Bete Amhara

Bete Amhara

Sunday, July 19, 2015

ሌተናል ጀኔራል ሃይሉ ከበደ (በኢትዩጵያ ታሪክ ዉስጥ የመጀመሪያዉ ሌተናል ጀኔራል)

ሌተናል ጀኔራል ሃይሉ ከበደ (በኢትዩጵያ ታሪክ ዉስጥ የመጀመሪያዉ ሌተናል ጀኔራል)
........................................................................(በአሹ ዋሴ የቀረበ)
ሌተናል ጀኔራል ሃይሉ ከበደ
ዋግ ሹም ጓንጉል የንግስና ዘመናቸዉ 1894-1905 ነበር፡ እርሳቸዉ በተሸሙበት ወቅት የአድዋ ጦርነት በመካሄዱ ጀግናዉን የዋግን ህዝብ ጦር በመምራት ታላቅ ጀብድ ፈፅመዋል ፡፡ዋግ ሹም ጓንጉል ብሩ ይመሩት የነበረዉ የዋግ ጦርም በአድዋዉ ጦርነት ጊዜ ከ 400 የሚበልጡ ጣሊያኖችን እንደማረከ ታሪክ ይናገራል፡፡ዋግ ሹም ጓንጉል ብሩ የጦር ሜዳ ጀግና መሆናቸዉ ከመታወቁም ሌላ በአስተዳደርም ዝነኛ ፍርድ አዋቂ እንደነበሩ ይነገርላቸዋል፡፡የእራስቸዉን ታሪክ የሚያዉቁ አባቶች እንደሚሉት (አንድ ግዜ ለዋግ ሹሞች ከየገበሬዉ እየተመለመለ የሚወሰደዉን ከ 10 አንድ ፍየል ሙክት ለመመልመል ተልከዉ የሄዱ መልክተኞች መምጣታቸዉን አስቀድሞ የሰማ ሃብታም ገበሬ‹ የሰቡ ሙክቶችን መርጦ ዋሻ ዉስጥ በመደበቅ የከሱትን ብቻ አቅርቦ አሳየ፡፡ በዚህም ግዜ ጠቋሚ በዋሻ የደበቃቸዉን አንድ ሺ ያህል ሙክቶች ስለ አስያዘበት በሙሉ እንዲወረስ ተደረገ፡፡

ይሁን እንጅ ገበሬዉ ለዋግ ሹም ጓንጉል አቤት ለማለት ቤጊዜዉ ቢመላለስ እሳቸዉ ለፍርድ ካልተቀመጡ በስተቀር በመንገድ ላይ አቤቱታ ስለማይቀበሉ በጣም ተጉላላ እና ስለተናደደ ከፊታቸዉ ቁሞ ሰደባቸዉ ፡፡ በዚህ ግዜ ጉዳዩ ምን እንደሆነ እንዲያስረዳ ተጠይቆ በዝርዝር ስለተናገረ የተወረሱት ሙክቶች እንዲመለሱለት እና ሁለተኛም በሳቸዉ ዘመን ምልምል እንዳይመለመልበት ስለተደረገለት መልማዮቹ ወደሱ ሲሄዱ ጓንጉል ይብቃ የሚለዉን ነፃ ያደረገዉን የፍርድ ቃል በመጥቀስ ሳይመለመልበት ኖሯል፡፡

ከዋግ ሹም ጓንጉል ሞት ቡሃላ ዋግ ሹም ከበደ ተሹመዋል፡፡ እሳቸዉም ደግና ሃይማኖተኛ መሪ እንደነበሩ ይነገርላቸዋል፡፡ እንደ አባቶች አገላለፅ ዋግ ሹም ከበደ ለድሃ አዛኝ እና ፍርድ እንዳይጓደል የሚጥሩ ነበሩ፡፡ሹመት የሚሰጡት ለዋግ ዘሮች ብቻ ሳይሆን የማስተዳደር ችሎታ እና እዉቀት ላላቸዉ ሰዎች ጭምር ነበር፡፡ ጉቦንም በከፍተኛ ደረጃ ይቃወሙ ስለነበር በአንድ ወቅት አንዲት ድሃ ሴት ለጉዳይ መታያ ጉቦ ባዶ ሞሰብ ይዛ በመሄዷ እንጀራ ተቀባዩ ጉቦ መቀበል እንዳለበት ይገነዘባል፡ ባዶ መሆኑን ካረጋገጠ ቡሃላ ሊያሲዛት ቢሞክርም ቢቸግራት ነዉ
ብለዉ መለሱዋት እና ጉዳይዋን ፈፅመዉ ላኳት ይባላል፡፡

