Bete Amhara

Bete Amhara

Wednesday, July 8, 2015

የአቋም መግለጫ

የአቋም መግለጫ....
******************
 ወያኔ ትግል ሲጀምር የጻፈውን «አማራን የማጥፋት» ግብ ለማሳከት ዛሬ ስልጣት በያዛበት ዘመን የተለያዩ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ነድፎ አማራውን ሲያጠፋው፤ በሀገሩ ሀገር ሂድ እየተባለ እንደ እብድ ውሻ በያለበት «ና ውጣ» እየተባለ ሲባረርና ሲግደል እያየሁ ይህንን በአማራው ላይ ባማራነቱ ብቻ የሚፈጸም ግፍ መቃወም ዘረኝነት ካስባለ፤
🔺ለዘመናት ተዋልዶና ተዛምዶ ከሚኖረው ከወንድሙ ከኦሮሚያ ህዝብ ጋር እንዲጣላና ደም እንዲቃባ ፀረ-አማራ ሀውልት ሲቆም፤ ቂም በቀል ለትውልድ ሲተላለፍና አማራው ከምድረ ገጽ እንዲጠፋ ትውልድ ሳይቀር በትምህርት ቤት ሲሰለጥን እያየሁ ስለአማራው መጻኢ እድል ድምጼን ከፍ አድርጌ መጮሄ ጎጠኝነት ካስባለ፤
🔺በኢትዮጵያ ባሉት ክልሎች ብቻ ሳይሆን ባለም ላይ ካሉ ህዝቦች ጭምር የመጨረሻ ደሀ ስለሆነው የአማራ ህዝብ መናገሬ መንደርተኛ ካስባለና አማራው ለሺ ዘመናት ያርሳቸው የነበሩ ማሳዎቹና ርስቶቹ እየተገደለና እየተባረረ የአባቶቹ ብቻ ሳይሆን የራሱም ቀላድ በትግራይ ውስጥ ሲካለል፤ አማራው እንዲያንስና አገር አልባ እንዲሆን ከትግራይ የተረፈው መሬቱ ተላልፎ ለጎረቤት ሀገር ሱዳን ሲሰጥ እያየሁ ስለአማራው ህልውና መናገሬ ጠባብነት ካስባለ፤
🔻በሀገሩና በቅዬው እየኖረ እንደ ትግሬው ገበሬና ሌሎችም ኢትዮጵያውያን በላቡና በደሙ የገዘውን ጠበንጃ «አስመዝግብ» እየተባለ ሲቀማና ለጥቃት ሲጋለጥ እያየሁ፤ በትግራይ ገበሬዎች ዘንድ የማተገበር ደንብ በአማራው ላይ እንዲተገበር ልዮ ህግ ሲወጣ እያየሁ በአማራ ላይ የሚፈጸመውን አድሎና በደል መናገር ዘረኛ ካስባለ፤
🔺 አማራን መሳደብ ለስልጣን የሚባበቃ፤ የፖለቲከኛነት ልክ የሚመዘንበት፤ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ የሚያሰጥ፤ የመለስ ዜናዊን የክብር ኒሻን የሚያሸልም፤ ገንዘብና መሬት እንዲሁም የመሳሰሉ ውድ ስጦታዎች የሚያስገኝ መሆኑን እየታዘብሁ ስለ አማራ መናገሬ ዘረኛ የሚያደርገኝ ከሆነ፤
🔺 አማራን ማፈናቀል ከትምህርትና ከስራ ልምድ በላይ ክብደት ያለው የእድገት መመዘኛ ሆኖ አማራን ከክልሉ በግፍ ጠራርጎ በማባረሩ የክልል ባለስልጣን ከነበረበት የስልጣን እርከን ወደ ፌደራል መንግስት የሚኒስትርነት ማዕረግ ሲመነደግ እያየሁ ባደባባይ ስለአማራ መጮሄ ጠባን የሚያስብለኝ ከሆነ፡ ከዚህ በኋላ በአይነትም በመጠንም ወደር ያማይገኝልኝ የገነገንሁ ቁጥር አንድ ዘረኛ ነኝ።
🚩የቀድሞው ጋሻው አለምየ አገኝ እንዳለው ጣሹ


📍የአሁኑ ጋሻው ዘአማራ