Bete Amhara

Bete Amhara

Saturday, July 4, 2015

ባለፉት ሀያ አራት አመታት የወያኔ አገዛዝ ዘመን አማራው የተጓዘባቸው ሶስት የትግል መንገዶች

Jalo Jalo እንደጻፈው
ባለፉት ሀያ አራት አመታት የወያኔ አገዛዝ ዘመን አማራው የተጓዘባቸው ሶስት የትግል መንገዶች ባጭሩ እንደሚከተለው አቀርባለሁ።
1. በኢትዮጵያዊነት ስም መታገል፣ 
ባለፉት ሀያ አራት አመታት ወያኔ የብሔር የጎሳ ተኮር ፖለቲካን በማራመድ አገሪቱን ሊበታትን ሲነሳ፣ ከመጀመሪያውኑ ጀምሮ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የወያኔ ተባባሪ በነበረበት ሰአት አማራ ብቻውን ይሄንን ጎሳ ተኮር ፖለቲካ ሲቃወም፣ እና ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያለ ሲጮህ፣ የድሮው ስርአት ናፋቂ፣ ነፍጠኛ ወዘተ የሚሉ ስሞች ሲሰጡት ነበር።
2. በአማራው ስም መደራጀት፣
እሽ በአማራ ስም ሌሎች ብሄረሰቦች እንደሚደራጁት፣ ያወጣችሑት ህገመንግስትም ስለሚፈቅድ አማራውን ከጥፋት የሚታደግ በአማራ ስም ድርጅት ይኑር ብለው ታላቆቻችን እነ መአድን የመሳሰሉትን አማራውን ከጥፋት የሚታደጉ ድርጅቶች ሲቋቋሙና በአማራው ህዝብ ላይ የሚደርሰውን ግፍ አደባባይ ማውጣት ሲጀምሩ በወያኔ የተቀነባብረ ሴራ እንዲፈርሱ ይደረጋል። መስራቾችንም በእስር በማማቀቅ ተገደሉ። እነ ፕር አስራትን የመሳሰሉ ኢትዮጵያውያን አማሮች ተገደሉ።
3. ቤተ አማራን መመስረት:
ሶስተኛው አማራጭ እና የህይወት መስዋዕትነት ለመክፈል የተነሳንበት ቤተ አማራን መመስረት ነው። ይሄም እናንተ ያስቀመጣችሑት አንቀጽ ይፈቅድልናል። ልክ እንደ ኤርትራ የራሳችንን ቤት እንመሰርታለን ብለን ከወዲሁ መንቀሳቀስ ስንጀምር፣ ድሮ ለኢትዮጵያ ጠበቃ በነበርንበት ግዜ እኛን ነፍጠኛ፣ የድሮ ስርአት ናፋቂ ወዘተ እያሉ የሰደቡን አሁን የኢትዮጵያ ጠበቃ ሲሆኑ ማየት ግርምትን ይጭራል። ቤተ አማራን የመመስረት አማራጭ መገፋታችን፣ መገደላችን፣ መፈናቀላችን፣ ወልደን ከብደን፣ በኖርንበትት፣ ባቀናነው ቀየ መንደር፣ አገራችሑ አይደለም እየተባልን በሰለጠነ ዘመን በጸሀይ፣ በግላጭ መባረራችን፣ በክትባት ስም መካን መሆናችን፣ የራስችንን መሬት ሳይቀር በግልጽ፣ በማን አለብንነት ስሜት መቀማታችን፣ መሬታችንን አንለቅም ባልን በጅምላ መረሸናችን፣ ወዘተ በአጠቃላይ ብሶት የወለደው ሀሳብ ነው።
እናንተ ገዢዎቻችን፣ ማንም ጭቆና ሳያደርስባችሑ፣ ደርግ አገሪቱን በተቆጣጠረ ማግስት ብሶት ወለደን ብላችሑ አገር ለመምራት ከደረሳችሑ፣ የእኛ ብሶት የእናንተን አንድ ሚሊዮን እጥፍ ነው። እናንተ በተቆጣጠራችሑት ፓርላማ ሳይቀር እንደ ተሰረቀ እቁብ ሁለት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ህዝብ ጎደለ ብላችሑ ያመናችሑትን እንኳን አስታውሱ። የእናንተ እራሳችሑ ባቀነባበራችሑት ሴራ ሀውዜን ላይ ደርግ የጨፈጨፋቸው አምስት ሺህ ትግሬዎች እረፍት የሚነሷችሑ ከሆነ በግፍ የተገደሉ፣ የተፈናቀሉ ከአምስት ሚሊዮን በላይ አማሮች እንዴት የእናንተን ብዙ እጥፍ እረፍት አያሳጡን??
ቤተ አማራ ከሰላሳ አምስት ሚሊዮን በላይ አማሮችን ጭቆና፣ ግፍ ይዞ የተነሳ ነውና፣ እናንተ እንዳሰባችሑት የሚፈረካከስ እንዳይመስላችሑ። ጉዞ ጀምረናል። እስከ ሞት ድረስ። ሞት ለአማራ የለመድነው ነውና አንፈራም፣ ወደ ሗላም አናፈገፍግም። አንድ ነገር ግን ልንገራችሑ፣ እየገደላችሑንም በእጥፍ እንበዛለን፣ ልታዳክሙን ስትነሱ የበለጠ እንበረታለን።
ድል ለአማራ ህዝብ!!!!
ቪቫ ቤተ አማራ!!!!!!