Bete Amhara

Bete Amhara

Sunday, July 12, 2015

ለመላው ቤተ አማራ ትውልድ የእለቱ መልእክት---ከትልቅ አማራ አንደበት

ለመላው ቤተ አማራ ትውልድ የእለቱ መልእክት---ከትልቅ አማራ አንደበት
=========================================
ለበጎም ሆነ ለክፉ አምላክ እዚህ ቤተ አማራ የተባለ ፕሮጀክት ላይ አስቀምጦኛል፡፡ ከእድሜ አለመብሰል ብዙ ጉድለት አለብኝ፡፡ ይህንን ጉድለቴን ግን የማገኛቸው አማሮች እየሞሉልኝ ነው፡፡ በአንድ ወገን እድለኛ ነኝ እላለሁ፡፡ ምክንያቱም እያንዳንዱ አማራ ባናገርኩት ቁጥር የማይረሳ ምክር፤ ተግሳጽና ትምህርት ነው የሚሰጠኝ፡፡ በሌላ በኩል አዝናለሁ፡፡ ይህ ሁሉ አዋቂ አማራ እያለን ምን ነክቶን ነው ህዝባችን የአለም ቁጥር አንዱ ጎስቋላ ሲሆን ከዛም በላይ የዘር ጥፋት ሲታወጅበት ዝም ያልነው ብየ እገረማለሁ፡፡ እና ዛሬ ያወራሁት እድሜ ዘመኑን በኢትዮጵያዊነት ለኢትዮጵያ የኖረ ትልቅ አማራ የሚከተለውን ቁም ነገር መከረኝ፡፡ ለእናንተም ይበጃል ስላልኩ አካፈልኳችሁ፡፡
እድሜየ ከ50 አመት በላይ ነው፡፡ ጡረታም ወጥቻለሁ፡፡ በቀሪው ዘመኔ አንድ ነገር እመኛለሁ፡፡ አማራ የራሱን ነጻ መንግስት ሳያውጅ እና ሳላየው እንዳልቀር፡፡ ከህይወት የቀረኝ ትልቁ ምኞቴ ይሄ ብቻ ነው፡፡ ከእንግዲህ ለአማራ ከዚህ የበለጠም ትልቅ ነገር የለም፡፡
አማራን ማጥፋት አሁን አይደለም የተጀመረው፡፡ ከሁለት ሽህ አመታት በፊት ጀምሮ ነው፡፡ ሮማዋያን ሊያጠፉን ጀምረው ነበር፡፡ አሁንም ኢትዮጵያን ሊያጠፉ የሚሹ ብዙ ወገኖች አሉ፡፡ ኢትዮጵያን ለማጥፋት አማራን ማጥፋት ብለው ከወሰኑ ቆይተዋል፡፡ እኛ ደግሞ አንጠፋም ባዮች ነን፡፡ የእኛ ትግል ላለመጥፋት የሚደረግ ትግል ነው፡፡ ማሰብ እና መንቀሳቀስ ያለብን ሞት የተፈረደበት መሆናችንን እያስታወስን ነው፡፡ ሞት እንደተፈረደበት ሰው እናስብ፡፡ እንደሞት ፍርደኞች እንስራ፡፡ እኛ የሞት ፍርደኞች ነን፡፡ እና የሞት ፍርዳችንን ወደህይወት ለመለወጥ የተነሳን የህይወት ወታደሮች ነን፡፡
ከውሀ ተማር፡፡ ውሀ ዛፍም፤ ገደልም፤ ድንጋይም ቢያጋጥመው መንገዱን ይሄዳል፡፡ መሄድ ስላለበት ይሄዳል፡፡ ሲሄድ ግን በዘዴ ነው፡፡ ገደልና ተራራን አይጋፋም፤ የጎንየሽ ስስ ብልቱን ፈልጎ በመሸርሸር ወይም በመጠማዘዝ ያልፋል፡፡ የአንተ ጉዞም እንደውሀ ነው መሆን ያለበት፡፡ መጋጨት ሳይሆን ሾልኮ ማለፍ፡፡ ውሀው ስለመጋጨቱ አያስብም፤ ከፊቱ ያለውን ነገር እንዴት እንደሚያልፈው ግን ያስባል፡፡ ለዛም ሁልጊዜ ለራሱ ማለፊያ መንገድ ሲቀይስ መሹለክ በሚችልበት ስስ ብልት በኩል ነው፡፡ የማትጥለውን ነገር አትጋጨው፤ እለፈው እና ሂድ፡፡ መጋጨትህ ማለፍን ሳይሆን ጀብዱህን ነው የሚያሳየው፡፡ ጀብዱ ደግሞ ብቻውን ዘዴ አይደለም፡፡ ከቻልክ ጀብዱን እና ዘዴን አዋህደህ ተራመድ፡፡ ሁለቱን ማዋሃድ ካቃተህ ግን ዘዴን ምረጥ፡፡ በዘዴ የሚራመድ አይወድቅም፡፡ ውሀ በዘዴ ይሄዳል፤ ስለሆን ከመንገዱ ቀርቶ አያውቅም፡፡ አንተም እንደውