Bete Amhara

Bete Amhara

Saturday, July 4, 2015

አንዳንድ ሰው በጥቂት ደቂቃዎች የማይጠፋ አሻራ ጥሎባችሁ ያልፋል

አንዳንድ ሰው በጥቂት ደቂቃዎች የማይጠፋ አሻራ ጥሎባችሁ ያልፋል
********************************************************
እንደዛሬው አማራ ሆ ብሎ ለአማራነቱ ከመቆሙ በፊት ጥቂት ሰዎች ወገናቸውን ለማንቃት ይባትቱ ነበር፡፡ ጣና ላይ እንደተደፋ አንድ ፍንጃል አረቄ ማለት ነበሩ፡፡ ከነዛ ሰዎች አንዱን ዛሬ አዋራሁት፡፡ “ድሮ ድሮማ” አለ ይህ ብርቱ አስቀድሞ የነቃ አማራ “ድሮ ድሮማ አንድ ሰው አማራ የሚል ቃል ጽሁፉ ውስጥ ካስገባ አምስት መቶ ስድብ ነበር በኢንቦክስ የሚደርሰው፤ እኔ ራሴ ስንቴ ተሰድቤያለሁ መሰለህ!”፡፡ አሁን ግን በጣም ደስተኛ እነደሆነ አጫውቶኛል፡፡ ብዙ ጠቃሚ ነገሮችም መክሮኛል፡፡ አንዳዶቹ አስተሳሰቤን የመቀየር አቅም ያላቸው ናቸው፡፡ የነገረኝን አንዳድ ነገሮች እና እኔም ሙሉ በሙሉ ያመንኩባቸውን ላካፍላችሁ፡፡
አማራ ለአማራ ጠላቱ አይደለም፡፡ ሁለት አማሮች ባይግባቡ እና እርስ በእርስ ቢቀዋወሙ ችግሩ የአካል ሳይሆን የአስተሳሰብ ነው፡፡ የአስተሳሰብ ልዩነት በአስተሳሰብ ነው የሚመታው፡፡ ራሱ አማራው ወገናችን ላይ የአካል ጥቃት ማድረስ ፈጽሞ የለብንም፡፡ የትም ይኑር የት አማራ አማራ ነው፡፡ በየትኛውም ጎራ ይሰለፍ አማራ አማራ ነው፡፡ ወንድምና እህታችን ነው፡፡ የመጨረሻ እጣ ፋንታችንም አማራነት ነው፡፡ አንድ እድልና ፋንታ ነው ያለን፡፡ ዛሬ የሚቃወመን አማራ ጠላታችን አይደለም፡፡ የሚቃወመን በግንዛቤ ችግር፤ አማራ የገጠመውን ችግር በቅጡ ስላልተረዳው ነው እንጅ ሲረዳው ከጎናችን ነው የሚቆመው፡፡ አማራ ላይ እንዴያው የከፋ ጥቃት እያደረሱ የሚያውኩት ላይ ካልሆነ በቀር ፈጽሞ አካላዊ ጥቃት ማድረስ አይገባም፡፡ ነገ አብሮን የሚቆመው ወንድም ላይ ዛሬ ጥቃት ማድረስ ፈጽሞ ተገቢ አይደለም፡፡ የምንታገለው አሁን ላለው አማራ ብቻ ሳይሆን ገና ለሚወለደው አማራ ሁሉ ነው፡፡ አማራን አሁን መግደል ማለት የአማራን ቁጥር ማሳነሰ ማለት ነው፡፡ ጨዋታው ደግሞ የቁጥር ነው፡፡ የቁጥር የበላይነት ተወስዶብን ከጨዋታ ውጭ እንዳንሆን ማንም አማራ ተቃዋሚውን እንደጠላት መመልከት የለበትም፡፡ ምንም ይሁን ምን ለአማራ ከሩቅ ወዳጅ ይልቅ ተቃዋሚ አማራ ይሻለዋል፡፡ የምንታገልለትም ለሚቃወመን አማራ ሁሉ ነው፡፡
አማራው ከፕሮፌሰር እስከ እረኛ ድረስ ወያኔን በግልጽ ወራሪ እስከሚለው ድረስ በርትተን እንስራ፡፡ አማራ ላይ እየደረሰ ያለው ችግር በፈጣሪ የመጣ ሳይሆን የወያኔ እጅ እንዳለበት ሁሉም አማራ እስከሚያውቅ ድረስ ማንቃት አለብን፡፡ የአማራ ትልቁ ችግር ራሱ ወያኔ መሆኑን እያንዳንዱ አማራ ማወቅ አለበት፡፡ አማራው በአንድ ላይ ከተሰባሰበ የሚደፍረው ምንም አይነት ምድራዊ ሀይል አይኖርም፡፡ የአማራ መሰባሰብና መደራጀት ትክክለኛው እና ብቸኛው መፍትሔ ነው፡፡ ዋናው ትግላችን አማራውን አማራ ማድረግ ነው መሆን ያለበት፡፡ ተቃዋሚም ሆነ ደጋፊያችን የምንነግረው ነገር ይገባዋል፡፡ ምክንያቱም እየነገርነው ያለው በአማርኛ እና በአማራኛ ነውና፡፡ ሰፊውና ጠቅላይ የሆነው አመከለካከታችን እንድንጠፋ ነው ያደረገን፡፡ እንደሚታወቀው የአማራ አመለካከት ኢትዮጵያ ብቻ ውስጥ ያሉትን ብሔረሰቦች ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ አካባቢ ያሉትን ሁሉ ወንድሞቸ ብሎ የሚምን ነው፡፡ ይህ ግን አደጋ ውስጥ ነው የጣለን፡፡ ስለዚህ አማራው እንዲተርፍ የግድ ይህን አመለካከቱን ቀይሮ ወደአማራነቱ እዲመለስ ያስፈልጋል፡፡
ብርቱው አማራ በትንሽ ደቂቃዎች እንዲህ ብሎ አስተማረኝ፡፡ ሌላም የማልጽፈው ብዙ ቁም ነገር ነገረኝ፡፡
አማራነት ወደፊት!