መገንጠል ስንት ነው? ቤተ አማራስ ምንድነው?
የአማራን መንግስት ስለማቋቋም የውይይት መነሻ ሀሳብ ማሰራጨታችን ይታወቃል፡፡ ከቤተ አማራም ከውጭም የሆኑ ሰዎች ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በንቃት እየተሳተፉበት ይገኛሉ፡፡ ለተሳትፏችሁ እጅግ እናመሰግናለን፡፡ ሃሳባችንን የደገፋችሁም፤ በእኛ ላይ የዛታችሁም፤ የሰደባችሁንም፤ ሁላችሁንም ገንዘብ ሳንከፍላችሁ፤ የተለየ ጥሪ ሳናደርግላችሁ በንቁ በመሳተፋችሁ እጅግ እናመሰግናለን፡፡ የሁላችሁንም ሃሳብ ሰምተን ጨመቅ አድርገን እንደገና አቅርበንላችኋል፡፡ የተለመደው ንቁ ተሳትፎአችሁ የቤተ አማራን መንግስት ለመመስረት እጅግ ወሳኝ በመሆኑ ያላችሁን ሃሳብ ስድብንም ጨምሮ ሳትሰስቱ እንድትሰጡ አሁንም በድጋሜ ትጠየቃላችሁ፡፡ የመጀመሪው መጀመሪያ፡፡
ሀ) ምነው እንደ እባብ ስንቀጠቀጥ እንዲህ አልጩሀችሁልንም ነበር? እውን እንዲህ የሚያደርጋችሁ እኛን በመውደዳችሁ ነው? አዲስ አበባ አብተክርስቲያናት እንኳ መጠጊያ ተከልክለን ስንባረር እጃችሁን ኪሳችሁ ውስጥ ከታችሁ ስትንጎራደዱ አልነበረምን? በየቦታወ ለታረዱት ማንን ጠየቃችሁልን? ማንስ ፍርድ ቤት ይቅረብ ብላችሁ ተሰለፋችሁልን? ፍቅራችሁ ይህ ነውነ ለእኛ? በዚህ ሁሉ መከራ ችግራችን አልታያችሁም ወይስ እንደውሻ ቆጠራችሁን? መልካም፡፡ ሰውነታችን እስኪታወቅና እስኪከበር ድረስ እንጓዛለን፡፡
ለ) አማራ ዜግነት አለውን? አማራ መንግስት ካጣ 40 አመት አልፎታል፡፡ ይህ አገዛዝ እኛን አይመለከትም፡፡ ዜግነት የለንም፡፡ እንደዜግነታችን ያገኘነው ነገር ቢኖር ምናልባት ግድና ሰቆቃ ነው፡፡ ጥያቄያችን ዜግነት ማግኘት ነው፡፡ አይደለም በተቀረው ኢትዮጵያ በክልላችን ባይተዋር ነን፡፡ እኛ ስለዜግነት እንናገራለን፡፡ እናንተ ደግሞ ቅርጽዋ እንዳይበላሽ ለምትፈልጓት ካርታ ትጨነቃላችሁ፡፡ ቸር መንገድ፡፤
ሐ) ምነው አሁን እኮ ያነሳነው ራስን መቻልና መንግስት መሆንን እንጅ ከተገነጠልንማ ቆየን እኮ፡፡ አሁን ያነሳነው የመሬት መገንጠልን እንጅ ከገነጠላችሁን እኮ ቆያችሁ፡፡ በማህበራዊ ህይዎት ተገንጥለናል፡፡ ከፖለቲካዊ ህይወት ተገንጥለናል፡፡ ከእምነትና ሀይማቶቻችን ተገንጥለናል፡፡ ከስነቃላችንና ወጋችን ሳይቀር ተገንጥለናል፡፡ ከሀገራችን የምጣኔ ሀብት ተቋዳሽነት ተገንጥለናል፡፡ ከስነጥበባችን ተገንጥለናል፡፡ ከሰውነታችን ተገንጥለናል፡፡ ይህንን ሁሉ ግንጠላ ያካሄዳችሁት እናንተው ናችሁ፡፡ በተግባር የገነጠላችሁን ተቀምጣችሁ ምነው እኛ ከዚህ ሁሉ ረፍት ለማግኘት አገራችንን ብቻ እንገንጥል ስንል ጦር ሰበቃችሁብን? ቀድሞውንም በዋላችሁበት እንዳንውል ነጥላችሁ ገንጥላችሁናል እኮ፡፡ እኛ ስንናገረው አስጠላችሁ አይደል? ምነው ስታደርጉት አላፈራችሁምሳ?
