አጼ ዮሐንስ እና አማራ ላይ የፈጸመው ክህደት
በጎንደር ቤተ አማራ ሳምንት ስለ አጼ ዮሐንስ ስናወራ የሚበዛው ነገር ከጎንደር ጋር ግንኙነት ያለው መሆኑን በማጤን ነው፡፡ የአማራ ልጆች ከእንግዲህ የሚፈሩት ሁለት ነገር ብቻ ነው--ውሸት እና እግዜርን፡፡ እስካሁን በይሉኝታ እና አብሮ ለመኖር በሚል ብሂል በእኛ ላይ የተካሄዱ ክህደቶችን ሳይቀር በቸልታ ስናልፋቸው ኖረናል፡፡ በተቃራኒው ሁለቱም የኦሮሞና የትግሬ ወራሪዎች የልጅ ልጆች የእኛ የሆነውን ሁሉ ከማጥላላትና ከመርገም ወደኋላ ብለው አያውቁም፡፡ ስለዚህ የአማራ ልጆች ይሉኝታችን ስለተሰበረ በቀጥታ መናገር ጀምረናል፡፡ አካፋን አካፋ ካላሉት የወርቅ ማንኪያ ነኝ ይላል በሚል መርህ እውነትን እና ውሸትን ያለ አንዳች ይሉኝታ እንገልጻለን፡፡ ስለዚህም የዚህን ንጉስ ስራ እና አማራ ላይ የተፈጸመውን ክህደት በእውነት ላይ ብቻ ተመስርተን እናብራራለን፡፡
በብዙ መለኪያዎች አጼ ዮሐንስ ከሀዲ ነው፡፡ በሀገር ክህደት ወንጀል መሰቀል የሚገባው ወንበዴ ነበር፡፡ ከዘመነ መሳፍንት ማብቃት ወዲህ ይህ ንጉስ በአማራ ላይ ያደረሰውን በደል ማንም አላደረሰውም--በዚህ ዘመን በወያኔ የበለጠ ከመደረጉ በቀር፡፡ ከአነሳሱ እስካወዳደቁ የአማራ ጠላት ሆኖ ነው የኖረው፡፡ እኔ ይህን ንጉስ ብዙ ጊዜ በይሉኝታ ስራራለት እና ስከራከርለት ነበር፡፡ በቤተ አማራ ጉዳይ ከተሰማራሁ ወዲህ ግን እውነትን በአግባቡ መመርመር በመጀመሬ ድሮ የነበረኝን ግምት እኔ ራሴ ታዝቤውአለሁ፡፡ በፍጹም ስህተት ነበርኩ፡፡ በአማራ ላይ ተነግሮ የማያልቅ በደል የሰራ ሰው ነበር፡፡
በመጀመሪያ አጼ ቴዎድሮስን አሳልፎ እንደይሁዳ ሸጠው፡፡ በጠብመንጃና በመጋረጃ እንዲሁም በመነጽር ነው የሸጠው፡፡ የንጉሱን ልጅ ለምን ትወስዳላችሁ እኔ ላሳድገው እንኳ አላለም፡፡ የድሮ ነገስታት ግን የተሸናፊዎችን ቤተሰቦች ራሳቸው ነበር የሚንከባከቧቸው፡፡ እሱ ግን በምንግዴሸነት የንጉስ ሚስት (እቴጌ) እና ልኡል አልጋ ወራሽ ልጅ እንደከብት በጠላት ተነድተው ሲሄዱ ዝም አለ፡፡ በዚህም ከአማራ ጋር አንዳች ግንኙነት እንደሌለው አስመሰከረ፡፡ የአጼ ቴዎድሮስ ልጅና ሚስት በውጭ አገር ሰው ሲጋዙ አጨብጭቦ ሸኘ፡፡ ለዚህም ውለታው አማራን የሚወጋበት መሳሪያ ከእንግሊዞች ተቀበለ፡፡ በጊዜው የተጻፈው የሄንሪ ብላንክ መጽሀፍ እንደሚያትተው እንግሊዞች አጼ ዮሀንስን በመጠቀም ጸረ አማራ ስራ ነው የሰሩት፡፡ በጽሁፉም ቴዎድሮስን በአማራነቱ ብዙ ቦታ ላይ ሰድቦታል፡፡ ወሎና ሸዋንም ሊያነሳሱበት ሞክረው ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡
