Bete Amhara

Bete Amhara

Friday, July 10, 2015

እውን ሃሜት ትግልን የማስቆም ሃይል አለውን?

እውን ሃሜት ትግልን የማስቆም ሃይል አለውን?
*******************************************
ከእንቅልፋችን ስንነሳ እና ፌስቡክን ዳሰስ ዳሰስ ባደረግን ጊዜ ነገር ነገር የሚሸቱ ጽሁፎች በዙሪያችን ተደርድረው እና እኛም የቡና ቁርስ ሆነን እራሳችንን አገኘነው። አቤት የሃሜቱ ብዛት? ሰው የእናንተ የአንድነት አጀንዳ ይቅርብኝ፤ሃሳባችሁን በግዴታ ልታሳምኑኝ አትሞክሩ፤ ህዝቤን አትንኩብኝ ስላለ ይህ ሁሉ የቡና ቤት ወሬን በአንድ ሰው ላይ መለጠፍ እንዴት ያስጠላል እባካችሁ። ትላንት የተደረገውን የጠፉ የቤተ አማራ በጎችን የማሰባሰብ ስራንም እነ አጅሬ የእውቅና እና የስልጣን ጥም ማርኪያ መንገድ አድርገው መውሰዳቸውን ባየን ጊዜ እጅጉን ተገርምን አፈርን። ለነገሩ ሰው በሃሜት አይሞትም እንጅ እንደ እነ አጅሬ ምኞት ቢሆን ኖሮ እስካሁን ከመቃብር በታች ሆነን ነበር።
ይህን የሚያደርጉት እነማን ናቸው? በጣም ጥቂት በግንቦት ሰባት ስም ቤተ አማራን መዘወር የሚፈልጉ ሰዎች እና አንዴ ቤተ አማራ ሌላ ጊዜ ብአዴን ላይ የሚንጠለጠሉ ድኩማን (ስም መጥቀስ ይቻል ነበር)። ቤተ አማራ ራሱን ችሎ እንጅ የማንም ሎሌ ሆኖ ሊሄድ አይችልም። መርሃችን አንድ ነው። ግንቦት ሰባት ኢትዮጵያን ነጻ አወጣም አላወጣም የቤተ አማራ የነጻ መንግስት ምስረታ እስከ መጨረሻው ይቀጥላል። ከግንቦት ሰባት ጋ የሚያዋድደንም ይሁን የሚያጋጨን ሃሳብ በተአምር የለም። እነሱ ኢትዮጵያን ነጻ ያውጡ እኛ ደግሞ የአማራ ህዝብ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለዘመናት ካሳለፈው ስቃይ የሚገላገልበትን የራሱን መንግስት እንመሰርታለን። በዚህ መሃል ግን በመካከላችን ቢቻል መረዳዳት ያ ሲቀር ደግሞ መከባበር በኖረ ነበር። ነገሩ ግን ወዲህ ነው። መጥለፍ ፤መናቅ፤የራሴን ሃሳብ ብቻ ተቀበሉ፤ እኔን ብቸኛው የኢትዮጵያ ፈውስ አድርጋችሁ ውሰዱኝ ሌላም ሌላም...በአደባባይ ከመስደብ እና ከማስፈራራት አልፎ በውስጥ መስመር የሚያስጠላ ዛቻ ማየት ምን ያህል ጋጠወጥነት እንደሆነ ሊገባኝ አይችልም።
ለማንኛውም ለሰፊው የቤተ አማራ የትግል እንቅስቃሴ ሲባል እና ለጊዜው ቢሆንም የተገኘችውን ትንሿን ሰላም ላለማደፍረስ ሲባል ሆድ ይቻለው ብለናል።
ሃሜቱም ማስፈራራቱም ይቀጥላል! እኛም እስከመጨረሻው ድረስ በአላማችን እንጸናለን።