሲሉ ያንን መጽሀፍ አለማንበባቸውን ቢያነቡትም አለመረደታቸውን ያመለክታል፡፡ ሀዲስ አለማየሁ ትንቢት በሚመስል መልኩ አማራ ያለፈበትን ሰቆቃ በደንብ አስቀመጥውላቸው ነበር፡፡ ያንንን መከራ ያሳለፈ ህዝብ በምንም መንገድ ጨቁዋኝ እና ጠላት ተደርጎ ባልተዘመተበትም ነበር፡፡ ሳይረዱት ቀርተዋል ወይም ሆነ ብለው በተንኮል ጆሮ ዳባ ልበስ ብለውታል፡፡ በምንም ተአምር ፍቅር እስከመቃብርን ያነበበና በውስጡ የተገለጹትን የእውነታ ነጻብራቅ የሆኑ ታሪኮችን የተረዳ ለአማራ ሊያዝንለት እንጅ ጠላቴ ብሎ ሊነሳሳበት ባልተገባም ነበር፡፡ ግን እስካሁን ድረስ እኛ አማሮች የሚረዳን በማጣት በጠላትነት ተፈርጀን ቀረን፡፡ የእኛን ችግር የሚረዳ በመጥፋቱም ህዝባችን ለታላቅ ጥፋት ተዳረገ፡፡ ከውስጡ የወጡትም እንኳ ለመረዳት ይሸፈንባቸዋል፡፡ ያ የታሪክ ማማ የደረሰ እና ለአገር ጠላቶች አገር ሰርቶ በደሙ አጥሮ የሰጠ ህዝብ ዛሬ በወያኔ ሴራ በአለም ላይ ቁጥር አንድ ደሀ ህዝብ እንዲሆን ተደረገ፡፡

አሁን ግን የህዝባችን እጣ ፈንታ በቤተ አማራ ትውልድ ላይ ወድቋል፡፡ ሁሉንም አቅማችንን ተጠቅመን እንሰራለን፡፡ ህዝባችንን ከወደቀበት የታሪክ አዘቅት እናወጣለን፡፡ ከዘመነ መሳፍንት በፊት ወደ ነበረበት ማማው እንመልሰዋለን! ይህንን ባናደርግ ግን እኛ ራሳችን በታሪክ ፊት አሳፋሪ ቡትቶ ለባሽ ሆነን እንቀራለን፡፡

በዚህ አጋጣሚ ከጎጃም ለበቀሉ ጸሀፍት የክቡር ሀዲስ አለማየሁን ፈለግ በመከተል በህዝባችን ላይ የሚደርሰውን ግፍ እንድትጽፉ እመኛለሁ፡፡ የትግል ግማሹ ስነ ጽሁፍ ነው፡፡ በደህና ቀን በአባቶቻችን ዳብሮ እና አድጎ የተሰጠንን አኩሪ ስነጽሁፋችንን በመጠቀም ወገናችንን እናንቃበት እናም ከፈጽሞ ጥፋት እንታደግበት፡፡ አማርኛን ለአማራ መድህንነነት እንጠቀምበት!

ጎጃም ቤተ አማራ

Monday, July 20, 2015

አማራ ለሆነ ፍጥረት ሁሉ! አማራ ነን ብለን ስም ያለው ሞት እንሙት!

አማራ ለሆነ ፍጥረት ሁሉ!
አማራ ነን ብለን ስም ያለው ሞት እንሙት!
ማንህም አማራ ነኝ ብለህ የምታስብ ሰው፤ አማራ ነኝ ብለህ ባታስብ እንኳ አማራ ነህ ተብለህ የተፈረጅክ ሁሉ ይህንን ስማ፡፡ ጠላትህ በጸጉርህ ቁጥር ነው፡፡ የምታውቀውን ጠላትህን መናቅህ እና ስውር የሆነ ብዙ ጠላት እንዳለህ ባለማወቅህ ለዚህ ደርሰሀል፡፡ ይህ ዘመን ሁሉንም ነገር ትተህ አማራ ብቻ እንድትሆን የሚስገድድህ ነው፡፡ ከሰማይ በታች ከራሳችን በቀር ማንም የሚደርስልን እንደሌለ እንወቅ፡፡ ከጫፍ እስከ ጫፍ እንደ አንድ ሰው አሳቢ እንደ አንድ ልብ መካሪ እንሁን፡፡ ምድር ከፍ ሰማይ ዝቅ ቢል ለእኛ መፍትሄው አማራነት ብቻ ነው፡፡ ከፕሮፌሰር አስራት ጀምሮ ብዙ ሰዎች አማራነትህን በአማራነትህ ለታወጀብህ ጥፋት መፍትሄ እንድታደርገው ተነግሮህ ነበር፡፡ ግን አማራ አይደለሁም፤ ኢትዮጵያዊ ነኝ፤ ዘረኛ መባል አልፈልግም እና ወዘተ እያልክ እምቢ አልክ፡፡ አሁን ተራ በተራ እያለቅክ ነው፡፡ ዛሬ አማራን መግደል ጎመን እንደመቀርደድ ቀላል ሆኗል፡፡ ዛሬ አማራን መግደል ህግ ነው፡፡ ገና ከዚህ የከፋ ያደርጋሉ፡፡ ለምን? አማራ ጠላታችን ነው መጥፋት አለበት ብለው ስለተነሱ፡፡ አማራ ጠላቴ ነው የሚል አገዛዝ እና ተግቶ የሚያጠፋህ አገዛዝ እንዴት ሆኖ ያንተ መንግስት ሊሆን ይችላል? መንግስት የለህም፡፡ ያለኸው አንድ በእንድ እስከሚያጠፋህ በማይለቅህ የጠላት አስተዳደር ውስጥ ነው፡፡ በጠላት እጅ እንዳለህ ማወቁ አንድ እርምጃ ነው፡፡ ቀጣዩ ደግሞ እኔ እንደዚህ ነኝ፤ እኔ እንዲያ ነኝ የሚለውን ማናቸውንም ነገር ትተህ በአስተሳሰብም በመንፈስም በስሜትም አንድ አማራ መሆን ብቻ ነው፡፡ ዙሪያህን የከበቡህ ጠላቶችህ ተዘጋጅተው ጨርሰዋል፡፡ ከዚህ በኋላ እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ፤ ዘረኛ አይደለሁም እያልክ ብትሰንፍ ትርፉ ለማንም ሳትሆን መጥፋት ነው፡፡ እርስ በእርስ እንደሰንሰለት ተያያዝ፤ ተነጋገር፤ ተባበር፡፡ ይህን ካደርግክ ጠላት በፊትህ ሊቆም ዘንድ አይችልም፡፡ ይህን በግፍ ተቀጥቅጦ የተገደለ ሰው የእናንተ ወንድም ነው፡፡ ገናም እንደነዚህ ያሉ ወንድሞችና እህቶቻችሁ በማጎሪያ ውስጥ ናቸው፡፡ ሊገደሉ ቀን የተቆረጠላቸውም ሞልተዋል---መቸም አታጣውም፡፡
በጠዋት የረገፍከው ሳሙኤል አወቀ ነፍስህን በገነት ያኑርልን!
አማራ ይቅደም ጠላቱ ይውደም!

Sunday, July 19, 2015

ሌተናል ጀኔራል ሃይሉ ከበደ (በኢትዩጵያ ታሪክ ዉስጥ የመጀመሪያዉ ሌተናል ጀኔራል)

ሌተናል ጀኔራል ሃይሉ ከበደ (በኢትዩጵያ ታሪክ ዉስጥ የመጀመሪያዉ ሌተናል ጀኔራል)
........................................................................(በአሹ ዋሴ የቀረበ)
ሌተናል ጀኔራል ሃይሉ ከበደ
ዋግ ሹም ጓንጉል የንግስና ዘመናቸዉ 1894-1905 ነበር፡ እርሳቸዉ በተሸሙበት ወቅት የአድዋ ጦርነት በመካሄዱ ጀግናዉን የዋግን ህዝብ ጦር በመምራት ታላቅ ጀብድ ፈፅመዋል ፡፡ዋግ ሹም ጓንጉል ብሩ ይመሩት የነበረዉ የዋግ ጦርም በአድዋዉ ጦርነት ጊዜ ከ 400 የሚበልጡ ጣሊያኖችን እንደማረከ ታሪክ ይናገራል፡፡ዋግ ሹም ጓንጉል ብሩ የጦር ሜዳ ጀግና መሆናቸዉ ከመታወቁም ሌላ በአስተዳደርም ዝነኛ ፍርድ አዋቂ እንደነበሩ ይነገርላቸዋል፡፡የእራስቸዉን ታሪክ የሚያዉቁ አባቶች እንደሚሉት (አንድ ግዜ ለዋግ ሹሞች ከየገበሬዉ እየተመለመለ የሚወሰደዉን ከ 10 አንድ ፍየል ሙክት ለመመልመል ተልከዉ የሄዱ መልክተኞች መምጣታቸዉን አስቀድሞ የሰማ ሃብታም ገበሬ‹ የሰቡ ሙክቶችን መርጦ ዋሻ ዉስጥ በመደበቅ የከሱትን ብቻ አቅርቦ አሳየ፡፡ በዚህም ግዜ ጠቋሚ በዋሻ የደበቃቸዉን አንድ ሺ ያህል ሙክቶች ስለ አስያዘበት በሙሉ እንዲወረስ ተደረገ፡፡

ይሁን እንጅ ገበሬዉ ለዋግ ሹም ጓንጉል አቤት ለማለት ቤጊዜዉ ቢመላለስ እሳቸዉ ለፍርድ ካልተቀመጡ በስተቀር በመንገድ ላይ አቤቱታ ስለማይቀበሉ በጣም ተጉላላ እና ስለተናደደ ከፊታቸዉ ቁሞ ሰደባቸዉ ፡፡ በዚህ ግዜ ጉዳዩ ምን እንደሆነ እንዲያስረዳ ተጠይቆ በዝርዝር ስለተናገረ የተወረሱት ሙክቶች እንዲመለሱለት እና ሁለተኛም በሳቸዉ ዘመን ምልምል እንዳይመለመልበት ስለተደረገለት መልማዮቹ ወደሱ ሲሄዱ ጓንጉል ይብቃ የሚለዉን ነፃ ያደረገዉን የፍርድ ቃል በመጥቀስ ሳይመለመልበት ኖሯል፡፡

ከዋግ ሹም ጓንጉል ሞት ቡሃላ ዋግ ሹም ከበደ ተሹመዋል፡፡ እሳቸዉም ደግና ሃይማኖተኛ መሪ እንደነበሩ ይነገርላቸዋል፡፡ እንደ አባቶች አገላለፅ ዋግ ሹም ከበደ ለድሃ አዛኝ እና ፍርድ እንዳይጓደል የሚጥሩ ነበሩ፡፡ሹመት የሚሰጡት ለዋግ ዘሮች ብቻ ሳይሆን የማስተዳደር ችሎታ እና እዉቀት ላላቸዉ ሰዎች ጭምር ነበር፡፡ ጉቦንም በከፍተኛ ደረጃ ይቃወሙ ስለነበር በአንድ ወቅት አንዲት ድሃ ሴት ለጉዳይ መታያ ጉቦ ባዶ ሞሰብ ይዛ በመሄዷ እንጀራ ተቀባዩ ጉቦ መቀበል እንዳለበት ይገነዘባል፡ ባዶ መሆኑን ካረጋገጠ ቡሃላ ሊያሲዛት ቢሞክርም ቢቸግራት ነዉ
ብለዉ መለሱዋት እና ጉዳይዋን ፈፅመዉ ላኳት ይባላል፡፡

ዋግ ሹም ከበደ በላስታ እና በጎንደር ባላባት የሆኑትን የደጃዝማች ንጉሴ ፋሪስን ልጅ ወይዘሮ ሂሩትን አግብተዉ ሌተናል ጀኔራል ሃይሉን፡ እንዲሁም ደጃዝማች በላይን፡ ፊት አዉራሪ ገሰሰን፡ደጃዝማች በላቸዉን፡‹ጣሊያን ጋር ሲዋጉ የተገደሉ› ፡ደጃዝማች እጅጉን እና ግራ አዝማች በዛብህን ወልደዋል፡፡ ከዋግ ሹም ከበደወዲህም የዋግን የቆየ ጀግንነት እንዲታደስ ያደረጉት ልጃቸዉ ደጃዝማች ቡሃላ ሌተናል ጀኑራል ሃይሉ ከበደ ናቸዉ፡፡

ጀኔራል ሃይሉ ከ1927-1933 ኢትዮጵያን የወረረዉን የፋሽስት ጦር በማርበድበድ ጀግናዉን የዋግን ህዝብ አሰልፈዉ በቆራጥነት ሲዋጉ ፡ ወለህ በተባለዉና የሰቆጣ ከተማ አቅራቢ በሆነዉ የጦር አዉድማ ላይ አንገታቸዉ በጠላት ተቆርጦ ወደ ጣሊያን ሮም ሲወሰድ፡ ተራፊዉ አካላቸዉ ደግሞ ከሰቆጣ ከተማ በታች በሚገኘዉ እና ጉድጉዳ በተባለዉ ገደል እንዲጣል ተደርጉዋል፡፡ ሆኖም የአከባቢዉ ገበሬዎች አስከሬናቸዉን ወድቆ በማግኘታቸዉና የእራሳቸዉ መሆኑን በመገንዘባቸዉ ከአንድ የተወሰነ ቦታ ላይ ቀብረዉት ቆይተዋል፡፡ ፋሽስት
ጣሊያን ተሸንፎ የኢትዮጵያ ነፃነት ሲመለስ ግን አፅማቸዉ ከተቀበረበት ቦታ ተቆፍሮ ከወጣ ቡሃላ የአያታቸዉ የዋግ ሹም ተፈሪ ፡የአባታቸዉ የዋግ ሹም ከበደ አፅም ካረፈበት በሰቆጣ ደብረ ገነት መድሃኒአለም በክብር አርፉዋል፡፡ ይህን ጀግንነታቸዉን በመገንዘብም የኢትዮጵያ መንግስት ከሞቱ ቡሃላ ሌተናል ጀኔራል በሚለዉ ማእረግ እንዲጠሩ አድርጓል፡፡ማእረጉም በኢትዮጵያ ቤተ መንግስት ለክብራቸዉ ሲባል ከንጉሱ በስተቀር የመጀመሪዉ እንደነበር አበዉ ይናገራሉ፡፡