ከአጼ ተክለ ጊዮርጊስ ጋር ተዋግቶ ንጉሱን ሲያሸንፍ ከክርስቲያን ንጉስ የማይጠበቅ የአረመኔ ተግባር ፈጸመበት፡፡ ከማረከው በኋላ በጭካኔ ሁለቱን አይኖቹን መንቅሮ አውጥቶ ጣላቸው፡፡ ንጉስን ያህል ነገር እንደዛ ማድረግ ታይቶ አይታወቅም፡፡ ያን ያደረገውም ንጉሱ አገው አማራ ስለሆነ እና በአገው አማራ ላይ ከፍተኛ ጥላቻ ስለነበረው ነው፡፡ የሚገርመው የንጉሱ ልጅ የእሱ ሚስት መሆንዋ ነው፡፡ እንዴት አይነት የወረደ ሰብእና እንደሆነ እንግዲህ ገምቱት፡፡
ከአጼ ተክለ ጊዮርጊስ ጋር ተዋግቶ ንጉሱን ሲያሸንፍ ከክርስቲያን ንጉስ የማይጠበቅ የአረመኔ ተግባር ፈጸመበት፡፡ ከማረከው በኋላ በጭካኔ ሁለቱን አይኖቹን መንቅሮ አውጥቶ ጣላቸው፡፡ ንጉስን ያህል ነገር እንደዛ ማድረግ ታይቶ አይታወቅም፡፡ ያን ያደረገውም ንጉሱ አገው አማራ ስለሆነ እና በአገው አማራ ላይ ከፍተኛ ጥላቻ ስለነበረው ነው፡፡ የሚገርመው የንጉሱ ልጅ የእሱ ሚስት መሆንዋ ነው፡፡ እንዴት አይነት የወረደ ሰብእና እንደሆነ እንግዲህ ገምቱት፡፡
ወሎ ላይ የሀይማኖት ጦርነት በማድረግ ሙስሊሞችን እጅ እና እግራቸውን በመቁረጥ አጠፋ፡፡ ብዙዎችም አገር ጥለው ተሰደዱ፡፡ ወሎን አጠፋት፡፡ ጎጃምን ገና ለገና ከንጉሱ እምነት የለተየ ቀኖና ይቀበላል በሚል ዘር አጠፋ፡፡ በራሱ ቃልም “ክርስቲያኑ አገር ጎጃምን አጠፋሁት” አለ፡፡ ዛሬ እሱ እጅና እግራቸውን የቆረጣቸው የጎጃም አካባቢዎች አንድ እጁ ነሴ፤ ሁለት እጁን ነሴ እየተባሉ ጠራሉ፡፡ እጃቸውን ስለነሳቸው ማለት ነው፡፡ ይህ እንግዲህ በሀይማኖት ሰበብ አማራ ላይ ያደረሰው ጥፋት ነው፡፡
የሸዋን ንጉስ ምኒልክን እና የጎጃምን ንጉስ ነገር ሰርቶ በተንኮል አጣልቶ አዋጋቸው፡፡ የተንኮሉ ስሌትም ሁለቱም ሲሸነፉ ደካማ አማራን እንደፈለገ ለመርገጥ ነበር፡፡ ይሁን እና እርስ በእርስ የተዋጉት የአማራ ጦረኞች አጼ ዮሀንስን በመተው እርስ በእርሳቸው አንድ ሆኑ፡፡ በዛ ጊዜ ጎጃም እና ሸዋ በመተባበራቸው አማራ ከባሰ ጥፋት ዳነ፡፡
ለእንግዝ ቅጥረኛ በመሆን የሱዳንን የነጻት ተዋጊዎችን በመውጋት ጎንደር ላይ ይህ ቀረው የማይባል ጉዳት እንዲደርስ አደረገ፡፡ የእሱን ወረራ በመቃወም ሱዳኖች ጎንደርን ወረሩ፤ አወደሙ፤ ህዝቡን ጨረሱ፡፡ የእርሱ መዘዝ ጎንደርን አጠፍቶ ፍርስራሽ ብቻ አደረጋት፡፡ በጣም የሚገርመው በመጀመሪያው ዙሩ ጦርነት ጎንደር የጠፋቸው ለከተማዋ እና ለጠቅላላዋ ጎንደር አንድም ጠባቂ ሰው ስላላስቀመጠላት ነው፡፡ ይህም ግዴለሽነቱን ያሳያል፡፡ አንዳንዶች