እንኳን ደስ አለን፡፡ www.beteamhara.org እንዲህ አምሮ አየር ላይ ዋለ፡፡ ይህ ከፌስቡክ ቀጥሎ የደረስንበት የአማራ ህዝብ ብቸኛ ነጻ መገናኛ ነው፡፡ ነገ ደግሞ ሌላ መገናኛ ይኖረናል፡፡ ከእንግዲህ ስለአማራ ማናቸውም ነገር በዚህ ገበያ ላይ ይውላል፡፡ ማንም ሰው በአማራ ጉዳይ ማናቸውንም መረጃ ማሳተም ከፈለገ መድረኩን ይሔው ብለናል፡፡ ይህ እንዲሆን የገንዘብ ወጭውን የሸፈናችሁትን የቤተ አማራ ልጆች በአማራ ህዝብ ስም ልናመሰግን እንወዳለን፡፡ የተለየ ምስጋና የሚገባው ደግሞ ይህንን ድረ ገጽ የፈጠረው @Enkokow Gojje ነው፡፡ እንቆቆው ጎጀን ከልብ እናመሰግነዋለን፡፡ Make a Donation የሚለው ለጊዜው አገልግሎት እንዲሰጥ አላደረግነውም እና ወደዛ መግባት አያስፈልግም፡፡ ገና እየጀመርን ስለሆነ ብዙ መረጃ የለውም፡፡ በማንኛውም የአማራ ጉዳይ የሚላኩ ጽሁፎች እና መረጃዎች በቅርቡ የሚሞሉበት የአማራ የሳይበር ቤተ መዝገብ ነው፡፡
በድጋሜ እንኳን ደስ አለን!
ቤተ አማራ ወደፊት!
በድጋሜ እንኳን ደስ አለን!
ቤተ አማራ ወደፊት!