................................................(ምንጭ ፣ የአገዉ ህዝብ ታሪክ በ Dr. Ayalew Sisay)
ነገደ አገው
------------ ከአለቃ ታዬ መፅሀፍ(1914 ዓ.ም የታተመ)
አገዎች ግን ለ3 ተከፍለው ቋንቋቸውም ስሩ አንድ ሲሆን በየክፍላቸውና በየአገራቸው ጥቂት ጥቂት ልዩነት ያለው ሆነ፤እነርሳቸውም በ3 አገር ስም ይጠራሉ፤የላስታ አገው፤የዳሞት አገውና የሐልሐል ቦጎስ አገው ተብለው ይጠራሉ፡፡ የሁሉም መሰረትና ምንጭ የላስታ አገው ነው፡፡
የላስታ አገዎች 7 ሆነው ዝሆንና ጎሽ አደን ብለው ሄዱ፤ከዚያ ሰው እንደሌለበት ፤ጠፍ እንደሆነ ተመልክተው የአገሪቱንም ደግነት አይተው በየዱሩ፡ በየዛፉ፡እጅግ ንብ የበዛበት ብዙ ማር የሚገኝበት አገር ነውና፡ ማርና፤የዱር እንሰሳት ስጋ አድነው እየበሉ 7 ወር አገሪቱን ደህና አድርገው ዞሩና መረመሩ፡፡ ከዚህ በኋላ ምሽቶቻቸውንና፤ ልጆቻቸውን፤ላማቸውን፤ፍየላቸውን፤ጓዛቸውን ሁሉ አምጥተው በዚያቸ አገር ተቀመጡባትና አቀኗት፡፡ ባላገሮችና ባላባቶችም ሆኑባት አገሩም አገው ምድር ተባለ፡፡ በ7ቱ አባቶች በየክፍሉ ሲዘረዘር 7 ቤት አገው ይባላል፡ በ7ቱ አባቶቻቸው ስም አገራቸው ሰይመው 7 ቤት አገው ተብለው በየአገራቸው በየክፍላቸው ይጠራሉ፡፡ የሐልሐል ቦጎስ አገዎች ግን በአንድ ዘመን በየአገሩ ርሃብ በሆነ ጊዜ እንዲሁ በላስታ አገው 7 ወንድማማች አገዎች ከነሚስቶቻቸው፤ ከነልጆቻቸው፤ 3 እህቶቻቸው ከነባሎቻቸው ተሰደው ሐልሐል ቦጎስ ገቡ፡በዚያም ዱሩን መንጥረው እባቡን ገድለው ቤት ስርተው አገር አቅንተው ተቀመጡ ይባላል፡፡ የላስታ አገዎች በዋግ የሚኖሩ ዋኖች እነርሱ ናቸውና በመጀመሪያ የያዙትን አገር(በቀዳማዊ ሚኒሊክ ዘመን ይለዋል) አልለቀቁም፤ እስከዛሬም አልተነቃነቁም፡፡
አዊና የፈረስ ትርኢት...
-------------------
(ተጓዡ ጋዜጠኛ ሔኖክ ስዩም ለዛሬ ደግሞ ወደ አዊ ዞን ተጉዞ በ1933 የተመሰረተው የአዊ የፈረሰኞች ማሕበር በየዓመቱ በአዊ ዞን የሚያካሄደውን የአዊን የፈረሰኞች ቀን አከባበር ያወጋናል...) አዊን እያለፍኩ ነው፡፡ ለምለሙን ምድር፤ ጥር እየተሸኘ አይደለም፡፡ አዊና ፈረስን ነጣጥሎ ማየት አይቻልም፡፡ አዊ ፈረስና ጥር ደግሞ ሶስትም አንድም ናቸው፡፡ ሩቅ ላላችሁ አዊ አማራ ክልል የሚገኝ አዊ የተባለ ብሔረሰብ መኖሪያ ነው፡፡ የጎጃም ምድር፤ ለሙ ሀገር አዊ፤ ፈረስ ለአዊ ሁለንተናው ነው፡፡ እርሻ ስራው ጉልበቱ በመሆኑ ይወደዋል፡፡ በክፉም ሆነ በደግ በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች መጓጓዣ ትራንስፖርቱ ፈረስ ነው፡፡ ለአዊ ሁሌም ያስፈልገዋል፡፡ ያለ ፈረስ አዊን ባናስበውስ፤ አዊ በደስታውም ቢሆን በዓሉን የሚያደምቀው በፈረስ ነው፡፡ ሰርጉ ጭምር በፈረስ ይዋባል፤ ሞቶ ወደ መቃብር ሲሸኝም ፈረስ መሸኛው ነው፡፡ የአዊ ፈረሶች በክብር የሚሸለሙ፣ ሁለመናቸው የሚስብ ከልጅነታቸው የሚገሩ ናቸው፡፡ የሚጋለቡበትን ሜዳ ሰንጥቄው እያለፍኩ ነው፡፡

መምጣት የምትሹ ከአዲስ አበባ በ435 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው እንጅባራ ከተማ ብላችሁ ኑ፤ እንጅባራ የአዊ መዲና ነው፡፡ አዊ በረጃጅም ተራሮቹ፣ በውብ ፏፏቴዎቹና ባልተነካው የአዊ የባህል እሴት የሚታወቅ ዞን ነው፡፡ አዊና ፈረስን ደጋግሜ ሳነሳባችሁ አትገረሙ፡፡ በ1933 ዓ.ም የተመሰረተው የአዊ ፈረሰኞች ማህበር 74 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ የአዊ ፈረሰኞች ማኅበር ጠላትን ከሃገር ለማስወጣት አንድነትን ለመፍጠር በሚል በአንድ የተደራጀ ነበር ያኔ….. ዛሬ ደግሞ በየዓመቱ የአዊን የፈረስ ጉግስ ይደግሳል፡፡

የአዊ ፈረሰኞች ማኅበር 22,275 አባላት ያሉት ሲሆን ይህ ማኀበር በየዓመቱ ዓመታዊ በዓል ያከብራል፡፡ ይህ በዓል የአዊ ፈረሰኞች ቀን ይባላል፡፡ በዚህ የባህል አከባበር ደንብ አመታዊው በዓል ከወረዳ ወደ ወረዳ እየተዘዋወረ የሚከበር ነው፡፡ አዊ ዞን አስር ወረዳዎች አሉት፡፡ አንድ ወረዳ በአስር አመት አንዴ የአዊ ፈረሰኞች ቀንን የማዘጋጀት እድል ይገጥመዋል፡፡ የአዘጋጅነት እድሉ በተራ የሚዞር ሲሆን አዘጋጁ ወረዳ ሰፊ ዝግጅት ያደርጋል፡፡ በዚህ የፈረሰኞች ቀን ከፈረስ ስፖርት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ባህላዊ ስፖርቶች ይካሄዳሉ፡፡ እነዚህ ባህላዊ የፈረስ ስፖርቶች በዋናነት ሶስት ናቸው፤ ከእነዚህ መካከል ጉግስና ሽርጥ ቀልብ ሳቢ ውድድሮች ናቸው፡፡

በውድድር መልኩ ከሚዘጋጁት ውድድሮች ባሻገር በፈረስ የሚደረጉት ያልተደራጁ ትርኢቶች ለሚመለከታቸው የተደራጁ መሳይ ማራኪና ሳቢ ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ወረዳ በዚህ አመታዊ የፈረስ ትርኢት ላይ አንድ አንድ ከብት ይዞ ይመጣል፤ በትንሹ በበዓሉ አስር ከብቶች ይታረዳሉ፡፡ የአዊ የፈረሰኞች ቀን በሚል በየዓመቱ የሚከበረው ይህ የፈረስ ትርኢት በወርሃ ጥር ካሉት በአንዱ እሁድ ቀን ይከበራል፤ መደበኛ ቀን የለውም፡፡ ወሩ ግን የግድ ጥር ዕለቱም እሁድ መሆን ይጠበቅበታል፡፡

ከዚህ ባሻገር ዓመታዊው በዓል መቼ እንደሚውል በማኅበሩ ይገለጻል፡፡ ለምሳሌ እንደ ዓመቱ ልዩ ክስተት ተቆጥሮ ያለፈው የ2004 ዓ.ም የአዊ ፈረሰኞች ቀን በዓል ጥር 20 ቀን 2004 ዓ.ም በደማቅ ዝግጅት ተከብሮ ነበር፡፡ በድምቀት እና እንግዳን በማሳተፍ ደረጃ የመጀመሪያ ነው የተባለለት የ2004 ዓ.ም የአዊ ፈረሰኞች ቀንን በዓል ያስተናገደችው ቲሊሊ ከተማ ነበረች፡፡ ቲሊሊ ስደርስ መልሼ ያንን ውብ ጊዜ አስታወስኩት::
ፋጥዝጊ!
--------
ፋጥዝጊ ሰቆጣ ሳድግ ቦርቄ ከደኩባቸዉ ቦታዎች አንዱ ነዉ፡፡ የሚገርም አስደማሚ ቦታ ነዉ ሰቆጣ አድጎ በመስቀለ ክርስቶስ በኩል ወለህን ድግርሽን አበሃንስን ሲቪሉን ጉድጉዳን አደጋን የማያውቅ የለም፡፡ ፍጥዝጊ ከሰቆጣ ወደ ሰሜን በኩል የሚገኝ በገደል የተከበበ ሜዳማ ቦታ ነዉ፡፡ በሰብል አብቃይነትም የታወቀ ነዉ፡፡ ከሜዳዉ ጫፍ በደቡብ በኩል ሰቆጣን ሙሉ ለሙሉ ማየት ያስችላል፡፡ በሰሜን በኩል ትልቅ ወንዝ የሚታይ ሲሆ ወንዙ ዳር በሰፊዉ ሌላ ጊዜ የማጫውታችሁ በድንጋያማ ክብ ወደላይ ከተመዘዘ ተራራ ላይ ያለች የምትታይ ጥንታዊ ቤተ ክርስቲያን ማየት ያስችላል፡፡ ስለልጅነቴና ስለጓደኞቼ ስላሳለፍነዉ ጣፍጭ ጊዜ ለሌላ ጊዜ ይቆየን፡፡ ዋናው ነጥቤ ሰቆጣ አየር ማረፊያ ነበራት! ትገረሙ ይሆናል ነገር ግን በደርግ ጊዜ የአየር ማረፊያ ነበራት፡፡ ካላመናችሁ ፍጥዝጊ ወጣ በለና ቅርፅን ሳይቀይር ተንጣሎ ይታያል፡፡ እንደዉም አየሮች ማረፍ ሲደብራቸዉ ፍጥዝጊ ላይ የእርዳታ ቁሳቁስ ከአየር ላይ ይጥላል፡፡ አስካሁንም ወደዚያ ሲያቀኑ ስቃጥላ ማግኘት የተለመደ ነዉ፡፡ ማወቅ ያልቻልኩት አየር ማረፊያውን ደርግ ለምን ሲጠቀምበት እንደነበር ነዉ፡፡ የምታውቁ ሹክ በሉን፡፡ ደርግ መቸም ሲርብህ አብልቶ ሲጠማህ አጥት ሲበርድህ አልብሶ ነበር የሚገድለዉ፡፡ የአሁኖቹ ከደርግ በመማር በብልጠት ገድለዉ ያፋልጋሉ! ዛሬ ሰቆጣ እንኳን አየር ተለቅ የሉ አውቶብሶች የማይገቡባት ሁናለች፡፡እድሜ ታግለን ለዚህ ላበቃነዉ የወንበዴ ስብስብ!!! ዛሬ ሰቆጣ ውሃ ለመጠጣት የሃይላድ መግዥ ያስፈልጋታል፡፡

ባጠቃላይ ዋግ በደርግና በኢሃዴግ ስትነፃፀር መብራት ስናይ በደርግ ጄኔሬተር አሁን 24 መብራት መሆኑ በጥሩ ጎኑ እሱም ታምራት ላይኔ ባያስገባዉ ዛሬም ጨለማ ውስጥ ልንሆን ይችላል፡፡ መንገድ ብናይ ያኔም የጠጠር መንገድ ዛሬም ጠጠር መንገድ፡፡ የዉሃ የምታውቁት ነዉ፡፡ እንግዲህ ሰቆጣ ከመብራትና ስልክ ውጭ ደርግ እንደተዋት ናት፡፡ እንደዉም በደርግ ወንዞቻችን አልደረቁም ነበር የከተማችን ውበት በለስ ወንዝ አልደረቀም ነበር፡፡ እነ ይልማ በአመት አንድጊዜ በጳጉሜ እየታጠባችሁ አታካብዱ አይለንም ነበር፡፡ ይልማ ያላወቀዉ በአመት አንድ ጊዜም ሆኑ ብዙ ጊዜ የምንታጠብበትን በለስን ስላሳጣችሁን መሰለኝ ጭሆታችን፡፡ ምን ታደርጉ የዋህና ዝም የሚል ህዝብ ስታገኙ ያለዉን አረጃችሁብን፡፡ በዘንድሮ ምርጫም ወንበር ለማሞቅ የምትፈለጉት ለውድድር መቅረባችሁን ለጥፋችሁ አየን፡፡ ጭራሽ ካሳ ጋር አብራችሁ ስትቀርቡ ተሳቀቅን!!! በተለይ ለተወካዮች ምክር ቤት ያቀረባችሃት በጣም ነዉ የምትወክለን እንኳን የህዝብ ችግር ልትናገር ህግ ለማፅደቅ እጅ የምታወጣም አይመስለኝ፡፡ ቁጭ እንዳለች አለች ወደፊትም መሆኗ ነዉ፡፡ ነብስ ያለዉ ለህዝብ የሚወግን ዋግ አይመረጥም አይፈለግም!!

