ቤተ አማራ ምን ይዞ ነው የራሱን መንግስት የሚመሰርተው?
--------------------------------------------------------
ሰሞኑን ከጓደኞቼ ጋር ሰብሰብ ብለን ስንጫወት ከጓደኞቼ አንዱ ለሌሎቹ እንዲህ አላቸው። እኔን እየጠቆመ -- ከቤተ አማራ አቀንቃኞች አንዱ ይሔ ነው አላቸው። ስለ ቤተ-አማራ እስኪ ንገረን አሉኝና እኔም ስለቤተ አማራ የምችለውን ሁሉ አብራራሁ። ቤተ አማራ -- የአማራ እንግልት የገባቸው አማራ ወጣቶች የመሰረቱት ወጣ ያለ (radical) አስተሳሰብ ነው። እኛ ከምንም በላይ አማራ እንደገና እንደዜጋ የሚቆጠርበት አገር ያስፈልገዋል ብለን እናምናለን። ለአከፉት 40 አመታት ኢትዮጵያ ለአማራ አገር ልትሆነው እናትነት ልታሳየው አልቻለችም። ወያኔ እንኳን ቢወድቅ ለአማራ ጥሩ አመለካከት የሌላቸው ሕዝቦች በተሰበሰቡባት ኢትዮጵያ የአማራን ሕልውና የምታስከብር ኢትዮጵያን መመስረት ከባድ ነው -- አይቻልምም። ቤተ-አማራ ከኢትዮጵያ ጋር ምንም ችግር የለበትም። ነገር ግን ኢትዮጵያን የምንፈልጋት እርስዋ ስትፈልገን ብቻ ነው፤ እንደ ዜጎችዋ ስትቀበለን ብቻ ነው። እንጂ ኢትዮጵያ እያስገደለችንንና እየተፈናቀልን አብሮ መኖር በሚል ስበብ ብቻ የምናፈሰው ደም ከዚህ በሁውላ አይኖርም። ብቻ ስሜታዊ ሆኜ ተናገርኩ። ከዚያም አንዱዋ ጉዋደኛዬ ይህንን ጥያቄ ጠየቀችኝ።
--------------------------------------------------------
ሰሞኑን ከጓደኞቼ ጋር ሰብሰብ ብለን ስንጫወት ከጓደኞቼ አንዱ ለሌሎቹ እንዲህ አላቸው። እኔን እየጠቆመ -- ከቤተ አማራ አቀንቃኞች አንዱ ይሔ ነው አላቸው። ስለ ቤተ-አማራ እስኪ ንገረን አሉኝና እኔም ስለቤተ አማራ የምችለውን ሁሉ አብራራሁ። ቤተ አማራ -- የአማራ እንግልት የገባቸው አማራ ወጣቶች የመሰረቱት ወጣ ያለ (radical) አስተሳሰብ ነው። እኛ ከምንም በላይ አማራ እንደገና እንደዜጋ የሚቆጠርበት አገር ያስፈልገዋል ብለን እናምናለን። ለአከፉት 40 አመታት ኢትዮጵያ ለአማራ አገር ልትሆነው እናትነት ልታሳየው አልቻለችም። ወያኔ እንኳን ቢወድቅ ለአማራ ጥሩ አመለካከት የሌላቸው ሕዝቦች በተሰበሰቡባት ኢትዮጵያ የአማራን ሕልውና የምታስከብር ኢትዮጵያን መመስረት ከባድ ነው -- አይቻልምም። ቤተ-አማራ ከኢትዮጵያ ጋር ምንም ችግር የለበትም። ነገር ግን ኢትዮጵያን የምንፈልጋት እርስዋ ስትፈልገን ብቻ ነው፤ እንደ ዜጎችዋ ስትቀበለን ብቻ ነው። እንጂ ኢትዮጵያ እያስገደለችንንና እየተፈናቀልን አብሮ መኖር በሚል ስበብ ብቻ የምናፈሰው ደም ከዚህ በሁውላ አይኖርም። ብቻ ስሜታዊ ሆኜ ተናገርኩ። ከዚያም አንዱዋ ጉዋደኛዬ ይህንን ጥያቄ ጠየቀችኝ።
ቤተ-አማራ ምን ይዞ ነው የራሱን መንግስት የሚመሰርተው? አማራ ክልል እኮ ለም አይደለም። እንደ ደቡብ ምርት የሚሰጥ መሬት የለንም። ምን ይዘን ነው አገር የምንመሰርተው?
