Bete Amhara

Bete Amhara

Saturday, July 4, 2015

ደርቡሽ ጎንደርን ባቃጠላት ጊዜ የተገጠመ ግጥም፡፡

ደርቡሽ ጎንደርን ባቃጠላት ጊዜ የተገጠመ ግጥም፡፡
ጎጃም ለጎንደር ሊበቀልለት ሳር ውሀ ሜዳ ላይ በጀግንነት ተዋጋ፡፡ እድል ግን ፊቷን አዞረች….ጎንደርም ተቃጠለ፤ ጎጃምም ተሸነፈ…ሁለቱ ታላላቅ የአማራ አገረ ግዛቶች በአንድ ጊዜ ተሸነፉ፡፡ ግን ወድቀው አልቀሩም፡፡ ትንሳኤን አደረጉ እንጅ፡፡ በዛ ዘመንም በሸዋና በወሎ የነበረ አማራ ተጠናክሮ ነበር፡፡ ጎንደርና ጎጃም በወሎና ሸዋ መጠናከር ተጽናኑ፡፡ እጅግ ፈጥነው ለማገገምም ምክንያት ሆነላቸው፡፡
*******************************
ወገራ አሳላፊ ደምቢያ እንጀራ ጣይ፡
ተበላህ ጎንደሬ አትነሳም ወይ፤
አትከለክልም ወይ ይዘህ አለንጋህን፡
አሞራ ሲበላው የገዛ ገላህን፡፡