Bete Amhara

Bete Amhara

Sunday, July 5, 2015

የትግራይ ነገስታት ተንኮል

የትግራይ ነገስታት ተንኮል
በ1868 እ.ኤ.አ. አጼ ቴዎድሮስ በመቅደላ ራሳቸውን ሰውተው የኢትዮጵያ ማእከላዊ መንግስት ባዶ በነበረበት ሰአት ለሃገረ ገዥው ዙፋን ሶስት ታላላቅ ተፎካካሪዎች ነበሩ። የላስታው ንጉስ ዋግስዩም ጎበዜ፤ የትግራዩ አጼ ዮሃንስ እና የሸዋው አጼ ሚኒሊክ። የላስታው ንጉስ ዋግስዩም ጎበዜ የአጼ ዮሃንስ እህት የሆነችውን ድንቅነሽ ምርጫን አግብቶ ይኖር ነበር። በዚህ ቤተሰባዊ ትስስር የተነሳ ንጉስ ዋግስዩም ለአጼ ዮሃንስ በትግራይ ውስጥ የፖለቲካ እውቅና ማግኘት የቀኝ እጅ ሆነው አግልግሏል።
ይሁን እንጅ የዋግስዩምን የአመራር ብቃት እና በዋግ አካባቢ ያለውን ህዝባዊ ድጋፍ የተመለከቱት እህት እና ወንድም ሁኔታው አላምራቸው ሲላቸው እና ንጉሱ ወደ ዙፋኑ እየቀረበ መሆኑ ሲገባቸው ቅስሙን የሚሰብሩበት መላ ሲዘይዱ ኖረው በአንድ ነገር ተስማሙ። በጦርነት ከማሸነፍ ባለፈ ዋግስዩምን የእቁም እስረኛ አድርጎ ማስቀመጥ። በ1871ም በጦርነት ከተሸነፈ በኋላ ምኞታቸው ተሳካላቸው እና አድዋ አጠገብ ከሚገኘው አቡነ ገሪማ ገዳም ህይወቱ በ1873 እስክታልፍ ድረስ ከወንድሙ እና ከእናቱ ጋር በባለቤቱ ሰላይነት ለሁለት አመት የቁም እስረኛ ሆኖ እንዲኖር ተደረገ። በወቅቱ መታሰሩ ብቻ ሳይሆን ዳግመኛ ወደዙፋኑ ዝር እንዳይል አይነ ስውር እንዲሆን የተደረገ ሲሆን በመጨረሻም ግልጽ ባልሆነ መንገድ እንዲገደል ተደረገ።
ወንድሟን ለዙፋኑ ካበቃች እና ባለቤቷን ደግሞ ለእቁም እስር፤ ለአይነስውርነት እና ሞት ከዳረገች በኋላ ወይዘሮ ድንቅነሽ በ1873 ወደ መቀሌ ትዛወር እና ራስ ወልደ ኪሮስን አግብታ የንግስና ማእረግ ታገኛለች። ሚኒልክ በ1907 እስከ መጣበት ድረስም በንግስናዋ ከኖረች በኋላ ወዲያው ህይወቷ ሲያልፍ አዲስ አበባ ውስጥ ስርአት ባለው መልኩ የቀብር ስነ ስርአቷ ሊፈጸም ችሏል።
እንግዲህ እነ ሴቭ አድና ይህንን የከረፋ ታሪክ ነው እንድናወድስ ሌት ከቀን የሚወተውቱን!
አበስኩ ገበርኩ