Really? That is your understanding? አልኩና ፍጥጥ ብዬ ለረጅም ሰዓት አየሁዋት። ወደ ሃሳቤ ስመለስ ምናልባትም ሌሎች የአማራ ልጆች እንደዚህ ያስቡ ይሆናል ብዬ አሰብኩ። እናም ይህችን ፅሁፍ መሞነጫጨር እንዳለብኝ ውስጤ አመነ። ለእርሱዋም ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ነገር ነው የነገርኳት።
ጥያቄውን ለመመለስ በመጀመሪያ የአንድ አገር ሐብቱ ምኑ ነው ብሎ ማሰብ ነው።
ዋናው የአገር ሃብት ሕዝቡ ነው። አገርም የሚያድገው በሕዝቡ ጥረት ብቻ ነው። ቤተ-አማራም በጠንካራው እና በታታሪ ሰራተኛው 36 ሚሊዮን የአማራ ሕዝብ ያምናል፣ ይተማመናል። በጣም እሳት የላሱ፣ የተማሩ ለአገር ለወገን የሚተርፉ ሰወች ባለቤት ነው -- ቤተ አማራ። ሕዝባችን ነፃነት ካገኘ የተመኘውን መስራት እና መፈላሰፍ ከቻለ ለሕዝቡ መፍትሔ ሊሆኑ የሚችሉ ኃሳቦች ያመነጫል። እንዲያም እንዲሆን ይደረጋል። ከብዙ ሃብታም አገሮች ጀርባ ሕዝባቸው ብቻ ነው ያለው። ጃፓን ምን አላት ከሕዝቡዋ ውጭ? አብዛኞቹ የአውሮፓ አገሮችስ ምን አላቸው? ሕዝብን በተለይም የተማረውንና ኃሳብ ማመንጨት የሚችለውን ሕዝብ ለስልጣን ጥቅም ብለህ እንዳያስብ ስታደርገው አገር ይደኸያል። አስቡት ዋይት ኃውስ ጎልጉለው ሚስጥሬን ያገኙብኛል ብሎ አስቦ Google እንዳይመሰረት ከልክሎ ቢሆን ኖሮ እስካሁን Google ያፈራው ትሪሊዮን (Trillion) ዶላር ባልተገኘ ነበር። ከአሜሪካ ሐብት ጀርባ የሰወች ነፃ ማሰብ መቻል ብቻ ነው ያለበት። ያንን አይነት ነፃነት ለሕዝባችን በማጎናፀፍ ፈጠራን እናበረታታለን። ፈጠራን እንደጉማለን። የእኛ ሕዝብ እኮ ምን ያሕል እንዳያስብና እንዳይፈላሰፍ እንደተደረገ ለማየት ሺህ ዓመት ቅርፅዋ እንኳን ያልተቀየረ ማረሻ እንደምንጠቀም አስተውሉ። በጠቢቡ ሰለሞን ዘመን የነበረ ወናፍ ነው እስካሁን የምንጠቀመው። ትምህርት ለሐገር የጀርባ አጥንት እንደሆነ ስለምንገነዘብ ትምህርት ላይ ሰፊ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን። ያልተማረው ሕዝባችን ማንበብና መፃፍ እንዲችል በማድረግ የሕዝቡን ንቃተ ሕሊና ከፍ እናደርጋለን። ማንበብና መፃፍ የሚችልን ሕዝብ ከቴክኖሎጂ ጋር ማቆራኘት ስለሚቀልም እንደዚያ ይደረጋል።