አገሬ ሰቆጣ ዝምታን አበዛ
አገሬ ደሃና ዝምታን አበዛ
አገሬ ጋዝጊብላ ዝምታን አበዛ
አገሬ ዝቋላ ዝምታን አበዛ
አገሬ ሰሃላ ዝምታን አበዛ
አገሬ አበርገሌ ዝምታን አበዛ
እረ አገሬ ላስታ ዝምታን አበዛ
የተነሳ እንደሆነ ላይለቅ እንደዋዛ
ዝምታው ችግሩ ያለልክ በዛሳ፡፡
All the Above information is contributed by Lij Eyasu Ze Ethiopia
‪#‎Agaw‬ ‪#‎Bete‬

Saturday, July 18, 2015

ማንነቴ ማነው? የብሔር ማንነት አምባገነንነት


ማንነቴ ማነው? የብሔር ማንነት አምባገነንነት


በደርግም፣ በህወሃትም፣ በኢህአፓም፣ በኢዲህም፣ ….ተሰልፈው ‘ለህዝቤና ለሃገሬ የወደፊት መፃኢ እድል ይጠቅማል’ ተብለው በተሰለፉበትና ባመኑበት አላስፈላጊ መተላለቅ ሰላባ ለሆኑ ምስኪን የሃገሪትዋ ልጆች የሰላም እረፍት ይሁንላቸው። አሁን እኛ ያለንበትን ትግልም ሆነ የዘበናይ ህይወት ሳያዩ ቤተሰባቸውን በትነው በየገደሉና በየጎዳናው ቀርተዋልና።
ይህ አሁን በየመድረኩ የምንሰበከው ‘የብሔር ብሄረሰብ ብቻ ማንነት’ ፍልስምና ግን እነዚህ ሰማእታት ከታገሉለትና ከወደቁለት በተለየ አይን ያወጣ የመብት ረገጣነት እየተቀየረ ያለ ይመስለኛል። በተለይ በግል ከዚህ በፊት የማውቃቸው ቅን አሳቢዎች በዚህ ማህበራዊ መድረክ የሚያንፀባርቁት በብሄር ብሄረሰብ ሥም የማንነትን መብት ጭፍለቃ ሳነብ ስጋቴ እየናረ ነው። በዚህች ሃገር ብሔር ብሔረሰቦች መብታቸው የተሟላ አልነበረም። ማንነታቸውም (ባህላቸው፣ ቋንቋቸው …) ሙሉ በሙሉ በእኩልነት የተከበረና እኩል የመበልፀግ እድል አላገኘም፤ ይህ ማንነታቸው አልፎ አልፎም በሚያስተዳድራቸው አካል ሳይቀር መናናቁና መረሳቱ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ባህልቸው እንዲደበዝዝ ማድረጉ አይቀሬ ነው። አሁን የብሔር ብሔረሰቦች መብት በህግ ጭምር ተረጋገጠ። ከዚህ በላይ አልፎ ግን ኢትዮጵያ በነበራት ከሦስት ትውልዶች በላይ ጊዜ በፈጀ የጦርነት፣ የአገዛዝ፣ የረሃብ፣ የመስፋፋት፣ የስደት፣ የወረራ … ታሪኩዋ የተነሳ “የብሔር ማንነቴ ተደበላልቋልና የዚህ ታሪክ ማንነቴ ነው እኔን የሚገልፀኝ” የሚለውን ህዝብ ላይ ይህንን ያህል ማንነቱን የሚያንጓጥጥና ህልውናውን እስከመኖሩም የሚክድ ‘ኢትዮጵያዊ ማንነት የለም’ የሽብር ጦርነት መክፈት የነዛን ሰማእታት ደም እንደመምጠጥ ነው የሚቆጠረው፤ የተዋደቁት የራሳቸውን የብሔር ማንነት ለማስከበር እንጂ የውህድ ማንነትን ለመጨፍለቅ ነው ብዬ ስለማላምን ነው። የብሔራችሁን ማንነት የምታስከብሩት ወይንም የተከበረላችሁ የሚመስልላችሁ የግድ የኢትዮጵያ ታሪክ የፈጠረውን የውህድ ብሔር ማንነትን በማንጓጠጥ፣ በመፈረጅ፣ ሽብር በመንዛት … ብቻ ነው እንዴ?
እንነጋገር ከተባለ ከፍረጃ ሳጥን ወጥተን ፊት ለፊት እንነጋገር። እኔ አሁን የተዋቀሩት የማንነት የፖለቲካ ቡድኖች መብት ባከብርም አባል አይደለሁም። በአማርኛ አፌን ስለፈታሁና ኦርቶዶክስ ክርስትናን ከ40 ቀን እድሜዬ ጀምሮ ስለተከተልኩ ‘አማራ ነህ’ ብሎ ማንነቴን የሚወስን የዘመኑ ዘመነኛ መሰል አምባገነንነትንም አልቀበልም። ስንትና ስንት ብሄረሰብንና አፍ መፍቻ ቋንቋን በአንድ ክልል ከልሎ ‘ያንተ ብሄርና አፍ መፍቻ ቋንቋህ እኔ አውቄልሃለሁና በዚህ ብሄር ተጠራ: በዚህ ቋንቋ ተዳኝ: በዚህ ቋምቋም ተማር፤ ምክንያቱም የታገልንልህ እና የሞትንልህ መብትህ ነውና’ የሚል የአሻንጉሊት ጨዋታ ለሚነግረኝም መሳቅ አይሆንልኝም።
ይህንን ውህድ ማንነት ቀደም ሲል ከመዐህድ፣ ከነፍጠኛ፣ ከትምክህተኛ፣ … አሁን ደግሞ ከሰማያዊ፣ ከአንድነት … ጋር በግድ በመፈረጅ የሚከበር የብሔር ማንነት ሊገባኝ አይችልም። በቃ ከነጠላ ብሔር ብሔረሰብ እኩል ውህድ የብሔር ማንነትም የዚህች ሃገር አንዱ የውርስ ማንነት ነው፤ እኩል የጠራ ማንነት ነው፤ ለነጠላ ብሄር ብሄረሰብ ማንነቶች ጌጣቸው እንጂ ስጋታቸው አይደለም፤ የነጠላ ብሄር ብሄረሰብ ማንነት የጣት ቀለበታቸው እንጂ ፈንጂያቸው አይደለም። ይህ ማንነት እራሱን ኢትዮጵያዊ ብሎ መሰየሙ ከላይ ያነሳሁዋቸው እና ወደታችም አሁን በማነሳቸው ወደንም ይሁን ተገደን ያለፍንባቸው ብሔራዊ ብቻ ሳይሆን አለማቀፋዊ የኢትዮጵያዊነት ጫናዎች መገልጫ በመሆኑ እንጂ ምንም ሌላ የሚያስፈርጅ አመክንዮ አታገኙም። እኔ በአማርኛ አፌን እንድፈታ፣ ከሃገሪቱዋ ሁለትና ሶስት ብሔር ትዳር እንድወለድ፣ እዚህ ጫፍ ወደዛ ጫፍ እንድንቀሳቀስና ይህንን ውህድ ማንነት እንድላበስ የምትሉዋቸውና የፈረጃችሗቸው ቡድኖች ያደረጉት አስተዋይፆ ኢምንት ነው። እናንተም የመጀመሪያ ማንነታችሁ ነጠላው በሔራችሁ እንደሆነላችሁ ሁሉ ማንነቴ መሰረቱ ወደዳችሁም ጠላችሁም የብዙ ዘመን የኢትዮጵያ ያለፈ ታሪክ ነው። ወደውም ይሁን ተገደው ቅድመ አያቶቼ የዛ ታሪክ ዋና ተሳታፊ በመሆናቸው ማንነቴን ፈጥረዋልና ለውህድ ማንነቴ ስያሜ ‘ኢትዮጵያዊ’ ማለቴ ልክ ነው፤ ከብሄር ማንነት እኩል እውቅና፣ እኩል ቦታ እና እኩል ክብር እኩል የማንነት መታወቂያ ካርድ ሊሰጠው ግድ ይላል፤ ይህ ውህድ ማንነት ያለቋንቋው ሊዳኝም ሆነ ሊማር አይገባውምም፤ ከሶስት ትውልድ በፊት ለተፈፀመ ጥፋትም ቂም መመለሻ አድርጎ ማንነቴን ማቅረብ የዘር ማጠፋት ሙከራ ነው።
የኢትዮጵያ ታሪክ ደግሞ አንድ ገዢ ወይንም አንድ ብሔር ወይንም ኢትዮጵያኖች ብቻ የፈጠሩት አይደለም። ከሁሉም ብሔሮች አሻራ በላይ አለማቀፋዊ የዘመናት የተፅዕኖ በትርም አለበት። ኦሮሞዎች ግዛታቸውን ለማስፋፋት ወደሰሜን እየተመሙ ባይማርኩና ጃላ (ወዳጅ ወይንም ኦሮሞ) ባያደርጉ፣ የግራኝ አገዛዝ እስልምናን ወደሰሜን በኃይል ባያስፋፋ፣ ድርቅ ህዝብን ከአንድ ጎጥ ወደሌላ ባያንቀሳቅስ፣ የአውሮፓ መንግስታት የሶስትዮሽ ስምምነት አድርገው የአፍሪካን ቀንድ ባይቀራመቱ ኖሮ … የእኔ ውህድና ኢትዮጵያዊ ማንነት ላይፈጠር ይችል ነበር። ቅድሚያ ማንነቴም እንደናንተው ብሄሬ ይሆንና ኢትዮጵያዊነት የዜግነት ማንነቴም [ብቻ] በሆነ ነበር።
ከላይ በገለፅኳቸው በቂ ምክንያቶች የእኔ ማንነቴም ዜግነቴም በቃ ኢትዮጵያዊ ነው። ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር ካንገፈገፋችሁ ያንን ችግር መነጋገር አግባብም ልክም ነው። የብዙዎችንም የኢትዮጵያዊ ዜግነት መስፈርት ጥያቄ እረዳለሁ፤ በመነጋገር የሚፈታም ይመስለኛል። ኢትዮጵያዊ የሚባል ማንነትና ታሪክ ግን ለመሰረዝ መሞከር እራስን ከማጥፋት ጋር ይመሳሰልብኛል።
ይህን ውህድ ኢትዮጵያዊ ማንነትን ስትክድና ስታንጓጥጥ የራስህንም የብሔር ማንነት እየካድክና እያንጓጠጥክ  መሆኑን ቆም ብሎ ማሰቡ ብልህነት መሰለኝ። ውህድ ማንነቴ እኮ ያንተ ማንነት አንድ አካል ነው። ኢትዮጵያዊ ማንነት ያሰኘኝም እኮ ውህዱ የኢትዮጵያ ታሪክ ስለወለደኝ ነው። ኦሮሞና አማራን፣ አማራና ትግሬን …  ያጋባውና ልጆች አብረው እንዲያፈሩ ያደረጋቸው “የአማራው አምባገነንነት” ብቻ አይደለም፤ ድርቁም፣ ወረራውም፣ የኦሮሞው አምባገነንነትም፣ የኢስላም መሪ አምባገነንነትም፣ የክርስትና መሪ አምባገነንነትም (በዘመኑ የነበሩ አንዳንድ የኃይማኖቶቹ መሪዎች እንጂ ኃይማኖቶቹ ሰላምና እኩልነትን ያዘሉ ነበሩና) … ሁሉም የድርሻቸውን አበርክተው ነው። በዚህ የኢትዮጵያ ታሪክ አንዱን ብሔር ከሌላው ማግነን፣ አንዱን ማንኳሰስ የብሔረሰቦቹን ታሪክና ባህል ማናናቅ እንጂ ማክበር አይመስለኝም፤ ማን ከማን ያንስና። ታሪክ ሰሪ እንጂ የሌላውን ታሪክ ነጋሪ ብቻ ሆኖ ለዘመናት ያሳለፈ ብሄር ባለቤት ነን እንዴ? የድርቅ ስደት ብሄር ለይቶ ነበር እንዴ? አውሮፓውያኖችና ግብፆች የወረሩን ብሄር ለይተው ነው እንዴ? ይህንን ስል ግን ብሄሮች ባለፈው ታሪካቸው ሙሉ መብት ነበራቸው ብዬ እየተከራከርኩ አይደለም። እንኳን ባለፈው አሁንም ለሙሉ መብት ብዙ መስራት ይጠበቅብናልና፤ ከያንዳንዱ ብሄር በተፅእኖም ሆነ ባለማወቅ ተደብቀው ያሉና ለአለም የሚጠቅሙ የብሄር ብሄረሰቦች እሤት እንዳለን አውቃለሁና።
ምናልባትም የአውሮፓዎቹ የሶስትዮሽ የቅርምት ስምምነት ወይንም የግፆቹ ወረራ ተሳክቶ ቢሆን ኖሮ እንኳን የእኔ ውህድ ማንነት ሊፈጠር ቀርቶ የኦሮሞና የአማራው ብሄር እራሱ በተለያዩ ሁለትና ሶስት የተበጣጠሱ ሃገራት በተገኙ ነበር። አሁን በህብረትና ባንድ ሃገር የሚኖረው ብዙኃን ኦሮሞ የተገኘው በአማራ መስዋእትነትና በሚኒሊክ ጀግንነት ብቻ ነው እንዴ? ያኔ ኦሮሞው ለአንድነቱ አልተዋደቀም እንዴ? ያን ጊዜ የኦሮሞ ፈረሶች ባማረ መስካቸው ላይ ተኝተው የኦሮሞው የሾለ ጦር ከራስጌ ተገትሮ ነበር እንዴ? ሁሉም የደከመለት የኢትዮጵያ ታሪክ እኮ ነው። የድሎት ኑሮ በሌለው የተጋድሎ ታሪክ እንኳን: ብሄሮችን አስተሳስሮ እኔን እኔ ያደረገኝ ይህ የኢትዮጵያ ታሪክ እኮ ነው። እና ቅድሚያ ማንነቴ ስያሜው ‘ኢትዮጵያዊ’ ቢሆን ምን ያናድዳል፤ ምንስ ያስፍራል? የእኔ ውህድ ማንነቴ ‘ኢትዮጵያዊ’ ቢባል የብሄር ‘ማንነት ብቻ’ ላላቸው ደስታ እንጂ ስጋት ይሆናል እንዴ? ሁለት ሰዎች ተጋብተው ከጋራ ሥጋቸው ተቆርሶ ልጅ ሲወልዱ በህግም ሆነ በስብእና መስፈርት ያስደስታል እንጂ ያናድዳል እንዴ? የሁለቱም ልጅ እንጂ አንዱን ክደህ የሌላው ብቻ ሁን ያስብላል እንዴ? የጋብቻውን መከባበርና መናናቅ የልጁን የሁለትዮሽነት ያስቀይራል እንዴ? ምናልባት አባት እናቱ ላይ በደል ሊፈፅም ቢችል ልጁ የበደሉ ቂም መመለሻነት ‘የአባትህ አይደለህም’ ወይንም ‘የእናትህ አይደለህም’ ወደሚል ድምዳሜ ያስኬዳል እንዴ? ወደውም ይሁን ተገደው የፈፀሙት ግንኙነት አንዴ ልጁን አስገኝቶዋልና እንደገና ወደ ሆድ አይመልሱት፤ ልጁ እራሱን ሆኖ ከመኖር ሌላ በአባትና በናቱ የሆነውን እንዳልሆነ ማድረግ ይችላል እንዴ?
አብዛኞቻችን ከኢትዮጵያዊ ዜግነት በተጨማሪ የዚህ ኢትዮጵያዊ ማንነትም ባለቤት ነን ። ‘እኔ የዚህ ኢትዮጵያዊ ማንነት ባለቤት አይደለሁም ፤ ማን ነቴ ብሄሬ ብቻ ነው፤ ዜግነቴን ግን ገና ከሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ጋር ተደራድሬ የምወስነው ነው’ የሚልም መብቱ ነው፤ እሱንቱን እስከገለፀለት ድረስ እኔ ለእርሱ አዋቂ አይደለሁምና ደስ ይለኛል ። ግን የእርሱን የብሄር ማንነት በተወሰነ መልኩ የምጋራ የኢትዮጵያዊ ማንነቴ የሚበልጥብኝ እኔንም በእኔነቴ ማወቅ ግድ ይለዋል። ዜግነትን ሲደራደር እኔንም ሊያስታውስ ይገባዋል። ለነገሩ እኔ የእርሱን ማንነት በተወሰነ መልኩ እየተጋራሁት ማንነቴን ካናናቀ እንዴት ነው ከማንነቱ ጋር ትንሽም የጋርዮሽ ከሌላቸው ሌሎች ብሔር ብሄረሰቦች ጋር ‘ኢትዮጵያዊነትን በመከባበር እደራደራለሁ’ የሚል ሞራል እሚኖረው? ይህ ወሳኝ እራስን መጠየቂያና ማንቂያ ደወል ይመስለኛል። ‘ለብሔር መብት ሰምአት ሆኑልን ፤ እኛም የእነርሱን ራእይ እናስፈፅማለን ’ የሚሉቱ ደጋግመው ሊያስቡበት ይገባል ። ምክንያቱም ይህ ‘የብሄር ማንነት ብቻ’ አምባገነናዊ አስተሳሰብ ዲሞክራሲያዊ ያልሆነ መሆኑን በዚህ መረዳት ይቻላልና፤ ውህዱን የኢትዮጵያ ታሪክ (በመቶም ይሁን በሺ ዓመታት ይሰላ) የፈጠረውን የብሔር ብሔረሰቦች የአብራክ ክፋይ ውህድ ማንነት በዚህና በዚያ ፈርጆ፣ ገነጣጥሎ፣ ‘ማንነትህን እኔ አውቄልሃለሁ’ ብሎ፣ … የተሟላ የህዝቦችንም ሆነ የብሔር ብሔረሰቦችን መብት አስከበርኩ ማለት ወይንም ማስከበር በኢትዮጵያ ዘበት ነውና።
የብሔር ብሔረሰቦች መብት ተከብሯል ፤ የበለጠ እየተከበረም ነው፤ መከበርም አለበት (አስፈላጊ ከሆነም እስከመገንጠልም ይከበር። ለትውልዱ ጥሩ እንዳል ሆነ ባውቅም ድሮ እንጂ አሁን መገንጠልን አልፈራም። ጉዳቱም ሆነ ጥቅሙ እኔ ላይ ብቻ አይዘንም፤ ህዝብ እስካመነበት ድረስ ምን አገባኝ። በዚህ ሁለት አስርት ዓመታት የተረዳሁት ነገር ቢኖር መገንጠልን የምንቃወምበት ስጋት የባሰ መገንጠልን እየገፋፋ መሆኑን ነው)። የብሔር ብሔረሰቦች ክብሩን የበለጠ ምሉእ የሚያደርገው ግን እነዚህ ብሄር ብሔረሰቦች ከደም ከአጥንታቸው አዋጥተው በኢትዮጵታዊ ታሪክ አምጠው የወለዱትን ውህድ የብሄር ማንነት ክብር እና ቦታ ሲሰጡት ነው። ሰማእታቶች የተጋደሉትም ለዚህ ምሉእ የሃገሪቱዋ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ማንነት እንጂ አሁን እዚህ ማህበራዊ መድረክ ላይ በዚህና በዚያ በሚቀነቀኑ ፅንፍና ‘እኔ አውቅልሃለሁ’ የተምታታ ‘የብሔር ማንነት ብቻ’ አጥርነት ለማነቅና አምባገነን ለመሆን አይመስለኝም ። ከሆነም የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች መከራችን ገና አልተቋጨም ማለት ነው።
የተነሳሁበት ነገረ-አርእስት ገድቦኝ እንጂ የብሔር ማንነታቸውን ከኢትዮጵያዊነት ያስቀደሙትን ወገኖቻችንን ማንነት የሚያብጠለጥሉት ተመሳሳይ አምባገነናዊ እሳቤ ለሃገራችን ሃገራዊ ህልውና ጠንቅ የሚሆን ይመስለኛል። ኢትዮጵያ ለዘለአለም የምትኖረው ለሁላችንም ማንነት የተሟላ የማንነት ልብስ ተከባብረን ስንላበስላት ነው፤ ለህዝቦቿ አምባገነናዊ ማንነት ጭኖ ዲሞክራሲና ኢትዮጵያ ብሎ ማንባት የአዞውን እንዳይሆንብን ያሰጋልና።
*********