ለጎንደር ብሎ ተዋጋ የሚሉ አሉ፡፡ ይህ ውሸት ነው፡፡ ለጎንደር ብሎ ተዋጋ የሚባለው ደርቡሽ አሻፈረን ብሎ ጎንደርን ቢወር እና እርሱን ለማስለቀቅ ቢዋጋ ነበር፡፡ ነገር ግን ድርቡሾች ጎንደርን ሳይነኳት የራሳቸው አገር ሄዶ ነው የገጠማቸው፡፡ ያን ያደረገውም እንግሊዝን ለማስደሰት ነው፡፡ እውነታው ለጎንደር ተዋጋ ሳይሆን መባል ያለበት እንደኢትዮጵያዊ ንጉስ ለሚያስበው ሰው እንኳ ውርደት ነው ያመጣው፡፡ በሎሌነቱ እና በሞኝነቱ በጫረው ጦርነት ኢትዮጵያ ናት የተዋረደቸው፡፡ ሱዳኖች አንገቱን ቆርጠው ሆያ ሆየ ሲጫወቱበት የኢትዮጵያ ክብር ነው የወደቀው፡፡
ታሪክ ራሱን ይደግማል እንዲሉ ዛሬ ወያኔ የዚህን ንጉስ ስራ ነው እየሰራ ያለው፡፡ ንጉሱ ክርስትና ላይ ጫና አሳድሯል፤ ወያኔም እንደዛው፡፡ ንጉሱ እስልምና ላይ ጦርነት አውጇል፤ ወያኔም እንደዛው፡፡ ንጉሱ ሸዋና ጎጃም ብሎ በሴራ ከፋፍሎ እንዳዋጋው ሁሉ ዛሬ ወያኔ አማራን በብዙ ነገር ይከፋፍለዋል፤ ያጠፋዋል፡፡ ንጉሱ ጎጃምን አጥፍቷል፤ ወያኔም እንደዛው---የቤኒሻንጉል እልቂትና መፈናቀል፤ የጉራፈርዳ እልቂት እና መፈናቀል፤ በ1980ቹ አጋማሽ የተከሰተ ወረርሽኝ ያለ ህክምና ያጠፋው ህዝብ፤ እና አሁን የሚሰማው የዘር ማጥፋት ሂደት፡፡ ወሎን በሙስሊምነቱ ከማጥቃት በተጨማሪ ግዛቶቹን ነጥቆ መውሰዱ የወያኔን ዮሐንሳዊ የተግባር ልጅነት ያመለክታል፡፡ ንጉሱ ለእንግሊዝ በታዛዥነት ሱዳኖችን እንደወጋው ወያኔም ከሶማልያ ጋር በአሜሪካ ተቀጥሮ ይዋጋል፡፡ የንጉሱን ድርጊት ለመበቀል ጎንደር ላይ ድርቡሽ ወረራና ጭፍጨፋ እንዳደረገው ሁሉ በሶማልያ መወረር የተቆጣው እስላምም ባፈው የወገኖቻችንን አንገት በመቀንጠስ ጥላቻውን ያሳየን መሆኑ የታሪክ መደገምን ያመለክታል፡፡ ገናም ለወደፊቱ ብዙ መዘዘ አለ፡፡ ንጉሱ በነገስታቱ ላይ ያደረገውን አይነት ጭካኔ ወያኔም ይደገመዋል---ለምሳሌ የፕሮፍ አስራት የጭካኔ አገዳደል፤ በልዩ ልዩ ቦታ የተጨፈጨፈው አማራ፤ በእስር ቤቶች የሚደረገው ዘግናኝ ስቃይ፤ እና በአደባይ የሚፈጸመው ግድያ የንጉሱን የግብር አባትነት የሚደግም ነው፡፡
ይህ ሁሉ የሚያመለክተው ታሪክ ራሱን የሚደግም መሆኑን እና የንጉሱን ክርስቲያንነት እና አሁንም ከዛው የበቀሉትን ወያኔዎች ክርስትና የልብ ሳይሆን የይስሙላ መሆንን ነው፡፡ ሀይማኖት ያለው ሰው መቸም ያንን ያህል የአረመኔ ስራ ይሰራል ብሎ ማሰብ ይከብዳል፡፡ ንጉሱም ወያኔን የሚከተለው ጄሌም የስም እንጅ የተግባር ሀይማኖተኞች እንዳልሆኑ ያሳያል፡፡
መለክ ሐራ ከቤተ አማራ
ጎንደር ቤተ አማራ
ጎንደር ቤተ አማራ