Bete Amhara

Bete Amhara

Sunday, July 12, 2015

አይቴ ሐገሩ ለአማራ (የአማራ ሐገሩ የት ነው?)

አይቴ ሐገሩ ለአማራ (የአማራ ሐገሩ የት ነው?) 
Addis Alem እንደጻፈው
እንግዲህ እርማችሁን አውጡ፤ አማራ ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለተኛና ከዚያ በታች ዜግነት ቢያገኝ እንጅ ሐገሩ አይደለም። ነው የሚል ካለ ወይ ተኝቷል ወይንም መስማት አይፈልግም። ኢትዮጵያ ሐገሩ በነበረችበት ጊዜ ለሐገሩ ሰርቶ፤ መንገድ አሳይቶ፤ አለም ባልሰለጠነችበት ጊዜ እንኳን ራእይ ኖሮት ለአላማ በአላማ የኖረ ህዝብ ነው። ስለአንድነት ብናወራ ከእኛ በላይ መናገር የሚችል ማንም የለም። ዘመነ መሳፍንትን እነእንትና ጀምረውት እንኳ እኛ ልናቆም መከራችን አየን፤ መጨረሻም ጠላት ጎትተው መጡብን። ዘረ ቆርጥም የሆነች ሐገር። አማራ ኩሩ ህዝብ ነው። ካልነኩት የማይነካ። የዛሬን አያድረገው እንጅ ሲነኩት የሚፋጅ እሳት ነበር። የአማራ ህዝብ ታማኝ፤ ለቃሉ ሟች ነው። ማንም ስም የሌለው ኢትዮጵያዊ አማራ ህዝብ ወስጥ መኖር ይችላል፤ምስክር ጥሩ የሚለን ያለ አይመስለኝም ጸሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው። ለተቸገው ደራሽ ለተራበ አቁራሽ ነው። በደጉ ጊዜ አማራ ሐገሬ የሚለው ድፍን ኢትዮጵያን እንጅ አሁን ህውሀት የሰጠውን ሲፈልግ ለትግሬ ሲፈልግ ለሱዳን እየሸነሸነ የሚሰጠውን ቁራጭ መሬት አይደለም። ኤርትራም ሐገሬ ብሎ ኑሯል። አማራ የሚያስበው በሰውነቱ እንጅ በአማራነቱ አልነበረም። ሰው ከሆንክ በቂው ነበር፤ አብረን እንኑር እንጅ ለምን መጣህብኝ ብሎ የሌላ ቋንቋ ተናጋሪወችን አላባረርም፤ ኢትዮጵያን ተሸክሞ ነበር።
ዛሬስ?
ዛሬማ እንደአውሬ እየታደነ ይገደላል፡፡ እራሱ ባቀናት ሐገር ተገፍቶ እስር ቤት ይገባል፤አንተ መኖር ያለብህ እዚች ብቻ ነው ተብሎ ተከልሎ ይኖራል፡ሲፈልጉ ይገድሉታል፤ ያባሩታል፤ ያስፈራሩታል፡ ይቀንሱታል፡ እድሜ ልኩን ያካበተውን ንብረት ይዘርፉታል። አርሶ ባበላ ከመሬቱ ይነጥሉታል፡ አማራ እንዳይዋለድ ከፍተኛ ሴራ ይሰራበታል፤ ያረገዘችውንም አማራ ትወልጃለሽ ብለው እናትን ከነልጇ ይገድሏታል። የአማራ ሀብታም እንዳይኖር ከፍተኛ ውድድር በመፍጠር ከገበያ ያወጡታል፡ ብዙ ቀረጥ ይጭኑበታል። እንዳይማር በግ ጠባቂ ሁኖ እንዲቀር ይጎነጉኑበታል፡፡ በበሽታ ሲጠቃ ሐገር እንደሌለው፤ አማራ ሀኪም እንደሌለ ያለሀኪም ይሞታል። ለመውለድ የሄደችን እናት ጓንት ግዢ ተብላ የምትጠየቅ የአማራ እናት ናት። መብራት አያስፈልግሽም ተብላ በጨለማ እንድትኖር የተፈረደባት ሐገር የአማራ መሬት ናት(እስኪ ጀነሬተር ከጎንደር የተወሰደበትን ምክንያት የሚነግረኝ):: ይሄ ብሄር ጠላቴ ነው ብሎ ስርአት ተቀርጾ እርሱን ከምድር ለማጥፋት የተዶለተበት ብሄር አማራ ብቻ ነው። ለጦርነት እንጅ ለልማት የማይፈለግ አማራ ብቻ ነው። እንዲሞት እንጅ እንዲኖር የማይፈለግ።
የአማራ ህዝብ የት ገባ? ግማሹ በገደል ተወረወረ፤ግማሹ በጥይት ተገደለ፡በበሽታ ተገደለ። አለሁ የሚለውም “አንድነት“ በሚለው ዘፈን እየተውረገረገ የእርሱ ተራ እስኪደርስ ወንድሞቹን ያስገድላል። ከእንቅልፉ ያልነቃ አማራ። ለመሆኑ ኢትዮጵያ ሐገሩ ከሆነች ይህ ሁሉ ግፍ ይደርስበት ነበር? ኢትዮጵያ ሐገሬ እንዲላት ምን አደረገችለት? የምትገድል እናት አለች እንዴ? የአማራ ሐገሩ የት ነው? እግዚአብሔር ያያል።