Bete Amhara

Bete Amhara

Friday, July 10, 2015

የአማራ መሬት ቁራጭ ስትሆን የትግራይ ድንጋይ አብቃይ መሬት ግን ሉአላዊት ናት

የአማራ መሬት ቁራጭ ስትሆን የትግራይ ድንጋይ አብቃይ መሬት ግን ሉአላዊት ናት
በነገራችን ላይ ለወያኔ የኢትዮጵያ ሉአላዊነት ማለት በተግባር የትግራይ ሉአላዊነት ማለት ነው፡፡ ባደመ የተባለ ድንጋይ አብቃይ በረሀ በኤርትራ ተወረረ ሲባል ሉአላዊነት ተገሰሰ ተብሎ ራሳቸው ባመኑት 70 000 ሰው ተሰዋበት፡፡ የአማራ ምን የመሰለ ለም መሬት ለሱዳን ሲሰጥ ግን ለቁራጭ መሬት ጦርነት አንገጥምም ተባለ፡፡ ሌላውን ሁሉ እንርሳው እና በዚህ ብቻ አማራ በሉአላዊ ግዛት ስር እንዳልሆነ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ እስካሁን ወደትግራይ የተጠቃለለ መሬት እንጅ ከትግራይ የተወሰደ መሬት የለም፡፡ በህግ የተወሰነን እና ራሳቸው አጨብጭበው የፈረሙትን የኤርትራ መሬት ሁሉ በጉልበት ቀምተው መያዛቸውን ልብ ይሏል፡፡ በተቃራኒው እስካሁን ከአማራ ወደትግራይ የተወሰዱ መሬቶችን፤ ለሱዳን የተሰጡ መሬቶችን፤ ከጎጃም የተወሰደውን የመተከል አውራጃ ክፍል የአሁኑንን ጉምዝን፤ ከወሎ የተወሰዱትን መሬቶች፤ ከሸዋ የተወሰዱትን መሬቶች ስናይ ያለ ምንም ጥርጥር አማራ በሉአላዊ መንግስት ስር አለመሆኑን እንረዳለን፡፡ ከዚህም ተነስተን ይህ አገዛዝ የአማራ ጠላት አስተዳር እንጅ “መንግስት” አይደለም እንላለን፡፡ የአማራን መሬት ለራስ እና ለጎረቤት አገር መሸለም የቁራጭ መሬት ጉዳይ ነው፡፡ የሉአላዊነት ጉዳይ አይደለም፡፡ እስካሁን የተደረጉ ነገሮችን ስንመለከት በአማራ አገር ሀብት ለትግራይ መደራደር ነው፡፡ ለምሳሌ ለሱዳን የተሰጠው መሬት ሱዳንን መያዣ ነው፡፡ አንድ በዛ አካባቢ አማጹ እንዳይንቀሳቀስ እና ወያኔን ከስልጣን አባርሮ ወደትግራይ የተወሰደውን እና የሚወሰደውን መሬት እንዳያስመልስ፤ ሁለት ለአማራ በዚህ በተሰጠው መሬት ሳቢያ የዘላለም ጠላት መግዛት እና የትግራይ ሪፑብሊክነት የሚታወጅ ከሆን አማራ በሁሉም ቦታ ጦርነት ውስጥ እንዲገባና ተዳክሞ እነሱን እንዳይጠይቃቸው ለማድረግ፤ ሶስት የተሰጠው መሬት ለም ስለሆነ የአማራን የኢኮኖሚ አቅም ለማዳከም፤ አራት ምናልባት አሁን ሱዳ ድንበር የሚገደበው የአባይ ግድብን ለሱዳን እንደመደራደሪያ በማድረግ አሁን ለሱዳን የተሠጠውን መሬት መልሶ በትግራይ ስር ማድረግ እና ትግራይን እስከወለጋ ድረስ ማስረዘም ሊሆን ይችላል፡፡ ሌሎችንም የልማት እና መሰል እንቅስቃሴዎችን ልብ ብሎ በማጤን የዚህ አገዛዝ ዋና ስራ አማራን ማደህየት እንደሆነ ሊረዳው ይችላል፡፡ እንዘረጋዋለን የሚሉትን የባቡር ሀዲድ መዳረሻ ማየት ምን ያህል አማራን ከጨዋታ ውጭ የሚደርግ እንደሆነ መገንዘብ ይችላል፡፡ የፋብሪካና ሌላው ጉዳይም ታሳቢ ይደረግ፡፡