ደንቆሮ የሰማ እለት ያብዳል ይባል ነበር
ብዙወቻችን የማንፈልገው እና ፈፅሞ እንዳይሆን የምንመኘው የኢትዮጵያችን መበታተን ( መንግስት አልባ መሆን ወይንም አለመቻቻሉ አድጎ የከፋ ነገር ዉስጥ መግባት ) የምንጠላው ነገር ቢሆንም ፍፃሜው ግን አየገሰገሰ ሀገራችን ኢትዮጵያም የሰው ያለህ እያለች ነው፡፡
ዉድ የአማራ ልጆች እና ሀገር ወዳድ የሆናችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ወያኔ ዛሬ እያደረገ ያለው ( ትውልዱ ዘሩን እንዳይተካ ማድረግ፤ መሬቱን እየሸነሸኑ ግዛቱን ማጥበብ፤ በኢኮኖሚ እና ፖለቲካዊ ተፅዕኖ ሀቅሙን ማዳከም፤ ከያለበት እያፈናቀሉ በአንድ ትንሽ ስፍራ ማስቀመጥ እና ቢቻል ጨርሶ ማጥፋት አለዛም በጣም ትንሹ ብሄረሰብ አድርጎ ባርያ ማድረግ፤ አማርኛ ሚባለውን ቁአንቁአ ፈፅሞ ማጥፋት ወዘተ ) የሚሉት ትናንት ከፍተኛ ጥናት ተደርጎባቸው እና ተወስነው የተደመደሙ ናቸው፡፡ እናም ዛሬ የምናየው የውሳኔው አፈፃፀም አንጂ አዲስ ነገር አይደለም፤ ትናንት እሄን ውል የሚያውቁ እና የተረዱ ወገኖቻችን ብጮሁም ሰሚ አጥተው እና ሚረዳቸው ጠፍቶ በግፍ ተገድለዋል፤ ታድያ እኛ አልተረዳናቸውም ነበርና ያኔ ሲነግሩን አልሰማነም ኖሮ ዛሬ ስንሰማ እንደ አዲስ እንበረግጋለን፡፡
ዉድ የአማራ ልጆች አስተውሉ፡፡ ሞቅ ያለ ጩህት ወደሰማችሁበትም አትንጎዱ፡፡ ወያኔ ከመነሻው ፀረ አማራ ነው! ያንም በተግባር እያየን ነው (ወያኔ እና ሻቢያ የታጠቁት የመደብ ጭቆና ደርሶባቸው የመደብ ትግል ሊያደርጉ አልነበረም አማራን ለመደምሰስ በሚል የዘረኚነት ቅጀት ነው)፤ አሁንም ቢሆን የተጣሉት በግል ጉዳያቸው ሲሆን አሁንም አማራ ኢትዮጵያዊነት የሚለው ግን የሚያስማማ የግል ጉዳያቸው ነው፡፡
ዉድ የአማራ ልጅ አስተውል፡፡ (........) ጊንጥን ፈርቶ እባብ ቤት ተደበቀ እንደሚባለው አትሁን፡፡ ለመታገልም አትፍራ፤ ወያኔ እና ሻቢያ እኮ ሳይበደሉ ተበድለናል ብለው የውሸት ታሪክ ፅፈው፤ ተማሪው ትምህርቱን፤ ነጋዴው ንግዱን ትቶ፤ በስደት የነበረው ሙህር ሳይቀር በረሃ ገብተው ታግለዋል፤ ታድያ አንተ አኮ ከዛ የከፋ ወንጀል ተፈፀመብህ-- ማትታገልበት ምን ምክንያት አለ?
ከ10 ለማኝ 9 አማራ ነው፤ሴተኛ አዳሪው፤ ሎተሪ አዟሪው፤ ጎዳና ተዳዳሪው፤ ተሸካሚው፤ ጎስቁአላው ያንተ የኔ ወንድም አህት ብቻ ሁኗል፡፡ በስደት በረሃ እና ባህር ውስጥ ከሚያልቀው አብዛኛው እሄ ብሶተኛ ወገንህ ነው፡፡ ታድያ መቼ እንታገል? መቸስ ነው ሚበቃን? ነው ወይስ እንደ ፍልስጤም ሕዝብ ካምፕ ዉስጥ ሁነን ልንጮህ ነው?
የወገኔ ልጅ ንቃ ካለህበት ተነስ እና ወደ ብሶተኛው ወገንህ ፊትህን አዙር፤ የጀመርከው ትምህርት ወይንም ንግድ ለጊዜው ይቁም እና ለነፃነት ታጠቅ፤ የተሰደድህም ተመለስ .........................
የሰሜን ኮከብ
የወገኔ ልጅ ንቃ ካለህበት ተነስ እና ወደ ብሶተኛው ወገንህ ፊትህን አዙር፤ የጀመርከው ትምህርት ወይንም ንግድ ለጊዜው ይቁም እና ለነፃነት ታጠቅ፤ የተሰደድህም ተመለስ .........................
የሰሜን ኮከብ