ዋግ ሹም ከበደ በላስታ እና በጎንደር ባላባት የሆኑትን የደጃዝማች ንጉሴ ፋሪስን ልጅ ወይዘሮ ሂሩትን አግብተዉ ሌተናል ጀኔራል ሃይሉን፡ እንዲሁም ደጃዝማች በላይን፡ ፊት አዉራሪ ገሰሰን፡ደጃዝማች በላቸዉን፡‹ጣሊያን ጋር ሲዋጉ የተገደሉ› ፡ደጃዝማች እጅጉን እና ግራ አዝማች በዛብህን ወልደዋል፡፡ ከዋግ ሹም ከበደወዲህም የዋግን የቆየ ጀግንነት እንዲታደስ ያደረጉት ልጃቸዉ ደጃዝማች ቡሃላ ሌተናል ጀኑራል ሃይሉ ከበደ ናቸዉ፡፡

ጀኔራል ሃይሉ ከ1927-1933 ኢትዮጵያን የወረረዉን የፋሽስት ጦር በማርበድበድ ጀግናዉን የዋግን ህዝብ አሰልፈዉ በቆራጥነት ሲዋጉ ፡ ወለህ በተባለዉና የሰቆጣ ከተማ አቅራቢ በሆነዉ የጦር አዉድማ ላይ አንገታቸዉ በጠላት ተቆርጦ ወደ ጣሊያን ሮም ሲወሰድ፡ ተራፊዉ አካላቸዉ ደግሞ ከሰቆጣ ከተማ በታች በሚገኘዉ እና ጉድጉዳ በተባለዉ ገደል እንዲጣል ተደርጉዋል፡፡ ሆኖም የአከባቢዉ ገበሬዎች አስከሬናቸዉን ወድቆ በማግኘታቸዉና የእራሳቸዉ መሆኑን በመገንዘባቸዉ ከአንድ የተወሰነ ቦታ ላይ ቀብረዉት ቆይተዋል፡፡ ፋሽስት
ጣሊያን ተሸንፎ የኢትዮጵያ ነፃነት ሲመለስ ግን አፅማቸዉ ከተቀበረበት ቦታ ተቆፍሮ ከወጣ ቡሃላ የአያታቸዉ የዋግ ሹም ተፈሪ ፡የአባታቸዉ የዋግ ሹም ከበደ አፅም ካረፈበት በሰቆጣ ደብረ ገነት መድሃኒአለም በክብር አርፉዋል፡፡ ይህን ጀግንነታቸዉን በመገንዘብም የኢትዮጵያ መንግስት ከሞቱ ቡሃላ ሌተናል ጀኔራል በሚለዉ ማእረግ እንዲጠሩ አድርጓል፡፡ማእረጉም በኢትዮጵያ ቤተ መንግስት ለክብራቸዉ ሲባል ከንጉሱ በስተቀር የመጀመሪዉ እንደነበር አበዉ ይናገራሉ፡፡