መ) መገንጠል የሚለውን ቃል ያልወደዳችሁት ሰዎች የአማራ ነጻ መንግስት ማቋቋም ብላችሁ ተረዱት፡፡
ሠ) እኛ እየተናገርን ያለነው ስለጎስቋላውና ሰሚ ስላጣው መጻተኛ ወገናችን ነው፡፡ በአጉል ምክንያታዊነት ተጀቡናችሁ በህዝባችን የምታሾፉትን አማሮች አይመለከትም፡፡ የእናንተ ምክንያት ፈለጣ የአንድ አማራ ህይወት እንኳ አላዳነም፡፡ ዛሬም በህዝባችን ህልውና ላይ ትመጻደቃላችሁ፡፡ ግፍ ግን ሰአቷን ትቆጥራለች፡፡ ረ
) ይህ የአንድ ወይም የሁለት ሰው ሀሳብ ነው ያላችሁ ሰዎች አንድ ነገር ልብ በሉ፡፡ የተወሰኑ ሰዎች ሀሳብ ነው ብላችሁ ካመናችሁና ዋጋ የለውም ካላችሁ እርሱን፤ ተውን፡፡ ንቃችሁ ተውን፡፡ እኛ ግን ሃሳብ የአንድ የሁለት ሰው ነው፡፡ ተግባር የብዙሀኑ ነው እንላለን፡፡
ሰ) እንገንጠል ስንል መነጽሩን ነው የገለበጥነው፡፡ ወደራሳችን ተጨባጭ ሁኔታ ማየት፡፡ ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ቅድሚያ ያልነውን ትተን ቅድሚ ህልውና ከዛ ኢትዮጵያ ብለን አስተካክለነዋል፡፡
=============================================
1) አማራ የለም ያሉ አማራ የለም ላላችሁት ወገኖች የምንላችሁ ነገር ይህ ነው፡፡ አማራ ከሌለ የሌለ ነገር ሲገነጠል መከፋት የለባችሁም፡፡ የለም ባላችሁበት አፍ እንደገና አይቸሃለሁ የት አባትክ ነው የምትሄደው ብሎ መዛት ትዝብት ውስጥ ይከታል፡፡ የእኛን መኖር እስክታውቁ ድረስ ትግላችን ይቀጥላል፡፡ መኖርና አለመኖራችንን እዛው እቦታችን እንነጋገራለን፡፡ ህልውናችን መካዱም አንዱ የትግላችን ምንጭ ነው፡፡ እና ለአሁኑ አማራ የለም ባላችሁበት አቋማችሁ እንድትፀኑበት እንጠይቃለን፡፡ እርሱን፡፡ በቃ የለንም፡፡
2) አማራን መገንጠል የአላዋቂዎች ጥያቄ ነው ያሉ እኛ ስለዩኒቨርሲቲ መከፈት አይደለም እያወራን ያለነው፡፡ ጎሽ ለልጇ የምትሞተው ዲግሪ ወይም ዲፕሎማ ስላላት አይደለም፡፡ ለአማራ መቆርቆር የእውቀት ጉዳይ አይደለም፡፡ የስነ ፍጥረት ጉዳይ እንጅ፡፡ ጎሽም፤ ሰውም፤ አንበሳም ሆነ ነብር ወገኑ ሲነካ የስነ ፍጥረት ባህርይው ወደ ተከላካይነት ይወስደዋል፡፡ እናም እኛን ተንከባክበው ያሳደጉን ዲግሪም ሆነ ዲፕሎማ የሌላቸው እናቶቻችን ናቸው፡፡ የተማሩ እናቶች ያሳደጓቸው ቢኖሩ እንኩ እምብዛም ናቸው፡፡ እና እናቶቻችን ሲያለቅሱ ማየትን አልወደድንም፡፡ ስነፍጥረታዊ ውለታ ስላለብን፡፡ ከዛም ባሻገር እውቀትም ካስፈለገ የእናቶቻችን ማህጸን አይታማም፡፡ አማራን ከጥፋት መታደግና ለተገፋው አማራ መቆርቆር ከእውቀት ጋር ሳይሆን ከአብራክ ክፋይነት ጋር ነው የሚገናኘው፡፡