አጼ ዮሐንስ እና አማራ ላይ የፈጸመው ክህደት

አጼ ዮሐንስ እና አማራ ላይ የፈጸመው ክህደት

በጎንደር ቤተ አማራ ሳምንት ስለ አጼ ዮሐንስ ስናወራ የሚበዛው ነገር ከጎንደር ጋር ግንኙነት ያለው መሆኑን በማጤን ነው፡፡ የአማራ ልጆች ከእንግዲህ የሚፈሩት ሁለት ነገር ብቻ ነው--ውሸት እና እግዜርን፡፡ እስካሁን በይሉኝታ እና አብሮ ለመኖር በሚል ብሂል በእኛ ላይ የተካሄዱ ክህደቶችን ሳይቀር በቸልታ ስናልፋቸው ኖረናል፡፡ በተቃራኒው ሁለቱም የኦሮሞና የትግሬ ወራሪዎች የልጅ ልጆች የእኛ የሆነውን ሁሉ ከማጥላላትና ከመርገም ወደኋላ ብለው አያውቁም፡፡ ስለዚህ የአማራ ልጆች ይሉኝታችን ስለተሰበረ በቀጥታ መናገር ጀምረናል፡፡ አካፋን አካፋ ካላሉት የወርቅ ማንኪያ ነኝ ይላል በሚል መርህ እውነትን እና ውሸትን ያለ አንዳች ይሉኝታ እንገልጻለን፡፡ ስለዚህም የዚህን ንጉስ ስራ እና አማራ ላይ የተፈጸመውን ክህደት በእውነት ላይ ብቻ ተመስርተን እናብራራለን፡፡

በብዙ መለኪያዎች አጼ ዮሐንስ ከሀዲ ነው፡፡ በሀገር ክህደት ወንጀል መሰቀል የሚገባው ወንበዴ ነበር፡፡ ከዘመነ መሳፍንት ማብቃት ወዲህ ይህ ንጉስ በአማራ ላይ ያደረሰውን በደል ማንም አላደረሰውም--በዚህ ዘመን በወያኔ የበለጠ ከመደረጉ በቀር፡፡ ከአነሳሱ እስካወዳደቁ የአማራ ጠላት ሆኖ ነው የኖረው፡፡ እኔ ይህን ንጉስ ብዙ ጊዜ በይሉኝታ ስራራለት እና ስከራከርለት ነበር፡፡ በቤተ አማራ ጉዳይ ከተሰማራሁ ወዲህ ግን እውነትን በአግባቡ መመርመር በመጀመሬ ድሮ የነበረኝን ግምት እኔ ራሴ ታዝቤውአለሁ፡፡ በፍጹም ስህተት ነበርኩ፡፡ በአማራ ላይ ተነግሮ የማያልቅ በደል የሰራ ሰው ነበር፡፡

በመጀመሪያ አጼ ቴዎድሮስን አሳልፎ እንደይሁዳ ሸጠው፡፡ በጠብመንጃና በመጋረጃ እንዲሁም በመነጽር ነው የሸጠው፡፡ የንጉሱን ልጅ ለምን ትወስዳላችሁ እኔ ላሳድገው እንኳ አላለም፡፡ የድሮ ነገስታት ግን የተሸናፊዎችን ቤተሰቦች ራሳቸው ነበር የሚንከባከቧቸው፡፡ እሱ ግን በምንግዴሸነት የንጉስ ሚስት (እቴጌ) እና ልኡል አልጋ ወራሽ ልጅ እንደከብት በጠላት ተነድተው ሲሄዱ ዝም አለ፡፡ በዚህም ከአማራ ጋር አንዳች ግንኙነት እንደሌለው አስመሰከረ፡፡ የአጼ ቴዎድሮስ ልጅና ሚስት በውጭ አገር ሰው ሲጋዙ አጨብጭቦ ሸኘ፡፡ ለዚህም ውለታው አማራን የሚወጋበት መሳሪያ ከእንግሊዞች ተቀበለ፡፡ በጊዜው የተጻፈው የሄንሪ ብላንክ መጽሀፍ እንደሚያትተው እንግሊዞች አጼ ዮሀንስን በመጠቀም ጸረ አማራ ስራ ነው የሰሩት፡፡ በጽሁፉም ቴዎድሮስን በአማራነቱ ብዙ ቦታ ላይ ሰድቦታል፡፡ ወሎና ሸዋንም ሊያነሳሱበት ሞክረው ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡
ከአጼ ተክለ ጊዮርጊስ ጋር ተዋግቶ ንጉሱን ሲያሸንፍ ከክርስቲያን ንጉስ የማይጠበቅ የአረመኔ ተግባር ፈጸመበት፡፡ ከማረከው በኋላ በጭካኔ ሁለቱን አይኖቹን መንቅሮ አውጥቶ ጣላቸው፡፡ ንጉስን ያህል ነገር እንደዛ ማድረግ ታይቶ አይታወቅም፡፡ ያን ያደረገውም ንጉሱ አገው አማራ ስለሆነ እና በአገው አማራ ላይ ከፍተኛ ጥላቻ ስለነበረው ነው፡፡ የሚገርመው የንጉሱ ልጅ የእሱ ሚስት መሆንዋ ነው፡፡ እንዴት አይነት የወረደ ሰብእና እንደሆነ እንግዲህ ገምቱት፡፡

ወሎ ላይ የሀይማኖት ጦርነት በማድረግ ሙስሊሞችን እጅ እና እግራቸውን በመቁረጥ አጠፋ፡፡ ብዙዎችም አገር ጥለው ተሰደዱ፡፡ ወሎን አጠፋት፡፡ ጎጃምን ገና ለገና ከንጉሱ እምነት የለተየ ቀኖና ይቀበላል በሚል ዘር አጠፋ፡፡ በራሱ ቃልም “ክርስቲያኑ አገር ጎጃምን አጠፋሁት” አለ፡፡ ዛሬ እሱ እጅና እግራቸውን የቆረጣቸው የጎጃም አካባቢዎች አንድ እጁ ነሴ፤ ሁለት እጁን ነሴ እየተባሉ ጠራሉ፡፡ እጃቸውን ስለነሳቸው ማለት ነው፡፡ ይህ እንግዲህ በሀይማኖት ሰበብ አማራ ላይ ያደረሰው ጥፋት ነው፡፡

የሸዋን ንጉስ ምኒልክን እና የጎጃምን ንጉስ ነገር ሰርቶ በተንኮል አጣልቶ አዋጋቸው፡፡ የተንኮሉ ስሌትም ሁለቱም ሲሸነፉ ደካማ አማራን እንደፈለገ ለመርገጥ ነበር፡፡ ይሁን እና እርስ በእርስ የተዋጉት የአማራ ጦረኞች አጼ ዮሀንስን በመተው እርስ በእርሳቸው አንድ ሆኑ፡፡ በዛ ጊዜ ጎጃም እና ሸዋ በመተባበራቸው አማራ ከባሰ ጥፋት ዳነ፡፡