................................................(ምንጭ ፣ የአገዉ ህዝብ ታሪክ በ Dr. Ayalew Sisay)
ነገደ አገው
------------ ከአለቃ ታዬ መፅሀፍ(1914 ዓ.ም የታተመ)
አገዎች ግን ለ3 ተከፍለው ቋንቋቸውም ስሩ አንድ ሲሆን በየክፍላቸውና በየአገራቸው ጥቂት ጥቂት ልዩነት ያለው ሆነ፤እነርሳቸውም በ3 አገር ስም ይጠራሉ፤የላስታ አገው፤የዳሞት አገውና የሐልሐል ቦጎስ አገው ተብለው ይጠራሉ፡፡ የሁሉም መሰረትና ምንጭ የላስታ አገው ነው፡፡
የላስታ አገዎች 7 ሆነው ዝሆንና ጎሽ አደን ብለው ሄዱ፤ከዚያ ሰው እንደሌለበት ፤ጠፍ እንደሆነ ተመልክተው የአገሪቱንም ደግነት አይተው በየዱሩ፡ በየዛፉ፡እጅግ ንብ የበዛበት ብዙ ማር የሚገኝበት አገር ነውና፡ ማርና፤የዱር እንሰሳት ስጋ አድነው እየበሉ 7 ወር አገሪቱን ደህና አድርገው ዞሩና መረመሩ፡፡ ከዚህ በኋላ ምሽቶቻቸውንና፤ ልጆቻቸውን፤ላማቸውን፤ፍየላቸውን፤ጓዛቸውን ሁሉ አምጥተው በዚያቸ አገር ተቀመጡባትና አቀኗት፡፡ ባላገሮችና ባላባቶችም ሆኑባት አገሩም አገው ምድር ተባለ፡፡ በ7ቱ አባቶች በየክፍሉ ሲዘረዘር 7 ቤት አገው ይባላል፡ በ7ቱ አባቶቻቸው ስም አገራቸው ሰይመው 7 ቤት አገው ተብለው በየአገራቸው በየክፍላቸው ይጠራሉ፡፡ የሐልሐል ቦጎስ አገዎች ግን በአንድ ዘመን በየአገሩ ርሃብ በሆነ ጊዜ እንዲሁ በላስታ አገው 7 ወንድማማች አገዎች ከነሚስቶቻቸው፤ ከነልጆቻቸው፤ 3 እህቶቻቸው ከነባሎቻቸው ተሰደው ሐልሐል ቦጎስ ገቡ፡በዚያም ዱሩን መንጥረው እባቡን ገድለው ቤት ስርተው አገር አቅንተው ተቀመጡ ይባላል፡፡ የላስታ አገዎች በዋግ የሚኖሩ ዋኖች እነርሱ ናቸውና በመጀመሪያ የያዙትን አገር(በቀዳማዊ ሚኒሊክ ዘመን ይለዋል) አልለቀቁም፤ እስከዛሬም አልተነቃነቁም፡፡
አዊና የፈረስ ትርኢት...
-------------------
(ተጓዡ ጋዜጠኛ ሔኖክ ስዩም ለዛሬ ደግሞ ወደ አዊ ዞን ተጉዞ በ1933 የተመሰረተው የአዊ የፈረሰኞች ማሕበር በየዓመቱ በአዊ ዞን የሚያካሄደውን የአዊን የፈረሰኞች ቀን አከባበር ያወጋናል...) አዊን እያለፍኩ ነው፡፡ ለምለሙን ምድር፤ ጥር እየተሸኘ አይደለም፡፡ አዊና ፈረስን ነጣጥሎ ማየት አይቻልም፡፡ አዊ ፈረስና ጥር ደግሞ ሶስትም አንድም ናቸው፡፡ ሩቅ ላላችሁ አዊ አማራ ክልል የሚገኝ አዊ የተባለ ብሔረሰብ መኖሪያ ነው፡፡ የጎጃም ምድር፤ ለሙ ሀገር አዊ፤ ፈረስ ለአዊ ሁለንተናው ነው፡፡ እርሻ ስራው ጉልበቱ በመሆኑ ይወደዋል፡፡ በክፉም ሆነ በደግ በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች መጓጓዣ ትራንስፖርቱ ፈረስ ነው፡፡ ለአዊ ሁሌም ያስፈልገዋል፡፡ ያለ ፈረስ አዊን ባናስበውስ፤ አዊ በደስታውም ቢሆን በዓሉን የሚያደምቀው በፈረስ ነው፡፡ ሰርጉ ጭምር በፈረስ ይዋባል፤ ሞቶ ወደ መቃብር ሲሸኝም ፈረስ መሸኛው ነው፡፡ የአዊ ፈረሶች በክብር የሚሸለሙ፣ ሁለመናቸው የሚስብ ከልጅነታቸው የሚገሩ ናቸው፡፡ የሚጋለቡበትን ሜዳ ሰንጥቄው እያለፍኩ ነው፡፡

መምጣት የምትሹ ከአዲስ አበባ በ435 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው እንጅባራ ከተማ ብላችሁ ኑ፤ እንጅባራ የአዊ መዲና ነው፡፡ አዊ በረጃጅም ተራሮቹ፣ በውብ ፏፏቴዎቹና ባልተነካው የአዊ የባህል እሴት የሚታወቅ ዞን ነው፡፡ አዊና ፈረስን ደጋግሜ ሳነሳባችሁ አትገረሙ፡፡ በ1933 ዓ.ም የተመሰረተው የአዊ ፈረሰኞች ማህበር 74 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ የአዊ ፈረሰኞች ማኅበር ጠላትን ከሃገር ለማስወጣት አንድነትን ለመፍጠር በሚል በአንድ የተደራጀ ነበር ያኔ….. ዛሬ ደግሞ በየዓመቱ የአዊን የፈረስ ጉግስ ይደግሳል፡፡

