Bete Amhara

Bete Amhara

Friday, July 10, 2015

ወያኔ ያስቀናኛል፤ ኤርትራዎች ያስቀኑኛል፤ ትግሬዎች ያስቀኑኛል፤ ኦሮሞዎች ያስቀኑኛል…

ወያኔ ያስቀናኛል፤ ኤርትራዎች ያስቀኑኛል፤ ትግሬዎች ያስቀኑኛል፤ ኦሮሞዎች ያስቀኑኛል…
----------------------------------------------------------------------------------
በአማራነቴ ሳስበው ብዙ ነገር ያስቀናኛል፡፡ ዛሬ ያሰቡትን ያህል ባይኖሩም ኤርትራዊያን ለራሳቸው ብቻ በማሰብ እና በመተሳሰብ ያደረጉት ትግል፤ አሁንም እርስ በእርስ ያላቸው ትስስር፤ አንድም ኤርትራዊ ሌላ ኤርትራዊ አጠገቡ እያለ ችግር ላይ እነደማይወድቅ ሳስብ ያስቀኑኛል፡፡ ትግሬዎች እርስ በእርስ በመተሳሰብ አንድ ላይ በመሆን ለራሳቸው የሚበጃቸውን ማድረጋቸው፤ በትግሉ ወቅት ትግሬ አባቶች ምስጢር ለማግኘት ሲሉ ድንግል ልጃቸውን እንኳ ለደርግ ጦር አለቆች እየሰጡ መታገላቸው፤ አንድ ትግሬ ለሌላው ትግሬ ሟች መሆኑ፤ ከስኮላርሽፕ እስከ ጽዳት ስራ ድረስ እርስ በእርስ በመደጋገፍ ጥቅማቸውን ማስከበራቸው፤ በጥቅማቸው እና በትግሬነታቸው ላይ ከምንም ነገር ጋር የማይደራደሩ መሆናቸው፤ ሁሉንም ነገር ከትግሬ አንጻር ማየታቸውና ለራሳቸው በሚያመች መንገድ ብቻ ጥቅም ላይ ማዋላቸው ያስቀናኛል፡፡ ኦሮሞዎች ለኦሮሞነታው ብቻ መኖራቸው፤ ሰው ሲታሰርባቸው እና ሲገደልባቸው እንኳ አለም እንዲያውቀው ማድረግ መቻላቸው፤ ለወደፊቱ ይበጃል ያሉትን የኦሮሞ አገርነት በብዙ ነገር አሰናድተው ጨርሰው አንድ ገዳም ቀን እየተጠባበቁ መሆናቸው ያስቀናኛል፡፡
ወያኔ በተለይ ያስቀናኛል፡፡ ይሄ አንድነት በሚል ዜማ መሀል ላይ የቆመው አማራ ገለል ቢል የወያኔ እድሜ ወራት ብቻ የሚበቃው ነበር፡፡ ይህን አማራው አላወቀም፡፡ አማራው እንደሌላው ሁሉ እኔ አማራ ነኝ ብሎ እንደአማራ ማሰብ፤ መናገር እና መስራት የጀመረ እለት የወያኔ ግብአተ መሬት ነበር፡፡ አንድነት የሚል እና በአማራነት አልሰበሰብም የሚል አማራ ያለጥርጥር የወያኔ የእድሜ ማራዘሚያ መሆኑን ሳስበው ያበግነኛል፡፡ አማራው ለራሴ ነው የምኖረው ቢልና በብአዴንነትም ሆነ በሲቪል ሰርቫንትነት ማገልገሉን አስቸጋሪ ቢያደርግበት ለወያኔ ስልጣን ግልጽ ስጋት ነበር፡፡ አማራው አማራ ነኝ ብሎ መነሳቱ ወያኔን ዛሬ በአማራው ላይ የሚያደርሰውን ሰቆቃ አላንዳ ቅድመ ሁኔታ ያቆም ነበር፡፡ የአማራ መነቃቃት እና ለራሱ ማሰብ በቀጥታ ከወያኔ እድሜ ማጠር ጋር የተሳሰረ ነው፡፡ የኦሮሞ እስረኞች ቁጥር አብላጫ እንደሆነ አለም ያወቀላቸውና አንድ ነገር ኮሽ ሲል ቶሎ ትኩረት ማግኘቱ በኦሮሞነታቸው በመደራጀታቸው እና