Bete Amhara

Bete Amhara

Thursday, July 9, 2015

የአማር ህዝብ ትክክለኛ ሰብዓዊ መሆኑን የምናረጋግጥበት እረቂቅ ነገሮች

የአማር ህዝብ ትክክለኛ ሰብዓዊ መሆኑን የምናረጋግጥበት እረቂቅ ነገሮች ።እያንዳንዳችን ለጥቃቅን ነገሮች ትኩረት ሰጠን እንያቸው ፦የበታችነትም ሆነ የበላይነት ስሜት ስለማያሽንፈው የእናቱም ልጅ ቢሆን ስህተት ከሆነ እሱን ወይም እሷን ለመቃወም ወደኋላ አይልም ። የራሱን የግል ስም እና ዝና እንደሚገነባ እያወቀው ነገር ግን ታላቁን ህዝብ ይጎዳል ብሎ ካሰብ ለደቂቃዎች እንኳ መደራደር አይፈልግም።ግለሰቦች ይህንን አይነት ይዘት ያለውን የአቋም ችግር ሲሉት አስተውላለሁ በፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ይሉኝታ አያስፈልግም ።ይሉኝታን የምንጠቀምባቸው ብዙ ክፍት ቦታዎች አሉ።በእኔ የግል ህይወት ፍልስፍና ብዙሃኑ ህዝብ አይሳሳትም የሚል እመነት አለኝ በቀበሮ ጉድጓድ ውስጥ ሁነህ አሳ ነባሪ ሊታይህ አይችልም ካልህበት እየወጣህ ስትሄድ ልምዶችን እየቀሰምህ ትሔዳለህ ።ሰዎች የአቋም ችግር አለበት ይሉኛል ብለህ ከሰጋህ አንተ ህዝብህን አትወድም እንዲያውም ለእውነት እና እወደዋለሁ ለምትለው ህዝብ ያልቆምህ ውሸታም እና አታላይ ነህ ማለት ነው።

የሰው ልጅ እድሜ በጣም አጭር ስለሆነ በታቻለን አቅም በፍጥነት መልካም ነገሮችን ለመስራት መፈልግ አለብን እላለሁ ።እራስህን ጠይቅ ዛሬ ለግል ስም እና ዝና ብለህ ወይንም ደግሞ ከአፈርሁ አይመልስኝ ብለህ የግራ ዘመም ፖለቲካ ብትከተል መጭውን መከራ የሚሸከሙት ትንሽ ወንድምህ እና እህትህ ናቸው ሲቀጥል ልጅህ ይረከባዋል በእድሜ ወይም በሌላ ምክንያት ከፖለቲካ ጭዋታ ብንወጣ እንኳ የሰላም እንቅልፍ አይወስደንም ህሌናችን ያስረናል ህሌና ትንሹ ፈጣሪ ነው።በህሌና ጥፋት የታሰረን ማንም ፍርድ ቤት ሊፈተው አይችልም ።ሰሞኑን የሚደረገው የስድብ ትግል እኛ ካልነው ውጭ ስህተት ነው የሚሉ ትዕቢተኞች እንኳን ለህዝብ ይቅርና ለአባላቸው ለነበር ሰው እንኳ ክብር ሲሰጡ አላየንም ።የተያዘው የወንድማማቾች የፊስቡክ ስድብ ነገ ወደ ከፋ ደረጃ እንደሚወስድ ለማወቅ ጠቢብ መሆን አያስፈልግም ነበር።ይህንንም በቶሎ ለመገንዘብ ጥልቅ የሆነ አምሮን የሚፈልግ አልነበረም ።
..
ደስ የሚለው የአማራ ሰብዓዊነት ወቃሽ አለን ተንቆንጥጠን ያድግነን በመሆናችን ብዙሃኑ እና ታላቆች የሚሉንን እንሰማለን የማይስማ ካለ ግን ጀርባ መደቡ መጠናት ይኖርበታል ።ለምሳሌ ያክል ሌሎች ማህበረሰቦች ውስጥ ሂደን ምሳሌ እናንሳ አንድ አንድ ትግሬዎች በስራዓቱ እኛም አልተጠቀምንም ይሉናል ይህንን በአደባባይ አውጡት እና በጋራ እንታገለው ስትላቸው ጆሮ ዳባ ለበሰ ይሉሃል ።እንግዲህ አንድ ሰው ለሁለት ጌቶች ሊገዛ አይችልም ።ሕወሓቶች ሰባት ሁነው ሀገር ለማጥፋት ሲነሱ እኛ ወለድናቸው ከሚሉት አባቶቻቸው የተቆጣቸው ማንም አልነበረም እንዲያውም አይዞአችሁ ልጆቻችን አሏቸው ።ሌሎችንም ብዙ ምሳሌዎች ማንሳት ይችላል አስተዳደግ ይወስነዋል ።
የበታችነት ስሜት እንደ በርበሬ የሚያቅጥላቸው ህዝቦች የፊውዳል ስራአት ናፋቂ በማለት ጊዜያቸውን ሲያባክኑ እመለከታለሁ። የአመራው መደብ ገዥ ብለው የሚጠሩት እስከ ደርግ ስራአት ድረስ ስራአቱ መስመሩን ሲስትና ሲበላሽ ከማንም በላይ የተቃውሞውን ድርሻ የሚይዘው አማራው ነው። ዛሬ የትግራይ መደብ ገዥ ይህንን ነጭ እውነታ እየካደ ይገኛል ።የአማራ ገዥዎች ተብለው በሚጠሩት ዘመን አማራ ሌላውን ህዝብ ጨቁኗል የሚለው ወሬ ብቻ መረጃ ሊሆን አይችልም ።መረጃን መረጃ ነው ስላላችሁት ብቻ መረጃ ሊሆንላችሁ ፈጽሞ አይችልም ።
እኛንም ወቃሽ አያሳጣን !!!!!!!!!!!