የአዊ ፈረሰኞች ማኅበር 22,275 አባላት ያሉት ሲሆን ይህ ማኀበር በየዓመቱ ዓመታዊ በዓል ያከብራል፡፡ ይህ በዓል የአዊ ፈረሰኞች ቀን ይባላል፡፡ በዚህ የባህል አከባበር ደንብ አመታዊው በዓል ከወረዳ ወደ ወረዳ እየተዘዋወረ የሚከበር ነው፡፡ አዊ ዞን አስር ወረዳዎች አሉት፡፡ አንድ ወረዳ በአስር አመት አንዴ የአዊ ፈረሰኞች ቀንን የማዘጋጀት እድል ይገጥመዋል፡፡ የአዘጋጅነት እድሉ በተራ የሚዞር ሲሆን አዘጋጁ ወረዳ ሰፊ ዝግጅት ያደርጋል፡፡ በዚህ የፈረሰኞች ቀን ከፈረስ ስፖርት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ባህላዊ ስፖርቶች ይካሄዳሉ፡፡ እነዚህ ባህላዊ የፈረስ ስፖርቶች በዋናነት ሶስት ናቸው፤ ከእነዚህ መካከል ጉግስና ሽርጥ ቀልብ ሳቢ ውድድሮች ናቸው፡፡

በውድድር መልኩ ከሚዘጋጁት ውድድሮች ባሻገር በፈረስ የሚደረጉት ያልተደራጁ ትርኢቶች ለሚመለከታቸው የተደራጁ መሳይ ማራኪና ሳቢ ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ወረዳ በዚህ አመታዊ የፈረስ ትርኢት ላይ አንድ አንድ ከብት ይዞ ይመጣል፤ በትንሹ በበዓሉ አስር ከብቶች ይታረዳሉ፡፡ የአዊ የፈረሰኞች ቀን በሚል በየዓመቱ የሚከበረው ይህ የፈረስ ትርኢት በወርሃ ጥር ካሉት በአንዱ እሁድ ቀን ይከበራል፤ መደበኛ ቀን የለውም፡፡ ወሩ ግን የግድ ጥር ዕለቱም እሁድ መሆን ይጠበቅበታል፡፡

ከዚህ ባሻገር ዓመታዊው በዓል መቼ እንደሚውል በማኅበሩ ይገለጻል፡፡ ለምሳሌ እንደ ዓመቱ ልዩ ክስተት ተቆጥሮ ያለፈው የ2004 ዓ.ም የአዊ ፈረሰኞች ቀን በዓል ጥር 20 ቀን 2004 ዓ.ም በደማቅ ዝግጅት ተከብሮ ነበር፡፡ በድምቀት እና እንግዳን በማሳተፍ ደረጃ የመጀመሪያ ነው የተባለለት የ2004 ዓ.ም የአዊ ፈረሰኞች ቀንን በዓል ያስተናገደችው ቲሊሊ ከተማ ነበረች፡፡ ቲሊሊ ስደርስ መልሼ ያንን ውብ ጊዜ አስታወስኩት::
ፋጥዝጊ!
--------
ፋጥዝጊ ሰቆጣ ሳድግ ቦርቄ ከደኩባቸዉ ቦታዎች አንዱ ነዉ፡፡ የሚገርም አስደማሚ ቦታ ነዉ ሰቆጣ አድጎ በመስቀለ ክርስቶስ በኩል ወለህን ድግርሽን አበሃንስን ሲቪሉን ጉድጉዳን አደጋን የማያውቅ የለም፡፡ ፍጥዝጊ ከሰቆጣ ወደ ሰሜን በኩል የሚገኝ በገደል የተከበበ ሜዳማ ቦታ ነዉ፡፡ በሰብል አብቃይነትም የታወቀ ነዉ፡፡ ከሜዳዉ ጫፍ በደቡብ በኩል ሰቆጣን ሙሉ ለሙሉ ማየት ያስችላል፡፡ በሰሜን በኩል ትልቅ ወንዝ የሚታይ ሲሆ ወንዙ ዳር በሰፊዉ ሌላ ጊዜ የማጫውታችሁ በድንጋያማ ክብ ወደላይ ከተመዘዘ ተራራ ላይ ያለች የምትታይ ጥንታዊ ቤተ ክርስቲያን ማየት ያስችላል፡፡ ስለልጅነቴና ስለጓደኞቼ ስላሳለፍነዉ ጣፍጭ ጊዜ ለሌላ ጊዜ ይቆየን፡፡ ዋናው ነጥቤ ሰቆጣ አየር ማረፊያ ነበራት! ትገረሙ ይሆናል ነገር ግን በደርግ ጊዜ የአየር ማረፊያ ነበራት፡፡ ካላመናችሁ ፍጥዝጊ ወጣ በለና ቅርፅን ሳይቀይር ተንጣሎ ይታያል፡፡ እንደዉም አየሮች ማረፍ ሲደብራቸዉ ፍጥዝጊ ላይ የእርዳታ ቁሳቁስ ከአየር ላይ ይጥላል፡፡ አስካሁንም ወደዚያ ሲያቀኑ ስቃጥላ ማግኘት የተለመደ ነዉ፡፡ ማወቅ ያልቻልኩት አየር ማረፊያውን ደርግ ለምን ሲጠቀምበት እንደነበር ነዉ፡፡ የምታውቁ ሹክ በሉን፡፡ ደርግ መቸም ሲርብህ አብልቶ ሲጠማህ አጥት ሲበርድህ አልብሶ ነበር የሚገድለዉ፡፡ የአሁኖቹ ከደርግ በመማር በብልጠት ገድለዉ ያፋልጋሉ! ዛሬ ሰቆጣ እንኳን አየር ተለቅ የሉ አውቶብሶች የማይገቡባት ሁናለች፡፡እድሜ ታግለን ለዚህ ላበቃነዉ የወንበዴ ስብስብ!!! ዛሬ ሰቆጣ ውሃ ለመጠጣት የሃይላድ መግዥ ያስፈልጋታል፡፡