ትስስር በመፍጠራቸው ነው፡፡ የአማራ ግን ራሱ አገዛዙ ያመነው በሚሊዮን የሚቆጠር አማራ ሲሞት እንኳ ለምን ብሎ ጠያቂ የለውም፡፡ አማራው ባለመደራጀቱ እና ለምን ባለማለቱ ደመ ከልብ ሆኖ ቀረ፡፡ አማራ እኔ አማራ ነኝ ባለማለቱ ዛሬ አማራን መግደልና ማሳደድ ህግ ሆነ፡፡ አማራን የገደለ፤ ያሰረ እና ያፈናቀለ ማንም ለህግ አይቀርብም፡፡ ምክንያቱም ለምን ብሎ የሚጠይቅ ሌላ አማራ ባለመኖሩ፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነው አማራው ራሱ አውቆም ሳያውቅ ከአጥፊው ወያኔ ጋር ስለተባበረ ነው፡፡ ወደድንም ጠላንም ወያኔን አቅፎና ደግፎ የያዘው ራሱ አማራው ነው፡፡ አማራው ሙሉ በሙሉ ቢከዳው ወያኔ ይህንን ያህል ባልጨፈረብን እና ዘራችንን እስከማጥፋትም ባልደረሰ ነበር፡፡ ግን እንደአለመታደል ሆኖ አማራው የወያኔ አገልጋይ ነው፡፡ ግማሹ ብአዴን በመሆን የወያኔ ዋልታና ማገር ሆኖ ያገለግላል፡፡ ግማሹ አንድነት በሚል አሮጌ ልክፍት ውስጥ በመንገላወድ የአማራነትን እንቅስቃሴ ያከሽፋል፤ በዛውም የወያኔን እድሜ ያረዝማል፡፡ የተቀረው ደግሞ በግንዛቤ ችግር እና በግዴለሽነት ዝም ብሎ ፈዛዛ ኑሮውን ይቀጥላል፡፡ በዚህም ሳያውቀው የአጥፊውን እድሜ ያራዝማል፡፡
የአማራ ነጻ መንግስት የማቋቋም ፍላጎት ቢያይል ቀድመው የተማጽኖ ጥያቄ የሚያቀርቡት ትግሬዎች ናቸው፤ ኦሮሞውም ይከተላል፡፡ በጣም የሚያሳዝነው የአማራነት መጎልበት እና ለራስ ነጻ መንግስትነት ማሰብ ለአማራ የሚሰጠውን ጥቅም እና ለእነሱ የሚመጣባቸውን ጉዳት ትግሬዎቹ እና ኦሮሞዎቹ በደንብ ተረድተውት ሳለ አማራው ገና ያላወቀው መሆኑ ነው፡፡ የአንድነት አቀንቃኝ አማሮች የአማራውን መነቃቃት እና መደራጀት ቢደግፉት እነሱ ለሚሹት የአገር እንድነትም ፍቱን መድሀኒት መሆኑን አያውቁም፡፡ አሮጌውን ዘዴ በመከለስ ወይም በመቀየር በተለየ ዘዴ አገር አንድ ማድረግ እንደሚቻል እንኳ አይገነዘቡም፡፡ በዚህም የተነሳ ሳያውቁት የወያኔን እድሜ ያራዝማሉ፤ የአማራን ጥፋትም እንዲፋጠን ይተባበራሉ፡፡ ይህም ድርጊታቸው ለወያኔ መልካም ነገር ነው፡፡ ወያኔ ሊሰራ የሚገባውን ስራ እነሱ ይሰሩለታል፡፡ በዚህም ወያኔ ዘና ፈታ ብሎ በአማራው አገልጋይነት እየተንፈላሰሰ አማራን እያጠፋ ይኖራል፡፡ እድልም አብራው ናት፤ እቀናበታለሁ የምለው በዚህ ነው፡፡ አማራ እኔ አማራ ነኝ ብሎ በታሪኩ ለአንድ አመት እንኳ ቢንቀሳቀስ እና ሆ ብሎ ቢነሳ በሁለተኛው አመት የድል ባለቤት ይሆን ነበር፡፡ ስሙና መሰባሰቡ ላይ ያለውን ሀይል ባለማወቁ ከእሱ በሚያንሱ ኮሳሳ ሰዎች ተረግጦ ይማስናል፡፡
አማራ ሆይ የያዝከውን ሀይል እወቀው፤ ተጠቀምበትም፡፡
ድል ለቤተ አማራ