3) እኛ ብቻ ካልገዛናት ኢትዮጵያ ትውደም አሉ ያሉ ሳያስቡት እውነቱን በአደባባይ ያፈረጡት ወገኖች አማራ ልገንጠል የሚለው ኢትዮጵያን እኔ ነኝ መግዛት ያለብኝ ብሎ ስለሚያስብ ነው ያሉት ናቸው፡፡ እኛም የተቃወምነው የአካባቢያዊም ሆነ የጎሳ ቡድናዊ አስተዳደር ይቅር የሚለው ነው፡፡ ጎሳዊ አስተዳደር በደም የሚጠራራ እንጅ ክህሎትን መሰረት ያላደረገ በመሆኑ መላውን አገራችንንም ሆነ አመራን በደለው ነው፡፡ በስርአት የሚመራ ግለሰቦች በአቅማቸው ተወዳድረው የሚኖሩበት አገር ይፈጠር ነው፡፡ የትግራይ ስርወ መንግስት ከዘመኑ ጋር አይሄድም፡፡ ይበቃል ነው ያልነው፡፡ እነርሱ ግን ወደዳችሁም ጠላችሁም እናነት ተገዥ ናችሁ አሉ፡፡ ተገዥና ገዥ የሚለውን ስርአት ለማጥፋት የአማራ ልጆች ቀድመው ተሰልፈው የእሳት ራት ሆነዋል፡፤ በአብዮቱ ጊዜና ከዛ በኋላ፡፡ ያ ትግል ግን በዘመኑ ብሂል ሱፍ ለባሽ በሆኑ በተግባር ግን በትግራይ ፈላች ቆራጭ መሳፍንት ተጠለፈ፡፡ እኛንም ያስመረረን በአገዛዝ ውስጥ መኖር ነው፡፡ እኛ አስተዳደር እንጅ አገዛዝ አንፈልግም፡፡ የማንም የቡድን የበላይነት የማይንጸባረቅበት አገር ይመስረት ነው ያልነው፡፡ ዞሮ ዞሮ እንደ ወንጀል ተቆጠረብን እንጅ ሰሚ አልተገኘም፡፡
4) መገንጠል አያምርብንም ያሉ ይሄንን የሚሉት ደግሞ ተመችቶን ለሽርሽር እንሂድ ያልናቸው ይመስላሉ፡፡ ምርጫ አጥተን እና ተገፍተን የገባንበትን መንገድ የዝነጣ ወይም የጫጉላ አደረጉት፡፡ ዛሬ እናንተ ጫጉላ ቤት ስለሆናችሁ የእኛ ለቅሶ ድንኳን አልታያችሁም፡፡ በጊዜ የቀልዳችሁን ፍሬ ታገኛላችሁ ከማለት በቀር የምንለው የለም፡፡ መገንጠልን ለቁንጅና አልፈለግነውም፡፡ መገንጠልን የፈለግነው የህልውናችንን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ነው፡፡ እናም መገንጠል የውበት ውድድር አይደለም፡፡
5) ትግላችንን ይጎዳል ያሉ ትግለችንን በአንድም በሌላም ይጎዳል ያላችሁ አላችሁ፡፡ ኢትዮጵያዊነት ነው አሁንም ዘይቤያችሁ፡፡ እኛ ኢትዮጵያ የሚባለው ነገር ሀለተኛ አጀንዳችን ነው፡፡ እኛ ሳንገነጠል ቀድማችሁ እኛን በሰውነታችን በእኩልነት የሚያስተናግድ አገር መፍጠር ከቻላችሁ እሰየው ነው፡፡ መንገድ ላይ እንገናኛለን፡፡ በዚህ ላይ ችግር የለብንም፡፡ ይሁንና ገና ለገና የእናንተ ጸሎት ይሰምራል ብለን ራሳችንን ከማንቃትና ከማደራጀት ወደኋላ አንልም፡፡ ሳንጠላለፍ እንታገል፤ መንገድ ላይ ወይም ቀድሞ አንዱ ድል ያደረገበት ቦታ ላይ እንገናኝ፡፡
6) ገና ትረገጣላችሁ እንደሚታወቀው ወያኔ አማራን በጊዜ ሂደት ማዳከም ብሎም በተራዘመ መከራ ማጥፋት እንጅ እንዲህ ድንገት ቀኝ ኋላ ዙር ይላል ብሎ ጠርጥሮ አያውቅም፡፡ እቅዱ አማራ መገንጠልን ሲፈራ በአንቀጽ 39 እያስፈራራሁት ስበዘብዝና ስዘርፍ እኖራለሁ ነው፡፡ የአማራ መገንጠል ለወያኔ ባለ ሶስት ስለት ሰይፍ ነው፡፡ ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡ እናም ብዙዎቹ ዛቱ፡፡ ገና ትረገጣላችሁ አሉ፡፡ የዛቻ መአት አወረዱብን፡፡ ስድባቸው በእርግጥ ብርቅ አይደለም፡፡ ስድብ ማንነታቸው ከሆነ አርባ አመት አልፏቸዋል፡፡ የእነርሱን ብልግና ደግመን ብንናገር እኛው ባለጌ መሆናችን ስለሆነ በደፈነው በክብረ ነክ ቃላት ጭምር እንገንጠል ማለትን ፈሩ፤ አስፈራሩ፤ ዛቱ ብለን እንለፈው-የጉሮሮ ስንጥር የሚባለው ደረሰባቸውና ድንብርብር አሉ፡፡ ግን መደናበር መፍትሄ አይደለም፡፡ ሰከን ብሎ ስህተትና ድክመት ማረምና መፍትሄ መሻት እንጅ፡፡ አለበለዚያ ሌላ ልታቃጥልበት የያዝከው እሳት የራስህ እጅ ላይ መንደዱ ነው፡፡