ለእንግዝ ቅጥረኛ በመሆን የሱዳንን የነጻት ተዋጊዎችን በመውጋት ጎንደር ላይ ይህ ቀረው የማይባል ጉዳት እንዲደርስ አደረገ፡፡ የእሱን ወረራ በመቃወም ሱዳኖች ጎንደርን ወረሩ፤ አወደሙ፤ ህዝቡን ጨረሱ፡፡ የእርሱ መዘዝ ጎንደርን አጠፍቶ ፍርስራሽ ብቻ አደረጋት፡፡ በጣም የሚገርመው በመጀመሪያው ዙሩ ጦርነት ጎንደር የጠፋቸው ለከተማዋ እና ለጠቅላላዋ ጎንደር አንድም ጠባቂ ሰው ስላላስቀመጠላት ነው፡፡ ይህም ግዴለሽነቱን ያሳያል፡፡ አንዳንዶች ለጎንደር ብሎ ተዋጋ የሚሉ አሉ፡፡ ይህ ውሸት ነው፡፡ ለጎንደር ብሎ ተዋጋ የሚባለው ደርቡሽ አሻፈረን ብሎ ጎንደርን ቢወር እና እርሱን ለማስለቀቅ ቢዋጋ ነበር፡፡ ነገር ግን ድርቡሾች ጎንደርን ሳይነኳት የራሳቸው አገር ሄዶ ነው የገጠማቸው፡፡ ያን ያደረገውም እንግሊዝን ለማስደሰት ነው፡፡ እውነታው ለጎንደር ተዋጋ ሳይሆን መባል ያለበት እንደኢትዮጵያዊ ንጉስ ለሚያስበው ሰው እንኳ ውርደት ነው ያመጣው፡፡ በሎሌነቱ እና በሞኝነቱ በጫረው ጦርነት ኢትዮጵያ ናት የተዋረደቸው፡፡ ሱዳኖች አንገቱን ቆርጠው ሆያ ሆየ ሲጫወቱበት የኢትዮጵያ ክብር ነው የወደቀው፡፡
ታሪክ ራሱን ይደግማል እንዲሉ ዛሬ ወያኔ የዚህን ንጉስ ስራ ነው እየሰራ ያለው፡፡ ንጉሱ ክርስትና ላይ ጫና አሳድሯል፤ ወያኔም እንደዛው፡፡ ንጉሱ እስልምና ላይ ጦርነት አውጇል፤ ወያኔም እንደዛው፡፡ ንጉሱ ሸዋና ጎጃም ብሎ በሴራ ከፋፍሎ እንዳዋጋው ሁሉ ዛሬ ወያኔ አማራን በብዙ ነገር ይከፋፍለዋል፤ ያጠፋዋል፡፡ ንጉሱ ጎጃምን አጥፍቷል፤ ወያኔም እንደዛው---የቤኒሻንጉል እልቂትና መፈናቀል፤ የጉራፈርዳ እልቂት እና መፈናቀል፤ በ1980ቹ አጋማሽ የተከሰተ ወረርሽኝ ያለ ህክምና ያጠፋው ህዝብ፤ እና አሁን የሚሰማው የዘር ማጥፋት ሂደት፡፡ ወሎን በሙስሊምነቱ ከማጥቃት በተጨማሪ ግዛቶቹን ነጥቆ መውሰዱ የወያኔን ዮሐንሳዊ የተግባር ልጅነት ያመለክታል፡፡ ንጉሱ ለእንግሊዝ በታዛዥነት ሱዳኖችን እንደወጋው ወያኔም ከሶማልያ ጋር በአሜሪካ ተቀጥሮ ይዋጋል፡፡ የንጉሱን ድርጊት ለመበቀል ጎንደር ላይ ድርቡሽ ወረራና ጭፍጨፋ እንዳደረገው ሁሉ በሶማልያ መወረር የተቆጣው እስላምም ባፈው የወገኖቻችንን አንገት በመቀንጠስ ጥላቻውን ያሳየን መሆኑ የታሪክ መደገምን ያመለክታል፡፡ ገናም ለወደፊቱ ብዙ መዘዘ አለ፡፡ ንጉሱ በነገስታቱ ላይ ያደረገውን አይነት ጭካኔ ወያኔም ይደገመዋል---ለምሳሌ የፕሮፍ አስራት የጭካኔ አገዳደል፤ በልዩ ልዩ ቦታ የተጨፈጨፈው አማራ፤ በእስር ቤቶች የሚደረገው ዘግናኝ ስቃይ፤ እና በአደባይ የሚፈጸመው ግድያ የንጉሱን የግብር አባትነት የሚደግም ነው፡፡

ይህ ሁሉ የሚያመለክተው ታሪክ ራሱን የሚደግም መሆኑን እና የንጉሱን ክርስቲያንነት እና አሁንም ከዛው የበቀሉትን ወያኔዎች ክርስትና የልብ ሳይሆን የይስሙላ መሆንን ነው፡፡ ሀይማኖት ያለው ሰው መቸም ያንን ያህል የአረመኔ ስራ ይሰራል ብሎ ማሰብ ይከብዳል፡፡ ንጉሱም ወያኔን የሚከተለው ጄሌም የስም እንጅ የተግባር ሀይማኖተኞች እንዳልሆኑ ያሳያል፡፡


መለክ ሐራ ከቤተ አማራ
ጎንደር ቤተ አማራ

መላው የእስልምና ዕምነት ተከታዮች፦ ዒድ ሙባረክ! – ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

መላው የእስልምና ዕምነት ተከታዮች፦ ዒድ ሙባረክ! – ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

ለ፴(ሰላሣ) ቀናት በፆም እና በፀሎት ተወስናችሁ፣ ፈጣሪያችንን ስትለማመኑ የከረማችሁ የእስልምና ዕምነት ተከታይ ወገኖቻችን፦ ኢድ ሙባረክ!
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት
moreshበመሠረቱ የረመዳን የፆም ወር በረከትን እና መተዛዘንን ይዞ እንደሚመጣ የሚታመንበት ወቅት ነው። ሙስሊሞች በዚህ ወቅት ራሣቸውን በፆም እና በፀሎት ወስነው፣ ፈጣሪያቸውን ከመለመን ባሻገር ለድሆች ሠደቃ (ምፅዋት) በመለገስ፣ ለሌሎች ሰዎች ውለታ በመዋል፣ ለተራቡ በማብላት፣ ለታረዙ በማልበስ፣ የተጣሉትን በማስታረቅ፣ ሌሎችንም በጎ ተግባሮች በማከናወን ያሣልፉታል። ሆኖም ያለፉት ፳፬(ሃያ አራት) ዓመቶች ለኢትዮጵያውያን የእስልምና ዕምነት ተከታዮች ታላቅ የሠቆቃ እና የሽብር ዓመታት ሆነው ዘልቀዋል። ገና ከጥንስሱ «በከፋፍለህ ግዛው» መሠሪ የአገዛዝ ዘዴ ኢትዮጵያውያንን ለማጥፋት ቆርጦ የተነሣው የትግሬ-ወያኔ፣ ኃይማኖትን ለኢትዮጵያውያን የመፋጃ አጀንዳ ለማድረግ ያልፈነቀለው ድንጋይ፣ ያልማሰው ጉድጓድ የለም። ጥረቱ እንዳሰበው ባይሣካለትም፣ አንዳንድ የታሪክ ጠባሣዎችን ትቶ ማለፉ አልቀረም። ይህ የትግሬ-ወያኔዎች የአገዛዝ አቅጣጫ የባንዳ ወላጆቻቸው ጌቶች ከነበሩት ከፋሽስት ጣሊያኖች የተቀዳ ዘዬ ነው።
ባለፉት ጥቂት ዓመታት የእስልምና ዕምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን በጀመሩት «ድምፃችን ይሰማ» በተሰኘው ሰላማዊ የመብት ማስከበር ጥያቄ የተደናገጠው የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ፣ አያሌ የዕምነቱን ተከታዮች ለእሥር ሲዳርግ ጥቂቶችንም በግፍ ገድሏል።  ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በኢትዮጵያውያን የእስልምና ዕምነት ተከታዮች ላይ በትግሬ-ወያኔ አገዛዝ የሚፈፀመውን የጅምላ እሥር እና አረመኔያዊ ጭፍጨፋ በከፍተኛ ሁኔታ ያወግዛል።
በዚህ አጋጣሚ በአስቸጋሪ ሁኔታ በእሥር ቤት ውስጥ ሆነው እንደዕምነታቸው ሥርዓት የኢድን በዓል ለማክበር ያልቻሉትን የእስልምና ዕምነት ተከታዮች ሁላችንም በያለንበት እንድናስባቸው አደራ እንላለን።

ኢድ ሙባረክ!
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

ዐማራን ምን ነካው!

ዐማራን ምን ነካው

ዐማራን ምን ነካው ሲበዛ ጠላቱ ፣
ዘራፍ እምቢ ብሎ አለመነሳቱ ፤
ምን ነካህ ወገኔ እስኪ ተጠየቅ ፣
ፍራት ነው ትዕግስት ቁርጡን እንወቅ፤
አስተዋዩ ዐማራ የጀግኖቹ ዘር ፣
ለጠላት እጅ አይሰጥ የማይበገር ፤
ሲዋደቅ የኖረው ለዳር ለድንበሩ ፣
ቁርኝቱ ታላቅ ለኢትዮጵያ አገሩ ፣
ለጥቅም አይሸጥ ነፃነቱ ክብሩ ።
መሬቱን ሲቀሙት ከጎንደር ከወሎ ፣
ምንም እንዳልሆነ ፀጥ ረጭ ብሎ ፤
ደግሞ ይባስ ብሎ ዐማራ ተሣዶ ፣
ለዘር ፖለቲካው አረጉት ማገዶ ፤
ወልቃይትም ለቅሶ : ጠገዴም ዋያታ ፣
ከተማ ገጠሩ : በርከቶ ጫጫታ ፣
ሲረግፍ እንደቅጠል ዐማራ ሲመታ ።

ነፈሰጡሯ ታርዳ : ሽሉ ሲጋደም ፣
በደኖ : አርባጉጉ ፤ አሰቦት ገዳም ፤
ትልቅ ትንሽ አይል ለሕፃን አይራራ ፣
የዐማራውን ጨቅላ ሲመትሩት በካራ ፣
ገደል ሲጨምሩት ከነነፍሱ ዐማራ ፣
በአሶሳ : በወተር : ብዙ ግፍ ሲሰራ ።
ከእንስሳ ባነሰ ሲያርዱት ሲገሉት ፣
ከማሳው : ከቀየው ሲያፈናቅሉት ፣
ሀብት : ንብረት ዘርፈው ጥሪት ሲያሳጡት ፣
በአባይ አንደበት ስሙን ሲያጠፉት ፣
“ጨቋኝ ነው ጡት ቆራጭ” ብለው ሲያስጠሉት ።
እስከመቸ ይሆን ይሄ ወይኔ ወይኔ!
ዕቅዱን በተግባር ሲያሳካ ወያኔ ፣
ገዳማት ሲፈርሱ እንዳይሄድ ምናኔ ።
ዐማራን ምን ነካው ? ዐማራ ምን ሆነ ?
ለስንቱ እንደማይተርፍ በራሱ ጨከነ!
ፍራት ነው እንዳልል የሌለ ባባቱ ፣
ትዕግስት እንዳይባል ሲያስወጡት ከቤቱ ፣
ገደል ሲጨምሩት ሲያርዱት በሱነቱ ፣
ሁሌ እንዳለቀሰ በዚህ መሰንበቱ ፣
አልገባኝም ጭራሽ የዐማራ ስሌቱ?
የገጠመን ጠላት ይሉኝታ ቢስ ሆኖ ፣
ከምድር እንድንጠፋ አቅዶ ወስኖ ፤
ጠላት እያስነሣ በቆላ በደጋ ፣
ሁሌ ሲያሳድደን የዘረኛ መንጋ ፤
ጎጠኛ ወያኔ ባልተሞረደ አፉ ፣
“ዐማራ ጠላት ነው” እያሉ ሲፅፉ ፣
መቻል ደግ ነወይ ከልክ እያለፉ ?
ወያኔ ላይገደው የዐማራ ሥቃይ ፣
በትዕግስት ማለፉ መልስ ይሆናል ወይ?
ከእንግዲህ ይበቃል ተነሣ ወገኔ ፣
ራስህን አድን ከጨካኝ ወያኔ ።

by Mussa Muhabbet ZeWollo

Friday, July 17, 2015

አንዳንዶች አገው እና አማራ ሲባል ሁለት የተለያየ ነገር ይመስላቸዋል

አንዳንዶች አገው እና አማራ ሲባል ሁለት የተለያየ ነገር ይመስላቸዋ

 ግን ሁለት ስም እና የቋንቋ ልዩነት እንጅ በተቀረው ነገር ሁሉ አንድ ናቸው፡፡ ስለዚህ እንደእኔ አስተያየት አገው አማራ ነው እላለሁ፡፡ ይህንም የምልበት ምክንያት በስፋት የሚታወቀው በተለምዶ የአማራ ባህል የሚባለው ስለሆነ ነው እንጅ ገልብጠን አማራ አገው ነው ብንልም ተመሳሳይ ነው፡፡ በአንድ ሽህ እንድ ነገሮች አንድ ሆነን በቁንቁዋ እና ስም ብቻ ነው የምንለያየው፡፡

ስልጣን ከዛጉዌ ወደ ይኮኖ አምላክ ሲሸጋገር በሰላም ነበር፡፡ በስልጣን ላይ እና ታች ሲሆኑ በወርቅ እና በብር ሰሀን ነበር የሚታጠቡት፡፡ ዛጉዌ ስልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ የአማራው በብር ሰሀን ሲታጠብ ዛጉዌዎች በወርቅ ሰሀን ይታጠቡ ነበር፡፡ እንደገና ከይኩኖ አምላክ ጀምሮ አማራው በወርቅ ሰሀን ሲታጠብ ዛገዌ በብር ሰሀን ሲታጠብ ነበር፡፡ እስካሁን ተመዝግበው ከምናገኛቸው የኢትዮጵያ የስልጣን ሽግግሮች ሰለማዊው በአገውና በአማራ መካከል የሆነው ነው፡፡

