Bete Amhara

Bete Amhara

Wednesday, July 8, 2015

ግንቦት ሰባት ጌታ ነው

ግንቦት ሰባት ጌታ ነው
**********************************************************************************************
ሳልወድ በግድ የግንቦት ሰባት ተቃዋሚ ልሆን ችያለሁ።
*ምክንያት*
አማራ አማራ ስላልኩ ዛሬ ከፍተኛ ጦርነት፤ስድብ ፤ ዘለፋ እና ማስፈራሪያ ከግንቦት ሰባቶች እና ከአንዳንድ ወላዋይ ቤተአማራዎች ተከፍቶብኛል። የብሎኩ ብዛት የትየለሌ ነው (ጥርግ በሉ እንኳን እናንተ ሃምሌ እና ነሃሴም ሄዷል smile emoticon ) ዛሬ በፌስቡክ እንዲህ አምባገነንነቱ ፈጦ ከታየ ነገ ስልጣን የሚይዘው አካል የሃሳብ ልዩነት ማስተናገዱንም እንጃ ። እነዚህ ሰዎች በኢትዮጵያዊነት ጭምብል ዛሬም ህዝቤን ሊበድሉ ይፍልጋሉ። በእኛ ሞት ዛሬም አሮጊት ኢትዮጵያን መልሰው ሊገነቧት ይፈልጋሉ። እስኪ ከሁሉም በላይ አንድ ጥያቄ ልጠይቅ? እውን ግንቦት ሰባት ህብረ ብሄራዊ የፖለቲካ ድርጅት ነውን?

እና ድርጅቱ ኢትዮጵያዊ መልክ እና ቁመና ካለው ለምን የአማራ ልጅ ብቻ እንዲሞት ተፈረደበት? ለምን ትላንት ደርግን ለመጣል ሲሞቱ የነበሩ የአብራኬ ክፋዮች ግን ደግሞ አመድ አፋሾች ዛሬም ብቻቸውን ወደ መቃብር እንዲወርዱ ተፈረደባቸው? እስኪ ማነው በግንቦት ሰባት ውስጥ ምን ያህል የኦሮሞ ታጋዮች እንዳሉ የሚነግረኝ? መቼ ነው የትግራይ ተወላጅ በግንቦት ሰባት አባልነት ተጠርጥሮ ቃሊቲ የሚወርደው? ትላንት እስክንድር ዛሬ ኢየሩሳሌም አማረ - ሁሉም የአማራ እንቁ ልጆች ናቸው ያልኖሩትን ህይወት እየገበሩ ያሉት። በቃ ትላንትም ዛሬም ነገም በስም አንድ ነገር ግን በግብር የሌለች ኢትዮጵያን ለመመስረት ዘላለም አማራ መስዋእት የሚሆንበት ምክንያት ምን ያህል እድለ ቢስ ዘሮች እንደሆንን ነው የሚያሳየው። ሁሌም የምንታገለው እኛ ፤የምንሞተው እኛ።

የጦርነት ፊሽካ ተነፋ ተብሎ አዳሜ በደስታ ሰክሯል፤ ምስኪኑ የጎንደር ገበሬ ግን በባዶ ሆዱ ይሞታል ፤ ልጆቹን ይገብራል። ንብረቱ ይቃጠልበታል። የእኛ ምስኪን ህዝብ በጦርነት ሲለበለብ በሌላው የኢትዮጵያ ክፍል የሚገኝ አባወራ ቁጭ ብሎ ምድጃ ስር እሳት ይሞቃል።

እኛ አማራዎች መሞት ካለብን ለህዝባችን እና ለነጻው የቤተ አማራ መንግስታችን እንጅ ለቅራቅቦው (ጉራጌን አይጨምርም) ሁሉ መሆን የለበትም። የትላንቱ በቅቶን ዛሬ ልንማር ግድ ነው። የእለት ጉርሱን መብላት ያቃተው ህዝባችን እየተሰደደ፤ እየተገደለ ሌላው የቡና ወሬ የሚያደርግበት ምክንያት አይገባኝም። ከዚህ በኋላ አማራ የምትባል ፍጡር ሁሉ መደገፍ እና ከጎን ማሰለፍ ካለብህ ሞረሽ ወገኔ እና የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይሎች ግንባርን እንዲሁም አዲሱን የቤተ አማራ የፖለቲካ እንቅስቃሴ እንጅ በአንድነት ሰበብ ህይወትህን እና ገንዘብህን ለሚያስገብሩት መሆን የለበትም ።

አለበለዚያ የፕሮፌሰር አስራት ወጪት ሰባሪ ሆነን እንቀራለን!

*ሁለት ማሳሰቢያዎች*
1. ይህ ሙሉ በሙሉ የእኔ አቋም እንጂ ማንንም አይወክልም።
2. በጦር ሜዳ ነፍሳችሁን ለገበራችሁ የተሰማኝን ጥልቅ ሃዘን እንዲሁም ለመገበር ለተነሳችሁ የአጥንቴ ክፋይ የአማራ ልጆች ያለኝን አድናቆት ለመግለጽ እፈልጋለሁ።

ጆን - ከቤተ አማራ