ስለለም መሬት ከጀመርንማ ስንቱን ዘርዝሬ እጨርሰዋለሁ። ስለአዴት ጤፍ ላውራ ወይስ ስለፎገራ ሩዝ፣ ስለመተማ ጥጥና ሰሊጥ ላውራ ወይስ ስለመተከል በቆሎ፣ አማራ ውስጥ ምን የማይበቅል የእህል ዘር አለ። አሁን ባለበት ሁኔታ ብቻ ምንም አይነት ጥናትና ምርምር እንዲሁም ቴክኖሎጂ ሳይታከልበት እራሱ ምስራቅ አፍሪካን የሚቀልብ እህል እያመረትን ነው። ቤተ-አማራ ቴክኖሎጂን ወደ እርሻው ሲያመጣው በየቦታው እና በየአዝዕርቱ የእርሻ ምርምር ሲከፍትና ምርጥ ምርጥ ጭንቅላቶችን ሲያሰባስብ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አስቡት። አፍሪካን እንደምንቀልብ ጥርጥር የለውም። እንዴው ለጥቆማ ይህን ልናገር። አሁን ባደጉት አገሮች በቆሎ ለዘይትነት በስፋት ያገለግላል። CORN OIL የማይበላ ሰው ያለ አይመስለኝም። የምዕራብ ጎጃም በቆሎ ወደ ዘይትነት ቢቀየር እውነት አሁን ኢትዮጵያ ዘይት ወደውጭ ላኪ አገር አትሆንም ነበር። ግን ምን ዋጋ አለው። ምስኪን የኢትዮጵያ ሕዝብ በዘይት እጦት ይቸገራል። በዘይት እጦትም ምክኒያት ቀበሌ ተሰልፎ ለሶስት ጊዜ ሽሮ የማትሆን ዘይት ይዞ ወደ ቤቱ ይመለሳል።
ስለእንስሳት ሐብታችን ለማውራት ምኑን ተናግሬ ምኑንስ ልተወው። ስጋ ወደውጭ መላክ ወይን በፋብሪካ የለሰለሰ ቆዳ መላክ -- የቱን ላውራው። የእኛን ሐገር ቆዳ እና ሌጦ ለመስራት ስንት ፋብሪካዎች ይበቁናል? ስንትስ የስራ እድል ይፈጠራል? ሕዝብ የኢኮኖሚ አቅሙ ሲጨምር የስጋ ፍጆታው እንደሚጨምር ይታወቃል -- በዚያው ልክ የቆዳ ምርታችንም መጨመሩ መሆኑ ነው። ስንት ሚሊዮን ከብት፣ በግና ፍየል እንዳለን አስቡትና የምርምር ተቋማት ሲከፈቱ ስለሚሻሻለው ምርታማነታቸው አስተውለት። መልሱ እዛው ላይ አለ።
ጣናን የሚያክል ሐይቅ እባካችሁ ተተቀሙብኝ እያለ ነው። ጣና ላይ የሚሰራ አንድ የምርምር ተቋም ስናቋቁም የአሳ ምርታችን በስንት እጥፍ እንደሚጨምር አስቡት። አሳን በብልሃት መብላት ብቻ ነው የኔ የሚሆነው። እኔ አሁን ስለ Marine Life ብዙ ስለማላውቅ ስለጣና ጥቅም ላውራ ብል የጣናን ጥቅም በጣም አሳንሰዋለሁ። ግን አንድ ነገር አውቃለሁ ጣና ብቻውን ቀጥ አድርጎ ሊይዘን እንደሚችል። ቤተ-አማራ ጣናን እንደ ትልቅ ሐብት ያየዋል። ሊሰራበትና ሊጠቀምበትም አቅዷል። ለምግብነት ብቻ ሳይሆን ለኃይልም ጭምር። ጣና ገና ይዘመርለታል።
ስለቱሪዝም ላውራ እንዴ። ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ቱሪስት የሚመጣበት ዋናው ምክኒያት ለምንድን ነው ብላችሁ ጠይቃችሁ ታውቃላችሁ? የላሊበላ ፒስታ መንገድ እና በየቀኑ በረራ አለሞኖር ሳያግደው ቱሪስት ይተምማል። የጣና ገዳማት የረባ ከትንሽ ማዕበል የማያስጥል ጀልባ አለመኖሩ ሳያግደው ቱሪስቱ ይጎበኘዋል። ጎንደር ፋሲለደስስ ስንቱን ቱሪስት ጠራው! ከኢትዮጵያ የቱሪስት መስዕብነት እምብርት እኮ ያለነው እኛ ነው። ሳፋሪ (safari) ለመጎብኘትማ ኬኒያና ታንዛኒያ ይሻለሉ እኮ። ግን ታሪክ የሚጎበኝ፣ ባሕል የሚጎበኝ ነው ኢትዮጵያ የሚመጣው። ኢትዮጵያም ሲመጣ ቀጥታ ሩጫው ወደ አማራ ነው። ይሕ ሃቅ ነው።
