Bete Amhara

Bete Amhara

Wednesday, July 8, 2015

በጣም ተከፋሁ

በጣም ተከፋሁ
በጣም የተከፋሁበት ቀን ነው፡፡ የካቲት አምስት ቀን 2007 ዓ. ም ነበር እንደዚህ የተከፋሁት፡፡ ስለራሴ አይደለም፡፡ ምንም በማያውቀው የአማራ ህዝብ ላይ በሚወርድበት መአት እንጅ፡፡ ማዘኔን መናገሬ ነውር ሊመስል ይችላል፡፡ ግን አንዳንድ ወንድምና እህቶቸ ትረዱኝ ይሆናል፡፡ የምጽፈውም የራሴ የብቻየ ጉዳይ እንጅ የቤተ አማራ ጉዳይ አይደለም፡፡ እኔ ለአማራ ህዝብ ምንም ያልሰራሁ ሰው ነኝ፡፡ ግን የአማራን ችግር የዛሬ ሽህ አመት እንኳ ተመልሶ በማይመጣበት ሁኔታ ነው መፍታት የምፈልገው፡፡ እኔ በግሌ የአማራ ህዝብ ችግር በመንግስት ለውጥ ብቻ ይፈታል የሚል እምነት የለኝም፡፡ ከወያኔ ውድቀት በኋላ እንኳ ህዝቡን የሚጠብቀው ጥፋት እጅግ ያሳስበኛል፡፡ የህዝቡን የጠላት ብዛት እና አይነት ሳሰላው በጣም አዘንኩ፡፡

ዝም አይባል ነገር ችግር፡፡ በጣም የሚገርመኝ ግን ስለአማራ መጻፋችንን ሁሉም መቃወሙ ነው፡፡ ወያኔው፤ አንድነቱ፤ ኦሮሞው፤ አማራው….ሁሉም ተቃወመ፡፡ ምክንያቱ ግልጽ ነው፡፡ ይህም ለአማራ የሚያስብለት በጣም ትንሽ ሰው መሆኑን ነው የሚያመለክተው፡፡ አማራ ብሎ መናገርና መጻፍ ነውር የሆነበት ምክንያት ብዙ ነው፡፡ ከዚህም በመነሳት እኛን አፍ ለማዘጋት ያልተሞከረ ነገር የለም፡፡ መጀመሪያ ምርጫ አስቀያሽ ተባልን፡፡ ቀጥሎ የሳምንት ወሬ ነው አሁን ይተውታል ተባልን፡፡ ከዛ ወያኔ በገንዘብ የቀጠራቸው ተባልን፡፡ ከዛ ሻእብያ ናቸው ተባልን፡፡ ከዛ ኦነግ ናቸው ተባልን፡፡ ቅዠታሞች ተባልን፡፡ ዘረኞችም ተባልን፡፡ ከዛ ድጋሜ ወያኔ ናቸው ተባልን፡፡

ይህ ሁሉ ችግር አልነበረበትም፡፡ በግሌ ለአማራ እንደወያኔ አይነት ክፉና ጨካኝ ጠላት ይኖራል ብየ አልገምትም፡፡ ከዚህ በፊትም መኖሩ ያጠራጥራል፡፡ ወያኔን የምጠላውን ያህል ምንም ነገር አልጠላም፡፡ ከወያኔ በላይ አስጸያፊ ነገር አለ ብየ አስቤ አላውቅም፡፡ የሚያሳዝነው ግን ያንን የምጸየፈውን ስድብ አሁን መሸከሜ ነው፡፡ ዞሮ ዞሮ በጣም ያሳዘነኝ ነገር ይህ ነው፡፡ የአማራን ጠላት ቆጠርኩት እና አዘንኩ፡፡

1) አማራው ስለአማራ በቂ ግንዛቤ ማጣት
2) አማራ ያልሆኑት ለአማራ ያላቸው ጥላቻ
3) አማራው ራሱ የወጣበትን ማህበረሰብ ተመልሶ የማያይ መሆኑ፡፡ ይህ አጼዎችን ይጨምራል፡፡ ከነገስታቱ ጀምሮ ለራሳቸው ህዝብ የማያስቡ መሆናቸው እና ተማርኩ የሚለው ወደወገኑ ተመልሶ ስለማያይ ህዝባችን የአለም የመጨረሻው ጎስቋላ ህዝብ ሆነ፡፡ ሊጠፋ ሲፈረድበትም የሚደንቀው ሰው ጠፋ፡፡
4) ጽንፈኛ ጠባብ የብሄር ድርጅቶች ያደረጉት፤ የሚያደርጉት እና ሊያደርጉት እየተዘጋጁበት ያለው ክፉ ነገር፡፡
5) አማራው ራሱ ሁልጊዜ እንደማየው በወቅታዊ ዜና ነፋስ መወሰድ እንጅ ቆም ብሎ ተረጋግቶ ማሰብ እና ዘላቂ መፍትሄ መትከል አለመቻሉ፡፡
6) ወያኔ እና አማራው ላይ እያደረሰ ያለው ጥፋት፡፡
7) በወያኔ ስር የተኮለኮሉ የየብሐየረሰቡ ወኪሎች
አማራው ላይ ያላቸው ጥላቻ እና የሚያደርጉት ክፋት
8) ለአማራ የሚታገልም ሆነ የሚናገርለት አንድም ድርጅት አለመኖሩ እና ከዚህም የተነሳ የተፈጸመበት የዘር መጥፋት ሁሉ አለምም ሳያውቀው ጆሮ ዳባ ልበስ ተብሎ መቅረቱ፡፡ ይህም አሁን ለሚፈጸሙት እና ወደፊት ለታቀዱት የዘር ማጥፈት ድርጊቶች እና እቅዶች ድልድይ መሆኑ፡፡
9) አማራው አማራ ነኝ ብሎ በአንድነት እስካልተነሳ ድረስ ጠብ የሚል ስራ የማይሰራ መሆኑን አለመገንዘቡ፡፡
10) አማራው በአጉል ምክንያታዊነት እና ግብዝነት ህዝቡ ላይ የተደቀነውን ከባድ አደጋ አቅልሎ ማየቱ
11) አማራው እርስ በእርስ የማይግባባ እና በቶሎ ለመወንጀል መሽቀዳደሙ
12) ከአድዋ ድል ጋር ተያይዞ በአማራው ላይ ጥርስ የነከሱ እና በእጅ አዙር የሚያጠቁት አለማቀፋዊ ጠላቶች እንዳሉት በበቂ ሁኔታ አለመገንዘቡ፡፡
13) በታሪክ የገጠሙት እንደ ቱርክ አገዝ የግራኝ ጦርነት፤ የዮዲት ጉዲት ጦርነት፤ የደርቡሽ ጦርነት፤ የጣልያን ጦርነት፤ የኦሮሞ ወረራ የመሳሰሉት አማራን በታሪክ ያወደሙ ጥፋቶች ከዚህ በኋላ ተመልሰው አለመምጣታቸው ማረጋገጫ አለመኖሩ እና ሌላው ነገር በጣም አሳሰበኝ፡፡

ብዙ ብጽፍ ደስ ባለኝ፡፡ ግን ነገር ቢበዛ…ብየ ተውኩት፡፡
መለክ ሃራ!