አንዳንድ ሰዎች ስለአገው ስጣኔ ስናወራ የአማራን ለአገው ልትሰጡ ነው ወይ ይላሉ፡፡ የላሊበላም ስልጣኔ እኮ የሁለቱም ነው ይላሉ፡፡ አወ የሁለቱም ነው፡፡ አንዱን እንደዚህ ነው ማለት ሌላው አይደለም ማለት አይደለም፡፡ አገውና አማራ አንድ ነው የምንልበት ምክላትም ይህ ነው እኮ፡፡ አማራ በዋለበት የታሪክ ቦታ አገው አለ፤ አገው በዋለበት የታሪክ ቦታ አማራ አለ፡፡ ከዚህም ተነስተን አንድ ነን እንላለን፡፡
አገው እና አማራ አንድ ስንልም ዝም ብሎ የቃል ብቻ አንድነት አይደለም፡፡ በሚጨበጥ እና በሚዳሰስ ነገር ላይ ተመስርተን እንጅ፡፡ እኔ እንዴውም በውስጤ አገው ስል አማራ ማለቴ ነው፤ አማራ ስል አገው ማለቴ ነው፤ ቀድሞ ወደሃሳቤ የመጣልኝን ከተጠቀምኩበት አንዱ ሁለቱንም ይገልጽልኛል፡፡ ለሽህ ዘመናት በመካከላችን አንዳች ልዩነት ኖሮ አያውቅምም፡፡ ስለምንም ነገር ልዩነት ብለን የምንናገረው የለም--እኔ እስከምረዳው ድረስ፡፡

በእርግጥ አሁን ለአማራ በአማራነቱም ሆነ በአገውነቱ እንዲሁም ለአገው በአማራነቱ ተኝቶለት የማያውቀው ወያኔ ውስን የአገው ወጣቶችን አጉል የሀሰት ታሪክ እየፈጠረ እንደሆነ እና ስንጥቅ ለመፍጠር እየጣረ እንደሆነ እናውቃለን፡፡ የሌለ ታሪክ መፍጠር ስራው የሆነውን ወያኔን ተንኮሉን ማክሸፍ ነው፡፡ በእርግጥ ለአንበሳ አይመትሩም ለአገው አማራ ልጅ አይመክሩም ነው፡፡
አገው አማራ ቤተ አማራ

Clear the Confusion and See the Contribution

Clear the Confusion and See the Contribution
==================================
Now Amhara Nationalism has hit its pick. Few Amhara boys and girls, when we first devised this idea, put four goals that we decidedly could achieve. One was to make the Amhara Amhara; the second was to make sure that being Amhara is a source of pride, not shame; the third was to shake the foundation of the old political discourse of the country; and the last and fourth, to prepare the Amhara people for their new State of Amhara. What really happened is farther and farther than we had imagined at the onset. It seems a swift and a thunder-like scenario has happened. We calculated it would take years to make the Amhara Amhara. But it took only months to march every conscious Amhara to the final destiny of Amhara, which is rising Amhara consciousness and establish new independent Amhara State. At the beginning, it was not taken serious, some dubbed it as some kind of joke was on the play. Few weeks latter, the major ethinonationalists such as TPLF thugs and OLF remnants have perfectly found out that something real was happening. They perfectly know what Amhara Nationalism is and the quest for independent state means. They know how costly it would be to them; and at the same time, they know how a blessing in disguise it would be for the Amhara. In just few months, we shaken the old foundation of the nation which has been a trap for the Amhara mighty. The unity camp began to look back and realize the difference between the realities and the nightmares.
We made sure that no one could stop us. We made sure that we have trashed the OLF and TPLF camps that have been preoccupied with defaming and degrading every thing of Amhara and the people themselves. We changed the game. We marched against some individuals and their patronage of old thinkings that are usually anti Amhara in their nature. We succeeded. We silenced those rude groups; and we significantly shut their mouth. We sent a very clear and dangerous message to the TPLF particularly. Now they know that the millennia old unproductive relation between the people of Tigray and the People of Amhara can no longer go the same way it used to go. We found the diagnostic treatment to that seemingly eternal disease of the Amhara and Tigre hostile relation. And that was a shocking news to them, and a blessing to us.
The rise of Amhara Nationalism can solve not only Amhara’ problem but also the problem of the Horn of Africa. The day Amhara start to think like Amhara and mobilize in the same mightiest flow is the day of the end of Amhara suffering.
The birth of Bete Amhara is now no longer a Facebook agenda. It has come to be true. We achieved enormous successes in just few months. We have now formed the Bete Amhara Organization. We surely know whatever defaming is campaigned against us is the source of our strength. The number and intensity of critics against us is not new in its kind, we know it that no one likes Amhara to mobilize and live for themselves. We are facing the same thing what Amhara have been faced with for millennia. We are getting attention from the OLF camp, the unity camp, and the TPLF camp, the latter being the deadliest enemy of the people of Amhara. We are being status updates which is a signal that displays we have hit our target.
No Retreat! No Excuse! No Compromise! Go Amhara! Go Bete Amhara!

108 የሚሆኑ በአማራነታቸው የታሰሩ ሰዎች ስም ዝርዝር

108 የሚሆኑ በአማራነታቸው የታሰሩ ሰዎች ስም ዝርዝር ደርሶናል፡፡ ከሰአታት በፊት የለጠፍኩት ይሄንን ሁሉ ስላላካተተ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ አሁንም በአማራነታቸው የታሰሩት እነዚህ ብቻ አይደሉም፡፡ በየገጠሩ የታሩትን አምላክ ይቁጠራቸው፡፡ በድብቅ እስር ቤቶች የሚማቅቁትን አምላክ ይቁጠራቸው፡፡ የእነዚህ ወንጀል ምንም ይሁን ምንም በአማራነታቸው የተነሳ ነው እንዲሰቃዩ የሚደረጉት፡፡ እኛ አማራ ተበድሏል ስንል ይህንን በአይናችን እያየን ነው፡፡ አሁንም ማንኛውም የሰው ልጅ የሆነ ሁሉ ለእነዚህ ወገኖቻችን ድምጹን ያሰማ፡፡ ስቃያቸውን ባንካፈል እንኳ እንዳስታወስናቸው ይታወቅ፡፡ ወያኔ በዘረኝነት አስረህ የምታሰቃያቸውን አማራ ወገኖቻንን ፍታ፡፡ ወገኖቻችንን የማሰርም ሆነ ቀና ብለህ የማየት መብት የለህም፡፡ እነዚህ ሰዎች ተከዜን ተሻግረው አልመጡብህም፡፡ ምንም ሳይጎድልባቸው የሚያኖራቸው የራሳቸው ምድረ አማራ አላቸው፡፡ አንተ ነህ በራሳቸው አገር መጥተህ ያሰርካቸው፡፡ ጨርቄን ማቄን ሳትል ቅል ቋንቁራህን ይዘህ ተከዜን ተሻግረህ ሄደህ መኖር ትችላለህ፡፡ በራሳችን አገር መጥተህ ወገኖቻንን ማሰርና ማሰቃየት ከህግም፤ ከተፈጥሮም፤ ከአገርነትም አንጻር መብትህ አይደለም፡፡ አማራውን ፍታው በራሱ አገር ይኑር፤ አንተም በራስህ አገር ኑር፡፡ አማራው በአገሩ የመኖር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ አማራ አገር አገር የሚለው በአንተ እንዲሰቃይ እና እንዲታሰር ሳይሆን በሰላም አብሮ መኖር እና ትልቅ መሆን ይቻላል የሚል የዋህ እምነት ስለነበረው ነው፡፡ ወያኔ ሆይ አሁንም አማራውን ፍታ፤ ተከዜን ተሻግረህ ሂድ፡፡ አንተም በቤትህ እኛም በቤታችን መኖር እንችላለን፡፡ ከወያኔ ጋር መኖር ትርፉ መከራ ብቻ ነው፡፡
1. ተመስገን ደሳለኝ
2. እስክንድር ነጋ
3. ናትናኤል መኮንን
4. አንዳለም አራጌ
5. ውብሽት ታዬ
6. ሃብታሙ አያሌው
7. ዳንኤል ሺበሺ
8. የሽዋስ አሰፋ
9. ዘላለም ወርቅአገኘሁ
10. ፍቅረማርያም አስማማው
11. እየሩሳሌም ተስፋው
12. ብርሃኑ ተክለያሬድ
13. ቴድሮስ አስፋው
14. ማትያስ መኩርያ
15. ብሌን መስፍን
16. ተዋቸው ደምሴ
17. ንግስት ወንዳፈራሁ
18. ሜሮን አለማየሁ
19. ናትናኤል ያለምዘውድ
20. ሰንታየሁ ቸኮል
21. ማስተዋል ፈለቀ
22. ንግስት ወንድይፍራው
23. ሂሩት ክፍሌ
24. እማዋይሽ አለሙ
25. ሰለሞን ከበደ
26. ሜጀር ጀነራል ተፈራ ማሞ
27. ጀነራል አሳምነው ጽጌ
28. ኮነሬል አለሙ መኮንን
29. ዮናታን ወልዴ
30. መሙሽት አማረ
31. አብርሃም ጌቱ
32. ታደሰ መንግስቱ ( ደብረታቦር)
33. ዘመን ምህረት
34. ሌ/ኮ ሰለሞን አሻግሬ
35. ተመስገን ባይለየኝ
36. ጌታቸው ብርሌ
37. ሻለቃ መስከረም ካሳ
38. አደፍርስ አስማማው
39. አለሙ ጌትነት
40. መኮንን ወርቁ
41. ይበልጣል ብርሃኑ
42. ጎበና በላይ
43. ም/ሳ የሽዋስ ምትኩ
44. አይተን ካሳ
45. ውድነህ ተመስገን
46. ሌ/ኮ ፋንታሁን ሙሃባ
47. አራጋው አሰፋ
48. አባቡ ተፈሪ
49. ሌ/ኮ ደምሰው አንተነህ
50. አዱኛ አለማየሁ
51. ክፍሌ ሰገኘው ( ህይወታቸው በእስር አለፈ )
52. መንግስቱ አበበ
53. ጌቱ ወልዴ
54. የሽዋስ መንገሻ
55. ፋናው ውቤ
56. ሻለቃ ምስጋናው ተሰማ
57. አበራ አሰፋ
58. ጎሽይራድ ጸጋው
59. አመራር በላይ
60. ጌቱ ወርቁ
61. ተዋቸው ደምሴ
62. ሀብታሙ ምናለ
63. ሻለቃ መኮንን
64. ሌ/ኮ አበራ አሳዬ
65. ሌ/ኮ አለምነህ ጌትነት
66. ሳጅን አበበ ባያብል
67. አቶ ዘነበ ደሳለኝ ( ሰማያዊ ፓርቲ)
68. አቶ መንግስቱ ተበጀ ( ሰማያዊ ፓርቲ)
69. አቶ ቴድሮስ ሀብቴ ( ሰማያዊ ፓርቲ)
70. አቶ ደብሬ አሸናፊ ( ሰማያዊ ፓርቲ)
71. አቶ መርከቡ ሀይሌ ( ሰማያዊ ፓርቲ)
72. አናንያ ኢሳያስ ( ሰማያዊ ፓርቲ )
73. አቶ አብርሃም ጌጡ ( መኢአድ )
74. በድሉ መንግስቱ
75. ፋንቱ ዳኜ
76. አንድዋለም አያሌው
77. መላኩ ተፈራ
78. መሳይ ትኩ
79. አሻግሬ መንገሻ
80. ታመነ መንገሻ
81. ብርሃኑ ሰፋይ
82. ሃብታሙ ገ/ሚካኤል
83. ምትኩ ገ/ሚካኤል
84. ጥላሁን አበበ
85. አንጋው ተገኝ
86. አባይ ዘውዱ
87. እንግዳው ዋኘው
88. በላይነህ ሲሳይ
89. አለበል ዘለቀ
90. መምህር ግዛው
91. አወቀ ብርሃኑ
92. ፀጋው ገበየሁ
93. አስቴር ስዩም ( አንድነት)
94. መሩ አሻገር ( አንድነት)
95. ወ/ሮ እመቤት ሃይሌ ( አንድነት )
96. ማቲያስ መኩሪያ
97. ቴዎድሮስ አስፋው
98. እየሩሳሌም ተስፋው
99. ንግስት ወንድይፍራው
100. ሜሮን አለማየሁ
101. ስንታዬሁ ቸኮል
102. መርከቡ ሀይሌ
104. አቶ ዘነበ ደሳለኝ
105. አቶ መንግስቱ ተበጀ
106. አቶ ቴዎድሮስ ሀብቴ
107. አቶ ደብሬ አሸናፌ
111. ዳንኤል ሺበሺ
112. የሽዋስ አሰፋ