አስባችሁታል አንደ ከተማ መርጠን Internet City ብናደርጋት። እና የላሰ ከእይን የፈጠነ Internet ለዛች ከተማ ብናስገባላት። ምርጥ ምርጡን Computer Scientist እና Engineer ሰብስበን መስሪያ ቤት ሳይሆን ከተማ እንካችሁ ብንላቸው። ከዚያም እነዚያ ምሁሮቻችን ጨረታ እየተወዳደሩ ለትልልቅ ካምፓኒዎች (Google, Apple, Microsoft, Amazon, Oracle ...) በርካሽ ስራ መስራት ቢጀምሩ። አገራችንንም ቴክኖሎጂ በቴክኖሎጂ ቢያደርጉዋት --አስቡት። የሕንድዋ ሙምባይ(Mumbai/Bombe) የInternet City ሆና ነው ሕንዶች በComputer Science እንዲታውቁ የሆነት። የእኛዋም ይህች የInternet ከተማችን ከማንኛውም export በላይ የውጭ ምንዛሬ ታስገኛለች። የተማሩ ቤተ-አማራዎችንም ወደ አገራቸው እንዲገቡ ምንክኒያት ትሆናለች፤ አገራቸው ሆነው ለትልልቅ ካምፓኒዎች መስራት እንዲችሉ ታስችላቸዋለች። አንድ Microsoft የሚሰራ ወገኔ ስለዚህ ነገር ስናወራ ምን አለኝ መሰላችሁ። ኃሳቡን ለመንግስት አቅርበነው ነበር አለኝ። ቦሌን የInternet City እናድርጋት የሚል ፕሮፖዛል ይዘን ነበር የሔድነው አለኝ። በጉጉት -- እናስ ስለው። መንግስት አብዷል እንዴ Information ለእኛ የሚሰጠን አለኝ። ጭራሽ አይታሰብም አይሆንም ተባልን አለኝ። ለነገሩ ቆልፍ የሆነውን Information ወያኔ ለተማረው ከሰጠ ስልጣኑ እድሜ እንደማይኖረው ያውቃል። ለአገሪትዋ እድገት ሳይሆን ለስልጣናቸው ብቻ እንደሚጨነቁ ከዚህ በላይ ምን የሚያሳይ ነገር አለ?
እርግጠኛ ነኝ ይህንን ስታነቡ እንዴ ይሕስ ቢሆን የምትሉት ብዙ ነገር እንዳለ ቅአውቃለሁ። እናንተ እሱን እየጨመራችሁ አንብቡት። ሕብታም እንደሆንን እወቁ። ኮራ በሉ። የራሳችንን መንግስት ስንመሰርት የነፃነት አየር እየተነፈስን፣ ለወገናችን እየሰራን፣ የእኔ የምንለው የሚወክለን መንግስት መስርተን፣ ተሳስበን ተሰባስበን እንኖራለን። ከተሞቻችን የንግድ ማዕከል ይሆናሉ። እንደዚያም ዲዛይን ይደረጋሉ። ሕብረተሰቡን በማስተማር ሰፊ የአመለካከት ለውጥ መምጣት ያለባቸው ነገሮች ላይ አተኩረን በመስራት ስር ነቀል ለውጥ እናመጣለን። ይሆናል። ይሳካል። ብቻ ሁሉም ቤተ-አማራ በያለበት ይበርታ።
(ራስ የማነ የቤተ አማራ ኢኮኖሚስት)