Bete Amhara

Bete Amhara

Wednesday, July 8, 2015

ስለ መላው አማራ ከጎጃም ሁለት ምሳሌዎች

ስለ መላው አማራ ከጎጃም ሁለት ምሳሌዎች

በመጀመሪያ ጎጃም ምድር ሂድ፡፡ ምግብ ቤት ግባ፡፡ እዘዝ፡፡ ወጥተህ እጅ ማስታጠቢያ ላይ ለመታጠብ ድካም ነገር አዩብህ እንበል፡፡ በጆግ ያመጡልህና ያስታጥቡሀል፡፡ ከዛም የሚቀርብልህን ምግብ ታያለህ፡፡ ከዛም ትቀምሳለህ፡፡ ከዛም ጠግበህ ትበላለህ፡፡ መጥገብ ብቻ አይደለም፡፡ ታስተርፋለህ፡፡ ስታበቃም “ሂሳብ ስንት ነው?” ትላለህ፡፡ ይነገርሀል፡፡ ከዛ ግራ ይገባህና “እንዴት ሊሆን ይችላል? ይሄን ሁሉ እንዲህ የሚጣፍጥ ምግብ በልቸ ይህችን ብቻ እንዴት እከፍላለሁ?” ትላለህ፡፡ ተሳስተው ነውም ብለህ ታስባለህ፡፡ ባስ ሲልም ሳታስበው ሰርቀህ የበላህ ሁሉ ሊመስልህ ይችላል፡፡ ከዛም በድገጋሜ “እንዴት ሊሆን ይችላል” ብለሀ ትጠይቃለህ፡፡ “አይዋ እንደዛ ነው፤ አልተሳሳተክም” ትባላለህ፡፡ ከዛም “እነዚህ ሰዎች ለጽድቅ ነው ወይስ ለስጋቸው ነው ሆቴል ከፍተው ምግብ የሚሸጡት?” ብለህ ራስህን ትጠይቃለህ፡፡ በመጨረሻም ከእናትህ ቤት እንደተጋበዝክ ቆጥረኸው እያመሰገንክ ትሄዳለህ፡፡ አይገርምም ግን? አይ አይ አይገርምም፡፡ ይህ የጎጃም ልማዳዊ አኗኗር ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ይሄ እከክ የሆነ አገዛዝ ነገሮችን እየለዋወጣቸው ነው በእርግጥ፡፡ ይሁንና የጻፍኩት ነገር ከሞላ ጎደል አሁንም አለ፡፡

ጎጃም ውስጥ ማደር ፈለግክ እንበል፡፡ መኝታ ቤት ትከራያለህ፡፡ ከዛ የመኝታ ቤትህን ቁልፍ ስጡኝ ትላለህ፡፡ ይሰጡሀል፡፡ ከዛም ውድ እቃዎች ይዘህ ከሆነ “የት ላስቀምጥ?” ትላለህ፡፡ “መኝታ ቤትህ ውስጥ አስቀምጠው” ትባላለህ፡፡ ግራ ገብቶህ “እእ ሌ…...” ብለህ ሳትጨርስ “ዋ ያንተን ማን ይነካልሀል” ትባላለህ፡፡ ጎጃም ላይ ንብረትህን “ማን ይነካብሀል” አይደለም የምትባለው “ማን ይነካልሀል” እንጅ፡፡ በ “ማንም አይነካብህም” እና በ “ማን ይነካልሀል” መካከል ልዩነት አለ፡፡ እየቆየህ ስትሄድ ሌባ የሚባለውን ነገር ከአእምሮ ታጣዋለህ፡፡ ከዛም ያኔ ተሳስቸ ነበር ትላለህ፡፡

ጎጃምን ለምሳሌ ያህል አነሳሁ እንጅ እያንዳንዷን የአማራ ምድር አውቃታለሁ፡፡ የህዝቡ ደግነትና ጨዋነት ከአንዲት እናት የተወለደ እና አንዲት ደግ እናት “ሁላችሁም እንዲህ አድርጉ” ብላ የመከረቸው ነው የሚመስለው፡፡ በእርግጥም አማራ በጠቅላላው የአንዲት እናት ልጅ፤ አንዲት እናት ኩሩና ክብር እንዲሁም ስንስርአትና ጨዋነት ያለው ሰው መሆንን በአንድ ቃል ያስተማረቸው ህዝብ ነው፡፡ ግን ይሄን ደግ ህዝቤን በክፉ ሲያነሱብኝ ቃላት ሊገልጸው የማይችል የእልህ ሲቃ ይተናነቀኛል፡፡ ስለ አማራ በሌላ ክልሎች እንዲወራ የሚደረገው ጥላቻ እዚህ ምድራችን ላይ በእርግጥ የለም፡፡ የቅንነትና የትህትናችን እንዲሁም ልግስናችን ስራ ነው ተገልብጦ አማራ “ጨቋኝ፤ ነፍጠኛ” የምንባለው፡፡ ጊዜ የሰጠው ቅል ይሰብራል ነው፡፡ ለማንኛውም እኔ አማራ ነኝ፡፡ በጎኔትን እና ደግነቴን አውቀዋለሁ፡፡ እነሱ ስለክፉነቴ እና ጨቋኝነቴ ያውሩ፡፡ አንድ ቀን በምድር ያፍሩበታል ወይም በሰማይ ቤት ይጠየቁበታል፡፡ ህዝቤን አውቅሀለሁ፡፡ ስለደግነትና ቅንነትህም ድምጼን ከፍ አድርጌ አመሰግንሀለሁ፡፡ እናገርልህመ አለሁ፡፡
ጎጃም ቤተ አማራ
ሐምሌ ማርያም ድረስ ይታያል ክምሩ
ጎጃምን የሚያህል እስኪ አገር መርምሩ

የጎጃም ሳምንት ዛሬ ተጀምሯል፡፡ ሳምንቱን ሙሉ ይቀጥላል፡፡ ምርጫ ጋር ግንኙነት የለውም፡፡ የአማራን ነገር ለመስማት ምርጫ ምናምን ብሎ አይሰራም፡፡ ምርጫ ለማስቀየስ ምናምን የሚባለው ውሀ አይቋጥርም፡፡ ጦርነት የሚደረግ ከሆነ ንገሩን፡፡ ምርጫ ተጭብርብሯል አልተጭበረበረም ለሚል ጉንጭ ክርክር የምናጠፋው ጊዜ የለንም፡፡ እኛ ጎጃም ይበልጥብናል፡፡ ጎንደር ደግሶ እየጠበቀን ነው፡፡ ወደ ጎንደር ለመድረስ እንቸኩላለን፡፡ ምናልባት በምርጫው ምክንያት ትኩረት የማይሰጠው ቢሆን እንኳ ግድ የልም ገና እየጀመርን እንጅ እየጨረስን አይደለም፡፡ ገና የአማራ ብሔረተኝነት ጣሪያ እስኪነካ ድረስ በዙር ይቀጥላል፡፡
መልካም ሳምንት! ግፋ በለው ጎጃም
ጎጃም ቤተ አማራ