Thursday, July 16, 2015

ወያኔ አማራ ስለሆንኩ ቆለጤን የሚቀጠቅጠኝ ስለሚወደኝ ነው አይነት ነገር

ወያኔ አማራ ስለሆንኩ ቆለጤን የሚቀጠቅጠኝ ስለሚወደኝ ነው አይነት ነገር

ትናንትና ዜና ሳፈላልግ የወገኖቸን ስም ዝርዝር በሞት ባህር መዝገብ ሰፍሮ አየሁት፡፡ ከነዛም አንዱ ደፈር ያለ ወንድሜ ቆለጡን እንደኮርማ መቀጥቀጡን ለህዝብ አሳየ፡፡ ቆለጡን የተቀጠቀጠው አማራ በመሆኑ እና ዘሩ መጥፋት እንዳለበት እየተነገረው እንደሆነ አስረዳ፡፡ ይህ ድርጊት ሽህ ጊዜ የተደጋገመ ነው፡፡ እኔ ራሴ በአንድ ወታደራዊ ካምፕ ያየሁትን ልንገራችሁ፡፡ አንድ መኮንን እያዞረ አሳየኝ፡፡ ያየሁትን ባላይ ይሻለኝ ነበር፡፡ ምድር ቤት ውስጥ እንደበረዶ እንዲቀዘቅዝ ተደርጎ የተሰራ ቤት አሳየኝ፡፡ ለትንሽ ደቂቃ መቆም እንኳ ፈተና ነው፡፡ ኩርምት ብለው የተቀመጡ እስረኞች አየሁ፡፡ ውስጡ ቀዝዛ ቆሻሻ ውሃና ጭቃ ሞልቶበታል፡፡ ከዛ ውስጥ የሚንበላወሱ ሰዎች አየሁ፡፡ መጀመሪያ ምነው ወደዚህ ቦታ ባልመጣሁ አልኩ፡፡ መኮንኑ ቃል በቃል እንዲህ አለኝ “እነዚህ የታሰሩት አማሮች ናቸው፤ በየትኛውም ክፍለ ጦር የአማሮች እስር ሁኔታ እንደዚህ ነው፡፡” ሞት እስካንገታቸው ያሰጠማቸውን አማራ ወገኖቸን በዛ እስር ቤት ውስጥ ፊታቸው ቆሜ አየሁ፡፡ መኮንኑ ቀጠለ “የሚተርፉት ጥቂት ናቸው፤ ቢተርፉም ከእንግዲህ ሰውኛ ኑሮ አይኖራቸውም፡፡” ይህ በየለቱ በአማራ ላይ የሚደረገው ግፍ ነው፡፡ ወደዛ አልገባም፡፡ ትናንትና በሰማሁት ነገር ግን ድጋሜ በጣም ተረበሽኩ፡፡ ከዚህ በፊት ካየሁት ሁኔታ ጋር ተደበላለቀብኝ፡፡

ይህንን እንደኮርማ የመቀጥቀጥ ዜና አንዱ ፌስቡክ ላይ ለጥፎ አየሁ፡፡ ከስሩ አንድ የአማራ ስም ያለው ሰው “እንደዚህ የምትጽፈው ህዝብ ከህዝብ ልታጣላ ነው” አለ፡፡ ሌሎችም የአማራ ስም ያላቸው ሰዎች ተመሳሳይ ነገር ጽፈው አየሁ፡፡ ለራሴ አንገቴን ጉልበቴ ውስጥ ከትቸ አዘንኩ፡፡ ይህ ህዝብ እዲነቃ ግን ምን እናሳየው? እውን ከዚህ በላይ ህዝብ ከህዝብ መጣላት አለ? በርግጥ አማራ ላይሆኑ ይችላሉ እነዚህ ሰዎች፡፡ ግን አሁንም ብዙ ያልነቃ እና ይህንን ሊረዳ ፍላጎት የሌለው አማራ የትየለሌ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ይህ ድርጊት እንዲሰቀጥጥህ እኮ አማራ መሆን አይጠበቅብህም፡፡ ሰው ብቻ መሆን ነው የሚጠበቅብህ፡፡ በራስህ ሊደረግ የማትወደውን በሌላው ላይ አታድርግ የሚለውን ፍልስፍና ማወቅ ብቻ በቂ ነበር፡፡ ግን ይህ አማራ ምንኛ ያልታደለ ቢሆን ነው አማራ እንኳ የማያዝንለት? አንዳንድ ጊዜ ምናለበት ሁላችንም ድንጋይ ልብ በሆንን እና ሲያጠፉን ለምን ብለን ሳንጠይቅ በጠፋን እላለሁ፡፡ በአማራነተህ ቆለጥህን ቀጥቅጦ መካን ከማድረግና ከማሰቃየት እንዲሁም ከመስደብ በላይ ምን በደል አለ? ጠብ የሚባለው ከዚህ በላይ ምንድነው!? 

ግን በአማራ ልጆች ላይ ለምንድነው ይህ ሁሉ በደል የሚፈጸምባቸው ብለን እንጠይቅ እስኪ፡፡ ክሱ እንደሚስረዳው “በአሸባሪነት” ስለተጠረጠሩ ነው፡፡ ቁም ነገሩ ግን አማራ አለም ከተፈጠረ ጀምሮ የአሸባሪነት ስነልቡና የሌለው ጨዋ ህዝብ መሆኑ ነው፡፡ እጅግ ሰላም ወዳድ እና ሰው አክባሪ ህዝብ ነው፡፡ አሁን ግንቦት 7፤ መኢአድ፤ ሰማያዊ እና የቀድሞው አንድነት ፓርቲ አባላት በመሆናቸው የሚቀጠቀጡት አማሮች አሸባሪዎች ስለሆኑ አይደለም፡፡ እነዚህ የአማራ ልጆች የጠየቁት ጥያቄ ቀላል ነው፡፡ እኛም አገራችን ነው፤ በጋራ አገራችንን እናሳድግ፤ ዜግነታችን አይገፈፍ፤ አለም ወደደረሰበት የስልጣኔ ደረጃ ለመድረስ መንገድ እንጀምር እና ወዘተ ነው፡፡ ሲጨመቅ የሰለጠነ ሰው እንሁን ነው ያሉት፡፡ ይህ ግን አማራን ካላጠፋ እንቅልፍ ባይኑ ለማይዞረው ወያኔ ሽብር ነው፡፡

በዛም አለ በዚህ የአማራ ዘር እየጠፋ ያለው ከትግራይ በበቀሉ ወያኔዎች ነው፡፡ ከሰማይ ባለ በማንኛውም የሽብር ምክንያት የታሰረ ማንኛውም አማራ አሸባሪ አይደለም፡፡ ሰላም ወዳድ እና ለአገሩ ቅን የሚመኝ ነው፡፡ እነዚህ አማሮች ትግራይ ሄደው አላሸበሩም፡፡ በትንሹ በራሳቸው በአማራ አገር በሰላም መኖር ይችላሉ፡፡ የአማራን አገር የወረረው ወያኔ ነው “አሸባሪ” እያለ የሚያጠፋቸው፡፡ የሰው አገር በወረራ ይዞ በተወረረው የአማራ አገር ዜጋ ተሸበርኩ ማለት ራሱ በምን ቋንቋ እንደሚገለጽ አላውቅም፡፡ ለዛውም አብረን በሰላም እንኑር ስለተባለ ብቻ፡፡ አገሬን ለቅቀህ ውጣ አልተባለ፡፡ እንደ አገር አስብና አብረን እንኑር ብቻ ነው የተባለው፡፡ 

የወያኔን የአማራ ጥላቻ እና ጭካኔ ሳስበው በጣም ያስደነግጠኛል፡፡ ጣልያን ተመሳሳይ የአማራ ጥላቻ እንደነበረው ተመዝግቧል፡፡ አማራን በተለያየ መንገድ በተለያየ ቦታ አጥፍቷል፡፡ ግን የዘር ፍሬ ቀጠቀጠ የሚል ታሪክ አላነበብኩም፡፡ አማራን አምካኝ መርፌ ስለመውጋቱ አላነበብኩም፡፡ በርግጥ ዘሩ እንዳቀላቀልበት ኮንዶም ተጠቅሟል ሲባል ሰምቻለሁ (እርግጠኛ አይደለሁም)፡፡ ይህ ከሆነ ጣልያን ከወያኔ በስንት ጣእሙ ማለት ነው፡፡ ያ ኮንዶም ሲጠቀም፤ ይሄ ግን ማህጸንን ፍሬ አልባ ያደርጋል፤ የወንድ ብልትን ይቀጠቅጣል፡፡ የወያኔ የአማራ ጠላትነት እስካሁን በታሪካችን አይተነው የማናውቀው እና ጣልያንን የሚያስንቅ ነው፡፡

ነገሩ ታሪክ ራሱን ሲደገም መሆኑ ነው፡፡ መጽሀፉ በእጀ ስለሌለ ቃል በቃል አላስታውሰውም ግን የታሪኩ አንድምታ ይታወሰኛል፡፡ እንዲህ ሆነ፡፡ ስሁል ሚካኤል ከትግሬ መጥቶ በጎንደር ንጉሱን በሻሽ አንቆ ገድሎ የኢትዮጵያን መንግስት ጣለ፡፡ ከዛም ፈላጭ ቆራጭ ሆነ፡፡ አንድ ጊዜ ታዲያ ወታደሮቹ ሁለት የአማራ ሰዎችን ይይዙና ቆዳቸውን እስከነነፍሳቸው ይገፏቸዋል፡፡ በገፈፉት ቆዳቸውም አሸዋ ይቋጥሩበት እና ቆዳቸው ለተገፈፈው ሰዎች ያሸክሟቸዋል፡፡ አሸክመውም ይነዷቸዋል፡፡ ይህን የሰማ የላስታ፤ የጎጃምና የጎንደር ሰው ታዲያ ሆ ብሎ ጎንደርን አስጨንቆ ከበበና ስሁል ሚካኤልን እንዳይጥ ጨፍጭፎ ገደለው፡፡ ይህም ማለት የዚህ የጭካኔ ነገር ከጥንትም የነበረ መሆኑን ያሳያል፡፡ አሁንም ትግሬን ስለምትጠላ የምትሉ አማሮች ትኖራላችሁ፡፡ ነገር ግን ሀቅ ትግሬን አይጠላም ወይም አይወድም፤ እንዳለ በእውነትነቱ ይተላለፋል እንጅ፡፡ ባለፈው ፖስት የአጼ ዮሐንስን ጭካኔ ጽፌ ነበር፡፡ በተለይም የአማራን አንገት፤ ምላስ፤ እጅና እግር በጭካኔ ይቆርጥ እንደነበር ታሪክ የሚያወሳውን እውነት አስቀምጨ ነበር፡፡ በተለይ ንጉሰ ነገስት አጼ ተክለ ጊዮርጊስን ከማረከው በኋላ አይኑን መንቅሮ አውጥቶ መሬት ላይ እንደጣለ አንብበናል፡፡ ስሁል ሚከኤልም የሰው ቆዳ ገፎ ስልቻ ሰርቶ እስከነፍሳቸው ቆዳቸው ተገፎ የነበሩ ሰዎችን አሸክሞ መንዳቱን አየን፡፡ ወያኔ ለአርባ አመት የአማራን የዘር ፍሬ እንደሚቀጠቅጥ እና የሴትን ልጅ ጡት በኤሌክትሪክ እንደሚያቃጥል እንሰማለን፡፡ እንግዲህ የዚህን የጭካኔ ምንጭ ለመመርመር ሶስት ምስክር በቂ መሰለኝ፡፡ ለምንድነው በአማራ ላይ ከጥንት ጀምረው እንዲህ የሚጨክኑት የሚለውን በየህሊናችሁ መርምሩ፡፡ ልብ በሉ! የዚህ መልስ እኔን መስደብ ላይ አይደለም ያለው፡፡

መለክ ሐራ ከቤተ አማራ

Wednesday, July 15, 2015

የረር= አዲስ አበባ

የረር= አዲስ አበባ
==========
ሸዋ ከላሊበላ ቀጥሎ የተቋቋመች የአማራ ማረፊያ ናት፡፡
በላሊበላ ብዙ ዘመናት በልጽገው ኖሩ፡፡ ከዛ ወደ ሸዋ መጡ፡፡
ሸዋ ላይም ዋና ከተማቸውን መሰረቱ፡፡ የአሁኗ አዲስ አበባ
ለሁለተኛ ጊዜ ነው የአማራ ከተማ የሆነችው፡፡ ከላሊበላ
መጥተው የመሰረቷት ከተማ አዲስ አበባ ነበረች የረር በሚል
ስም፡፡ አዲስ አበባና አካባቢዋ እስከ ልብነ ድንግል ሽንፈት
ድረስ የአማራ ዋና ከተማ ነበረች፡፡ በተለይ አሁን ከአዲስ አበባ
ምስራቅ የሚገኘው የረረ ለረጅም ዘመናት ዋና ከተማ ነበር፡፡
ከአዲስ አበባ ሰሜን ያለው የአሁኑ እንጦጦ ራጉኤል የአማራ
ዋና ከተማ ነበር፡፡ ስለዚህ አንዳንዶች በስህተት ወይም ታሪክን
ካለማወቅ ወይም ሆነ ብለው የራሳቸው ለማድረግ
እንደሚያልሙት የኦሮሞ ወራሪዎች ዝባዝንኬ በአጼ ምኒልክ
የተመሰረተች አይደለችም፡፡ አዲስ አበባና አካባቢዋ ከይኩኖ
አምላክ ጀምሮ እስከ ልብነ ድንግል ድረስ በገደምዳሜው
ለሶስት መቶ አመት የአማራ ዋና ከተማ ነበረች፡፡ አጼ ምኒልክ
እንጦጦ ላይ ከተማ የመሰረቱት የአምደ ጽዮንን ከተማ ፈለግ
በመከተል ነው፡፡ ራጉኤል ያለው ዋሻ የአምደ ጽዮን ግምጃ ቤት
ነበር፡፡
ስለሆነም አዲስ አበባ አንዴ እንጦጦ ላይ፤ ሌላ ጊዜ የረር ላይ፤
ሌላ ጊዜ ተጉለት ላይ እየተዘዋወረች የአማራ ከተማ ሆና
አገልግላለች፡፡ አጼ ምኒልክ አካባቢውን እንደገና ነው
የአባቶቻቸውን ባድማ ታሪክ ለመመለስ ከተማ ያደረጉት፡፡ ከዛም
እቴጌ ጣይቱ የየረርን ከተማነት መልሳ በቦታው ተከለች፡፡
ስለዚህ አዲስ አበባ ሁለት ጊዜ የአማራ መዲና ሆነች፡፡

