Bete Amhara

Bete Amhara

Tuesday, July 7, 2015

የአማራ ልጆች በፖለቲካ ንቃት ከሁሉም ጭራ ነን

የአማራ ልጆች በፖለቲካ ንቃት ከሁሉም ጭራ ነን

የሃገሬ ወጣት አብዛኛው የፖለቲካ እውቀት የለውም ። መንጋ ነው። መግተልተል ብቻ ። እንደ ጋሬ ፈረስ ከርከች ከረከች ከርከች …ወደፊት ብቻ! ዙሮ አያይም ። ማን እዬነዳው ይሆን ፣ በጎኑ ማን አለ? ስንት ሰው ተሳፍሮበታል?… አያውቅም። ከርከች ከርከች ከርከች…
ይመስለኛል የእኛ ታላላቆች "ያ ትውልድ" ወደኛ ያስተላለፈው የፖለቲካ እውቀት የለም። በቃ እዛው ተጨራረሱ ። የትውልድ ክፍተት ተፈጠረ።
በተለይ የአማራ ልጆች በፖለቲካ ንቃት ከሁሉም ጭራ ነን።ኦሮሞውን ኦነግ ፖለቲካ አቃምሶታል።ትግራይን ህወሓት በደንብ አድርጋ ፖለቲካ ጠምቃቸዋለች። ፖለቲካዊ ጠላታቸው ማን እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቃሉ። ስለዚህ በየጊዜው ወዲህ ወዲያ እንደ ፔንድሎም አይወዛወዙም። የፖለቲካ መርሃቸው ሁልግዜም ያው ነው።አይለወጥም።

እኛ የአማራ ልጆች ግን ፖለቲካ ያስተማረን የለም እና ፖለቲካ አናውቅም። መጀመሪያ ደርግ የፊውዳል ርዝራዥ ብሎ የእኛን ፖለቲከኞች ፈጀ። ቀጠለ በኢሓፓ እና በደርግ ቀይ እና ነጭ ሽብር ጎራ ለይተው ታላላቆቻችን ተጨራረሱ ።የተረፉትን ደግሞ አሲምባ ላይ ሻእቢያ እና ህወሓት ፈጇቸው ። ከዚህ ሁሉ ተርፈው የቆዩትን እንደ ፕሮፌሰር አስራት አይነቶቹን ደግሞ ህወሓት ጨረሰቻቸው ። አማራ ፖለቲከኛ አልባ ሆኖ እጁን አጨብጭቦ ቀረ ። ባዶ!

እናም የምንሄድበትን አናውቀውም ። በሞቀው ዘፋኝ ሆነን ቀረን ።ለህዝቤ ምን ይጠቅመዋል? ብለን ሳይሆን የትግሉን ጩኸት ብቻ ነው የምንከተለው። ሞቅ ያለውን እንከተለዋለን ። አማራ አባል ያልሆነበት የፖለቲካ ድርጅት ያለ አይመስለኝም። ሁሉም ቦታ አለ።ህወሓት ውስጥ ነበረ፣ ኦነግ ውስጥ ፣ ደርግ ፣ኢሃፖ ፣ መኢሶን፣መኢአድ፣አንድነት፣ቅንጅት ፣አዲሃፓ፣ቀስተ ዳመና፣ ሰማያዊ ፣አርበኞች፣ የሽግግር ሸንጎ ፣ግንቦት 7 ፣ ግንቦት 7 አርበኞች ፣ ብአዴን፣ ኦህዴድ … …ሁሉም ቦታ አለ። ይሄ ምን ይባላል ታዲያ? ኦሮሞዎችን ብትመለከቱ ወይ ኦነግ ወይ ኦህዴድ ናቸው ። አለቀ ። ትግሬ ወይ ህወሓት ወይ አረና (በጣም ትንሽ) ።

የአማራን ህዝብ እድል ፈንታ የሚቆርስ ፓርቲ ያስፈልገናል። አማራን ከተኛበት ጭልጥ ያለ ፖለቲካዊ እንቅልፍ አስደንግጦ የሚቀሰቅሰው አካል ያስፍልጋል። የመጀመሪያው ስራ ይሄ ነው። የፖለቲካ ንቃተ ህሊናን ማዳበር ። የትግሉን ወሰን ፣ አላማ እና ግብ በደንብ ማወቅ ። ጠላቶቹን ላይቶ ማስቀመጥ… ……የመሳሰሉት ነገሮች ከሁሉም በፊት ሊገቡን ይገባል!!!