Bete Amhara

Bete Amhara

Wednesday, July 8, 2015

ግንቦት ሰባቶች ስንት ጊዜ ነው አማራን ልታፍኑ የምትሞክሩት?

ግንቦት ሰባቶች ስንት ጊዜ ነው አማራን ልታፍኑ የምትሞክሩት? (Mellek Hara Hara)
************************************************************************************
አንድ ነገር ግልጽ ሆኗል፡፡ ይህ ግንቦት 7 የተባለ ድርጅት እንደሚወራው ጸረ አማራ መሆኑ፡፡ ገና ለገና ስለአማራ ተናገሩ ተብለን ይሄ ሁሉ ዘመቻ ተከፍቶብናል፡፡ እኛ አማራ ነን፡፡ የእናተን ኢትዮጵያ ይዛችሁ ገደል ግቡ፡፡ በሰሞነኛ ዜና ሰበብ እኛን ለማፈን አትሩጡ፡፡ እናንተ ገንዘብ ከፍላችሁን አይደለም፡፡ በነጻ ነው ለህዝባችን እየጻፍን ያለነው፡፡ ደግሞ እንዴት እንዴት ነው የምታስቡት? ጭራሽ ኢንተርኔት በሰጠን እድል እንኳ እንዳንናገር ልትከለክሉን ይዳዳችኋል! ወያኔስ ከእናንተ የተለየ ምን አደረገ? እንዴውም ይህ የሚያመለክተው ወያኔን መሰል ጸረ አማራ አካል እየመጣ መሆኑን ነው፡፡ ለምን ኦነጎች ላይ አትዘምቱም? ለምን አረና ላይ አትዘምቱም? ለምን ኦብነግ ላይ አትዘምቱም? ከስንቱ የብሄረሰብ ድርጅት ጋር ገጥማችሁ እየኖራችሁ እኛ ላይ ችግራችሁ ምንድነው? እኛን ለማፈን የምትሮጡት ለምንድነው? ጦርነት እየተዋጋን ነው ብላችኁዋል፡፡ ለምን የራሳችሁን ስራ አትሰሩም? ማን አትዋጉ አላችሁ? በቃ እኛ ለእናተ ካላጨበጨብን መታፈን አለብን? ደግሞ ወገኖቻችንን የጥይት ሲሳይ ማድረጋችሁ አንሶ ጭራሽ እኛን ልታፍኑ ትሞክራላችሁ፡፡ እኛ ግንቦት ሰባት ይደግፈናል ወይም ይጣላናል ብለን አይደለም የተነሳነው፡፡ የተነሳነው ስለአማራ ለመናገር ነው፡፡ አማራ ስሙ ሲጠራ እንዲህ የምትንገሸገሹት ምን ስለሆናችሁ ነው? ገና ስንት አማራ ማለቅ አለበት ለእናንተ ሲባል? ከመሪያችሁ ጀምሮ የትግሬ አክራሪ አውርጀ “የአማራ አክራሪ አልፈልግም፤ አማራ አማራ አትበሉብኝ” የምትሉ ጸረ አማራዎች እንደሆናችሁ ይታወቃል፡፡ ይህ ማለት እናንተ የምትመሰርቱት መንግስትም ለአማራ ቦታ የለውም ማለት ነው፡፡ አማራን በአክራሪነት እና በጠላትነት ነው የሚፈርጀው ማለት ነው፡፡ የሰሞኑ እኛ ላይ የምታደርጉት ዘመቻም ይህን ወሬ የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ካሁን በኋላ እንዴውም እናንተን መታገል ሳያስፈልግ አይቀርም፡፡ እኛ አማራ አማራ ማለታችን ወያኔ የሚያስብለን ከሆነ እናንተ አማራን ለማፈን የምታደርጉት ጥረት ወያኔ፤ ደርግ፤ ኦነግ እና ሻእብያ ያስብላችኋል፡፡ ዛሬ እንዲህ የምትጨፍሩብን ነገ እድሉን ስታገኙ ምን እደምታደርጉን ስናስበው በጣም አስጊ ሁኔታ ውስጥ እንዳለን ያስረዳል፡፡ እናንተ ድል አደረጋችሁም ድል ሆናችሁም እኛ አማራውን ማንቃት እና ማደራጀታችን እንቀጥላለን፡፡ የአማራ ችግር በመሰረታዊነት በሚደረጉ እርምጃዎች እንጅ በሰሞነኛ ጩኸት የሚፈታ አይደለም፡፡