7) እኛ እኮ አንድ ነን እኛ እኮ አንድ ነን እያላችሁ ባታስቁን ምናለበት-መሳቅ በማንፈልግበት ወቅት፡፡ አንድነትን እያስተማራችሁን…ሰው ለካ ዝም ብሎ አይስቅም፡፡ በየቦታው የምታርደን ወይም ስንታረድ የምታጨበጭብ አንድ አገር ሰርተው የሰጡህ ልጆች መሆናችንን ዘንግተኸው ነው፡፡
8) አባቶቻችን ደም ያፈሰሱባት አጥንት የከሰከሱባት አገር ናት የሚሉ በርከት ያሉት አማሮች የሚያነሱት እሮሮ ደግሞ ያስገርማል፡፡ ኢትዮጵያ ላይ የአባቶቻችን ደም ፈስሷል፤ አጥንታቸው ተከስክሷል ይላሉ፡፡ የአባቴ ደም በፈሰሰበት ሁሉ የእኔም ደም ይፍሰስ ተብሎ የተጻፈ የማናውቀው ህግ ካለ ብትጠቁሙን ደስተኞች ነን፡፡ መሞት አይበቃንም እንዴ፡፡ ሞተን አለማለቃችን የሞት ጓደኞች አስመሰለን እኮ፡፡ በጀ፡፡ እዚህ አገር መኖር ያለብን ለአትንትና ደም ነው ማለት ነው፡፡ ለራሳች አይደለም መኖር ያለብን ማለት ነው፡፡ ማን ነው ግን አባቱ አትንቱ የተከሰከሰብት ቦታ ሁሉ ላይ የልጁም ይከስከስ ያለው፡፡ ደማችን የፈሰሰበት አገራችን ከሆነ ዘንዳ ምነው ኤርትራ ውሰጥ አርባ አመት ሙሉ በተደረገ ጦርነት ከ 100 000 በላይ አብራኮቻችን ሞተው የለም እንዴ፡፤ ወይስ የእነርሱ አትንትና ደም የሰው አይደለም፡፡ በዚህማ ከሆነ ሞቃዲሾም አገራን ነው፡፡ ደቡብ ኮሪም አገራን ነው፡፡ ደቡብ ሱዳንም፤ ኮንጎም፤ ሩዋንዳም አገራን ነው፡፡ የየመን ባህረ ሰላጤም አገራችን ነው ማለት ነው የአሳ እራት የምንሆንበት፡፡
9) ቡና የለንም የሚሉ ቡና አሁንም ገዝታችሁ ነው የምትጠጡት በኋላም ይገዛላችኋል፡፡ ካስፈለገም ይዘመርላችኋል፡፡
10) ባስቸኳይ ነጻ የአማራ መንግስት ይቋቋም የሚሉ በርቱ እንበርታ፡፡
11) የሌሎች ተገንጣይ ድርጅቶች መሳለቂያ ልንሆን ነው የሚሉ አቤት አቤት አሁን ተከብራችሁ ሞታችኋል፡፡ በየጉራንጉሩ እንደእባብ መቀጥቀጥ፤ መገደል. መፈናቀል፤ መዘረፍ፤ መዘለፍ፤ ዘር መጥፋት ሁሉ ክብር ከሆነ መዝገበ ቃላቱ ተለውጣል ወይ እኛ ያልገባን አንዳች ነገር አለ ማለት ነው፡፡ ግን አማራ እውን ክብርና ውርደትን ለይተው የማያውቁ ልጆችም አሉት ማለት ነው፡፡
12) ዜሮ የመጨረሻው በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው፡፡ አንድ እንኳ ጥያቄያችንን ከተጻፈው ህገ መብታዊ መብት አንጻር ያየልን የለም፡፡ ስድቡና ዛቻው ቀርቶ ጥያቄያችንን ብታውቁልን ምንኛ ደስ ባለን ነበር፡፡ ለዚህ ያደረሰንን ልትመረምሩ አልፈለጋችሁም፡፡ እስክታውቁት ከመቀጠል በቀር ሌላ ምርጫ የለንም፡፡ አማራ በዜሮ ተባዝቶ ኢትዮጵያ እንድትኖርላችሁ ነው ምኞታችሁ፡፡ መልካም፡፡ ቸር ይግጠመከን እላችኋለሁ፡፡
መለክ ሐራ