ጎንደር፡--ወርቅ አበድሮ ጠጠር የተመለሰለት

ጎንደር፡--ወርቅ አበድሮ ጠጠር የተመለሰለት

ጎንደርና ትግራይ በጉርብትና ኖረዋል፡፡ ትግራይ በተፈጥሮ የተጎዳ ስለሆነ ጎንደር ከጥንት እስከ 1983 አ.ም ድረስ ከትግራይ የሚመጡ ሰዎችን ወገቧን ታጥቃ ስታስተናግድ ነው የኖረቸው፡፡ የጎንደር ህዝብ ለትግሬ አንድ ቀን በሩን ዘግቶበት አያውቅም፡፡ ለዘመናት ከትግሬ የሚመጡ ሰዎች የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ይሰጡ ነበር፡፡ ማነጽና ካብ መካብ የመሳሰሉ ሞያዎች ይሰሩ ነበር፡፡ በማሳ እየተቀጠሩ ይሰሩ ነበር፡፡ ስራ እንኳን ባይሰሩም በየድግሱ ተጠርተውም ሳይጠሩም ይስተናገዱ ነበር፡፡ ከእያዳንዱ የጎንደር ሰው ቤት አጠገብ ግባዛ ወይም ጎጆ ወይም በረንዳ ላይ ቆጥ መሳይ አልጋ ይሰራላቸውና እዛ ይኖራሉ፡፡ ስራ ሲኖር ይሰራሉ፡፡ ስራ ሳይኖር እንደቤተሰብ አብረው ይኖራሉ፡፡ ለሽያጭ የሚሆን ነገር ሲፈልጉም ቃርሚያ ይለቅማሉ፡፡ አማሮችም ቃርሚያ ተውላቸው ይላሉ፡፡ ከደግነታቸው ብዛት የጎንደር አማሮች አውድማ እንኳ ጨርሰው አይጠርጉም፡፡ ለትግሬዎች ተውላቸው እያሉ ትርፍራፊ እህል ይተውላቸዋል፡፡ ያንን ጠርገው ለራሳቸው ይወስዳሉ፡፡ በየመንደሩ እየሄዱ ደግሞ ሰባራ ማድጋ፤ ወንፊት፤ ምጣድ ወዘተ ይጠግናሉ፡፡ ለስራቸው ክፍያም ቤት ያፈራውን ይመገባሉ፤ ገንዘብ ይሰጣቸዋል፤ እንደገናም እህል ይሰፈርላቸዋል፡፡ ዘወትር የጎንደር ህዝብ ትግሬዎችን በቤቱ አስጠግቶ ያኖራል፤ ስራ ያሰራል፤ ከማህበራዊ ህይዎቱ ደሀ ናቸው፡ መጤ ናቸው ሳይል ያስተናግዳቸዋል፡፡ አንድም ጎንደሬ ለትግሬ ክፉ አይን አሳይቶ አያውቅም፡፡ የትግራይ መጻተኞች የጎንደር እንግዳ ሆነው ነው የኖሩት፡፡ ስንቶቹ ክፉ ቀን ያለፈላቸው በጎንደር ደግነት ነው፡፡

ወያኔ ወደ ስልጣን ሲመጣ ደርግ የጎንደርን ወጣቶች ስለጨፈጨፈ ከጎንደር ጋር ጠላትነትን አፍርቶ ነበር፡፡ የደርግ ወታደሮች ክብሩን ወዳድ የሆነውን የጎንደርን ህዝብ በብዙ መልኩ ተፈታትነውት ነበር፡፡ ባለትዳሮችን ሁሉ ይደፍሩ ነበር፡፡ ደርግን አምርረው በመጥላትም የጎንደር አማሮች ለወያኔ ስንቅ እያቀበሉ፡ የደከመውን እያሳረፉ፡ እየተንከባከቡ፡ መረጃ እየሰጡ፡ እያገዙ፡ አሳልፈው ወደ ጎጃም እና ሸዋ ላኩት፡፡ ከተወሰኑ ቦታዎች በቀር የጎንደር ሰው በሰላም ነበር አሳልፎ የሸኛቸው፡፡ ምግብ እያበላ፤ ዉሃ አያጠጣ፤ ደርግን ራሱ እየተዋጋ አመጣቸው፡፡

ግን አገር እንደተቆጣጠሩ ያደረጉት የመጀመሪያ ስራ ጎንደር ውስጥ የነበረን ንብረት ሁሉ ወደ ትግራይ ማጋዝ ነበር፡፡ የአርበኞች ገጀራ አልቀራቸውም፡፡ ፋሲለደስ ግቢ ውስጥ ገብተው ሰፈሩበት፡፡ ውስጡ ኖሩበት፡፡ ልብስ ሁሉ አስጥተውበት ይዉሉ ነበር ለረጅም ጊዜ፡፡ በመቀጠል ተሰሚነት ያላቸውን ሰዎች እያደኑ እየሰረቁ ጨረሷቸው፡፡ ከፊሎችን በመጠጥ ቤት ግርግር እያስመሰሉ ገደሏቸው፡፡ እስካሁን የት እንደደረሱ ያልታወቁ ብዙ ናቸው፡፡ የመብራት ማመንጫ አልቀረም ሲያግዙት፡፡ እንደአጀማመራቸው ጎንደርን ራስዋን የሆነ ትልቅ የጭነት ማሽን ቢገኙ የሚወስዷት ነበር የሚመስለው፡፡ በእርግጥ በተለያየ ጊዜ ቦታውን መውሰዳቸው አልቀረም፡፡

እያበላ እያጠጣ መንገድ እየመራ ያመጣቸው የወልቃይትና ጠገዴ አማራ የመጀመሪያው ገፈት ቀማሽ ሆነ፡፡ መሬቱን የትግራይን ምልስ ጦር በነዋሪነት አሰፈሩበት፡፡ ወንዶችን እያደኑ ገደሉ፡፡ ሴቶችን እያስገደዱ ልጅ ወለዱባቸው፡፡ በግፍ እየጨፈጨፉ ጨረሷቸው፡፡ ሁሉንም ያበላቸውን ያጠጣቸውን፤ ክፉ ቀን ያሳለፋቸውን የጎንደር ህዝብ አጎሳቆሉት፤ ገደሉት፤ በእድገት የአለም ጭራ እንዲሆን አደረጉት፤ መሬቱን ወሰዱበት፡ ወደትግራይ ለመውሰድ ያልተመቻቸውን ቦታ ሁሉ ለሱዳን ሰጡበት፡፡ ሰሊጥ አምራቹን ህዝብ የዋጋ ተመን እየጣሉ ምርቱን ራሳቸው ይረከቡታል፤ የአገራችን የአማራ ህዝብም ሲያለማ ከርሞ እርሱ እርቃኑን ይቀራል---እስከ ዛሬ ድረስ፡፡ ምንም አይነት የመሰረተ ልማት እንዳይደረግለት አደረጉት፡፡ ብዙ የጎንደር ህዝብ እስካሁን ድረስ በበቅሎ፤ ግመል እና በእግር ነው ረጃጅም ርቀት የሚጓዘው፡፡ ጎንደር ላይ የተመረተ ምርት ቀድሞ ሱዳን ገበያ ላይ ነው የሚውለው፡፡ የአማራ የሀብት ምንጭ መሬትና ከብት በመሆኑ ከብቶችን በመኪና እየጫኑ ወደሱዳን ለአመታት ሲያጓጉዙ ከረሙ--አሁንም ቀጥለውበታል፡፡ የዚህ ዋና አላማው ለራሳቸው ገቢ ማግኘት እና በሂደት አማራውን ከብት አልባ አድርጎ ስደተኛ ማድረግ ነው፡፡ ይህም ለወያኔዎች ጎንደርን እና ወሎን በግዛታቸው ስር የመጠቅለል አላማ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ አማራ ከብት ከሌለው መሬቱን ማረስ አይችልም፡፡ መሬቱን ካላረሰ ደግሞ ጥሎት ይሰደዳል፡፡ ያን ጊዜም ወያኔ ይረከበዋል፡፡

የወያኔ ታላቋ ሪፐብሊክ ህልም ትግራይ ብቻ ናት ብላችሁ የምታስቡ ተሳስታችኋል፡፡ የወያኔ የህልም ድንበር አባይ ወንዝ ነው፡፡ እርሱም ጎጃምን እና አብዛኛውን ወሎን ይጨምራል፡፡ ታላቋን ትግራይ ሲመሰርቱም ህዝቡን በማጥፋት ነው፡፡ ህዝቡ ካልጠፋ ከተቀረው የአማራ ወገኑ ጋር ሊነጠልና እሽ ብሎ ስለማይሄድላቸው ብቸኛው አማራጭ ህዝቡን ማጥፋት ነው፡፡ በሀያ አመት ውስጥ የጎንደርን ሲሶ መሬት ሲወስዱ ማንም ምንም አላላቸውም፡፡ በዚህ ሲሶ ምድር ውስጥ የሚኖርም ህዝብ በአብዛኛው ጠፍቷል፡፡ በዚህ ስሌት ከሄድን ከአስራ አምስት አመት በኋላ ሙሉ ጎንደር በእጃቸው ትሆናለች፡፡ ካሁኑ እንኳ ጃኖራን፤ ራስ ደጀንን እና ደባርቅና አምባጊዮርጊስን ለማካለል እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡ በመማሪያ መጽሀፍቶቻቸውም የትግራይ ግዛት እንደሆኑ ለአዲሱ ትውልድ እያስተማሩ ነው፡፡ እነሱ ልጆቻውን ሲያሳድጉ ይሄ ይሄ ምድር ያንተ አገር ነው፤ ትግራይ ነው፤ እንጅ ኢትዮጵያ ነው እያሉ አይደለም፡፡ እናም በስሌቱ መሰረት ከ50 አመት በኋላ ጎጃምና ወሎ የተባሉ አገሮች አይኖሩም፡፡ እዛ የሚኖር አማራ የተባለ ህዝብም አይኖርም፡፡ ለዚህም ነው እቅዳችን 60 ወይም 70 አመት ነው የሚሉት፡፡ ይህ ጊዜ አማራን ለማጥፋትና የአማራን አገር ትግራይ ለማድረግ በቂ እንደሆነ አስልተውት ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ደግሞ ህዝብን ማጥፋት ቀላል ሆነላቸው፡፡ በቴክኖሎጅ በመታገዝ ማንም ሳይሰማ ህዝብን መጨረስ ያስችላቸዋል፡፡ እያደረጉትም ነው፡፡ በአንድ ጊዜ አይደለም የሚጨርሱን፡፡ በዚህ ሰፊ የጊዜ እቅድ በዘዴ ነው፡፡ ቀስ በቀስ አማራ ተረት ሊሆን ነው፡፡

ለዚህም ማረጋገጫው የነጻ አውጭ ስማቸውን አለመቀየራቸው እና የጥላቻ ዘመቻቸው እየባሰበት መምጣቱ ነው፡፡ ለምን የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ የሚለው ስማቸው አልተቀየረም ለሚለው መልሱ የትግራይ አስተማማኝ ነጻነት የሚታወጀው አማራ ሲያልቅ ወይም ተጽእኖ ማምጣት ወደማይችልበት አናሳ ጎሳነት ሲቀየር ብቻ ነው፡፡ አማራ እስከሚያልቅ ድረስ የትግራይ ነጻ አውጭነት ስምና ስራቸው ይቀጥላል፡፡ እነሱ ሞኞች አይደሉም፡፡ ለጊዜው የያዙት ስልጣን እና ያገኙት ድል አስተማማኝ እና ዘለቄታዊ እንዳልሆነ ያውቃሉ፡፡ ለዚህም ትግራይን ነጻ ማውጣት ገና ሂደት እንጅ ግብ ላይ አልደረሰም ይላሉ፡፡ የትግራይ ነጻነት ግቡን የሚመታው አማራ ጠፍቶ የአማራ ለም መሬቶች የትግራይ ሲሆኑ እና ተው ብሎ የሚገዳደራቸው አማራ ሲጠፋ ብቻ ነው፡፡ ይህም ማለት በእነሱ ስሌት ትግራይ የወታደራዊ ነጻነት እንጅ ያገኘቸው ገና የኢኮኖሚ ነጻነት አላገኘችም፤ በወደፊት ታላቅ ሪፐብሊክነት ደህንነትዋም ከአማራ ተጽእኖ ነጻ በምትወጣበት ቅርጽ አይደለም ያለችው፡፡ ስለዚህም የትግራይ ህዝብ ገና ነጻ አልወጣም ብለው እስከቀደመ ስምና ግብራቸው እንደቀጠሉ ናቸው፡፡ ያለ ምንም ጥርጥር ትግራይ ነጻ ሆነች የሚባለው አማራ ጨርሶ ሲጠፋ ብቻ ወይም ተመናምኖ አናሳ ሲሆን ብቻ ነው፡፡ እስከዛ ድረስ አማራን ማጥፋት እና የትግራይን የመሬት፤ የሀብትና መሰል ስፋትና ግንባታ መስራት ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ የያዙት ድል ጊዜያዊ መሆኑን ይገነዘባሉ፡፡ ስለዚህም ይህንን ጊዜያዊ ድል መሰረት ለማስያዝ ተግተው ይሰራሉ፡፡ የኛ አማራም የክፋታቸው ልክና ጥልቀት ስላልገባው ያጅባቸዋል፤ የእነሱን ስራ ይሰራላቸዋል፡፡ ከእነሱ ጋር የሚሰራ አማራ አማራን ተረት ለማድረግ ተግቶ እየሰራ እንደሆነ ይወቀው፡፡ ግን ግን አንድ ቀን ሲገባው እየየ ብሎ ያለቅሳል፡፡ እኔ የምፈራው ወደህዝባቸው ተመልሰው በሚያለቅሱበት ጊዜ ሁሉም ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ ምንም መፍትሄ ማምጣት እንደማይችሉ እንዳይሆኑ ነው፡፡ ከረፈደ በኋላ ለቅሶ ትርፉ ቅንድብ ማሳበጥ ብቻ ነው፡፡
እንግዲህ ጎንደር ወርቅ አበድሮ ጠጠር እንዲህ ተመለሰለት

መለክ ሐራ ከቤተ አማራ
ጎንደር ቤተ አማራ