በጎንደር በኩል ያለን የአማራ መሬት የትግራይ ብላችሁ በዜና ጣቢያችሁ የምታነቡና በግፍ ለተወሰደብን መሬት እውቅና የምትሰጡ ሆናችሁ ሳላችሁ እኛን ወያኔ ለማለት ድፍረት አገኛችሁ፡፡ ከደምሂት ጋር ተስማማችሁ እንዴ መሬታችንን ለመስጠት? ከአሁኑ እያስተዋወቃችሁ ይሆናል፡፡ ልክ ወያኔ እንዳደረገው እናንተም የደምሂትን ጦር ለማግኘት የአማራን መሬት ፈርማችሁ ሰጣችሁ? በምን ሂሳብ ነው የእኛን መሬት የትግሬ እደሆነ አድርጋችሁ ዜና የምታናፍሱት? አንድ ነገር ልንነግራችሁ እንወዳለን፡፡ መሬታችን ተስማምታችሁ ሰጥታችሁት ከሆን እናንተንም እነሱንም ልካችሁን አሳይተን እደምንመልሰው፡፡ በሚዲያችሁ አማርኛ ተናጋሪ ብላችሁ ክብራችንን መግፈፋችሁ ነው እናንተን የእኛ ወገን የሚያስብላችሁ? አማራ ብላችሁ እንኳ ለመጥራት የሚቀፋችሁ ሰዎች ናችሁ እንግዲህ እኛን ወያኔ የምትሉን፡፡ ወያኔ እንኳን ያንን ያህል እያጠፋን ስማችንን አልካደም፡፡ አማራ ብሎ ነው የሚገድለን፡፡ የእናንተው እኮ የተለየ ነው፡፡ ጭራሽ ስማችንን ሁሉ ፍቃችሁታል፡፡ ለእናንተ ስንል እንጥፋ? ወያኔን መዋጋት አማራን ማፈን ማለት መሆኑን አሁን አስረዳችሁን፡፡ አሁን የምታደርጉት ነገር ለእኛ ግልጽ ነው፡፡ አማራው ስለራሱ መናገር እና ማሰብ ስለጀመረ የእኛ የንግድ እቃነቱ ያበቃል የሚል ፍራቻ አላችሁ፡፡ ከዚህ በፊትም ልታፍኑን ስትሞክሩ እንደቆያችሁት አሁን ይሄን የጦርነት ወሬ እንደመልካም እድል በመጠቀም የእኛን ስም ማጥፋት እና ከወገናችን መነጠል ነው አላማችሁ፡፡ ያ ግን አይሳካም፡፡ የእናንተም የሰሞኑ ዜና ይበርዳል፡፡ እናንተም ይሄን ታውቁታላችሁ፡፡ እኛም ስራችንን እንቀጥላለን፡፡ ቢሆን ቢሆን እና አሸንፋችሁ መንግስት ብትመሰርቱ እንኳ አማራን ማደራጀት፤ ማንቃት እና የረሱን ነጻ የአማራ መንግሰት እና አገር ማስረከብ የማይቋረጥ ትግል ነው፡፡ እናንተም ጋር ሆነ፤ ወያኔም ጋር ሆነ ዲያሎስ ጋር ስለአማራ ነጻ መንግስትነት መታገል ይቀጥላል፡፡ የእናንተ የጊዜው ሩጫ ለእኛ ጠላት ማብዛት እና እኛን አስጠልቶ ማጥፋት ነው፡፡ ይህን ግን ወደፊት እናየዋለን፡፡

አማራነት ወደፊት!