Bete Amhara

Bete Amhara

Thursday, July 2, 2015

ግብር መክፈልን ከአማራ ክልል ተማሩ

ግብር መክፈልን ከአማራ ክልል ተማሩ
**************************************************************************************
አገር ቤት እያለሁ በኢቲቪ ከሰማኋቸው ዜናዎች መካከል የሚከተለው አንዱ ነበር።
ከደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን የገቢዎች ጽ/ቤት የተወጣጡ ባለሙያዎች በግብር አሰባሰብ ውጤታማነት ላይ የልምድ ተሞክሮ ለመውሰድ ወደ አማራ ክልል የገቢዎች ጽ/ቤት መሄዳቸው ነው። በዜናው ላይ እንዳየሁት ከሆነ ግብር በመሰብሰብ ውጤታማ ከሆኑ ክልሎች (የከተማ አስተዳደሮችን አይጨምርም ምክንያቱም አዲስአበባ አንደኛ ነው) አማራ ክልል ግንባር ቀደሙ ነው። ስለሆነም የክልሉ የገቢዎች ጽ/ቤት እንዴት እዚህ ውጤት ላይ ሊደርስ እንደቻለ እና ምን አይነት ተሞክሮ ለሌሎች ክልሎች ሊያካፍል እንደሚችል የሚያትት ዜና ሲሆን ከጉራጌ ዞን የመጡ ባለሙያዎችም በጎበኙት የግብር አሰባሰብ ዘዴ እጅጉን መደነቃቸውን እና ወደ ዞናቸው ሲመለሱ ይህን መልካም ተሞክሮ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚንቀሳቀሱ ዜናው ጨምሮ ይገልጻል።
ከዚህ በተጨማሪም የምታስታውሱ ከሆነ አልበገር ባዩ የቤተ አማራ ወንድማችን ጎንደርጎጃም ወሎሸዋ አንድ ነን ባለፈው እንደነገረን ከሆነ አማራ ክልል ወሊድን በመከላከል (ማምከንንም ይጨምራል) በሃገሪቱ ግንባር ቀደሙ ክልል ሆኖ ተሸልሟል።
እና ምን ለማየት ፈልጌ መሰላችሁ፤ አይናችንን ከከፈትን ከነዚህ ሁለት ጥሬ ሃቆች ብዙ የምንማረው እውነታ አለ። የወያኔ የረጅም ግዜ ስትራቴጂ ሆዳም አመራሮችን ዛሬ በሽልማት እያንበሸበሸ የአማራን ህዝብ ቁጥር በወሊድ መከላከል ሰበብ በመቀነስ እና በከፍተኛ ግብር ራቁቱን በማስቀረት አማራ የሚባል ህዝብ በኢትዮጵያ ምድር እንዳያንሰራራ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ቅስሙን መስበር ነው። ምንም እንኳ በኢንቨስትመንት ከትግራይ እና ኦሮሚያ የትናየት ርቆ ቢገኝም በግብር መክፈል ግን ግንባር ቀደም ተብሎ ተሸልሟል። እንግዲህ ይህ በኢትዮጵያ ውስጥ ቁጥር አንድ ግብር ከፋይ ህዝብ ነው ዛሬ ከአፍሪካም ከአለምም the poorest region ሆኖ የተገኝው።
ጎበዝ ጨርሰን ከመጥፋታችን በፊት ብንነቃ መልካም ይመስለኛል!!!
ጆን_ከቤተ አማራ