Bete Amhara

Bete Amhara

Saturday, July 11, 2015

ወራሪው ወያኔ ደብረታቦር ላይ እንዲህ አደረገ

ወራሪው ወያኔ ደብረታቦር ላይ እንዲህ አደረገ
በ1985 ዓ.ም መጨረሻ የጀኔራል ሀይሌ መለሰን ቤተሰቦችና ጠቅላላ የመንደሩን ሰዎች ሰብስቦ ወስዶ ገደለ፡፡ ከዛም ጫካ ውስጥ በመጣል የጅብ ራት አደረጋቸው፡፡ የጄኔራሉ የወንድም ልጅ በአጋጣሚ ከስፍራው አልነበረምና ተረፈ፡፡ ወደዘመዶቹ ሄዶም የአባቱን አስከሬን ከጅብ የተረፈውን አግኝቶ ቀበረ፡፡ ግን ወዲያው አበደ፡፡ እብድ ሆኖ ቀረ፡፡

ከደብረታር እስር ቤት ሰዎችን በላንድሮቨር ጭኖ በተለያየ ጊዜ በመውሰድ ጋሳይ የተባለች ቦታ ላይ ይገርፍ ነበር፡፡ እንደ ደርግ ጊዜ፡፡
ደብረ ታቦር ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ እየወሰደ እየገደለ የተገደሉ ሰዎችን አስከሬን ለአውሬ ይጥል ነበር፡፡ ከእነዚህም አንዱ የደምቢያ አውራጃ አስተዳዳሪ የነበረው አስር አለቃ ጌትነት ይገኝበታል፡፡ የአስር አለቃውን አስከሬን ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ከጣሉት በኋላ ከፊሉን ጅብ በልቶት የተረፈውን አንድ ካህን አግኝቶ ያመለክታል፡፡ በተገላቢጦሽ ካህኑ አንተ ነህ የገደልክ ተብሎ ታሰረ፡፡

እንደሚታወቀው ትግራይ ለማገዶም ሆነ ለቤት መስሪያ የሚሆን ዛፍ የማይበቅልበት አገር ነው፡፡ ትግራይን ለማልማት በሚል ሰበብ ወራሪው የወያኔ ጦር ደብረ ታቦር ከተማ ውስጥ በራስ ጉግሳ ጊዜ የተተከሉትን ትልልቅ ዛፎች በሙሉ በመቁረጥ ወደትግራይ አጋዘ፡፡ የከተማዋ ትልልቅ ዛፎች የተቆረጡት በቀበሌ ትእዛዝ በዘመቻ መልክ ነበር፡፡ ከተማዋን ምድረ በዳ አደረጋት፡፡ ከዛም ወዲህ የደብረ ታቦር ህዝብ በማገዶ እንጨት በጣም ይቸገር ነበር፡፡ ሌሎችንም ደርግ የተከላቸው ጫካዎች መንጥሮ ወደ ትግራይ አጋዘ፡፡

ከ1983 በፊት ደብረ ታቦርን እንደተቆጣጠረ የከተማዋን ወጣቶች አፍሶ ትግራይ ውስጥ ሽራሮ የሚባል ቦታ ከምድር በታች ያስራቸዋል፡፡ እዛም ለሁለት አመት ከምድር በታች አስሮ የተላ ዱቄት እንዲመገቡ በማድረግ በአሰቃቂ ሁኔታ አስሮ አቆያቸው፡፡ ጸጉራቸው ሸብቶ እና በሽተኞች ሆነው ወጡ፡፡ (ከእነዚህ አንዱ ተርፎ ዛሬ አለ፤ ሙሉ ታሪኩን እንዲያካፍለኝ እጣርኩ ነው፤ ሲደርሰኝ እለጥፈዋለሁ፡፡)
ድል ለአማራ ህዝብ
ቤተ አማራ