ባጠቃላይ ዋግ በደርግና በኢሃዴግ ስትነፃፀር መብራት ስናይ በደርግ ጄኔሬተር አሁን 24 መብራት መሆኑ በጥሩ ጎኑ እሱም ታምራት ላይኔ ባያስገባዉ ዛሬም ጨለማ ውስጥ ልንሆን ይችላል፡፡ መንገድ ብናይ ያኔም የጠጠር መንገድ ዛሬም ጠጠር መንገድ፡፡ የዉሃ የምታውቁት ነዉ፡፡ እንግዲህ ሰቆጣ ከመብራትና ስልክ ውጭ ደርግ እንደተዋት ናት፡፡ እንደዉም በደርግ ወንዞቻችን አልደረቁም ነበር የከተማችን ውበት በለስ ወንዝ አልደረቀም ነበር፡፡ እነ ይልማ በአመት አንድጊዜ በጳጉሜ እየታጠባችሁ አታካብዱ አይለንም ነበር፡፡ ይልማ ያላወቀዉ በአመት አንድ ጊዜም ሆኑ ብዙ ጊዜ የምንታጠብበትን በለስን ስላሳጣችሁን መሰለኝ ጭሆታችን፡፡ ምን ታደርጉ የዋህና ዝም የሚል ህዝብ ስታገኙ ያለዉን አረጃችሁብን፡፡ በዘንድሮ ምርጫም ወንበር ለማሞቅ የምትፈለጉት ለውድድር መቅረባችሁን ለጥፋችሁ አየን፡፡ ጭራሽ ካሳ ጋር አብራችሁ ስትቀርቡ ተሳቀቅን!!! በተለይ ለተወካዮች ምክር ቤት ያቀረባችሃት በጣም ነዉ የምትወክለን እንኳን የህዝብ ችግር ልትናገር ህግ ለማፅደቅ እጅ የምታወጣም አይመስለኝ፡፡ ቁጭ እንዳለች አለች ወደፊትም መሆኗ ነዉ፡፡ ነብስ ያለዉ ለህዝብ የሚወግን ዋግ አይመረጥም አይፈለግም!!

አገሬ ሰቆጣ ዝምታን አበዛ
አገሬ ደሃና ዝምታን አበዛ
አገሬ ጋዝጊብላ ዝምታን አበዛ
አገሬ ዝቋላ ዝምታን አበዛ
አገሬ ሰሃላ ዝምታን አበዛ
አገሬ አበርገሌ ዝምታን አበዛ
እረ አገሬ ላስታ ዝምታን አበዛ
የተነሳ እንደሆነ ላይለቅ እንደዋዛ
ዝምታው ችግሩ ያለልክ በዛሳ፡፡
All the Above information is contributed by Lij Eyasu Ze Ethiopia
‪#‎Agaw‬ ‪#‎Bete‬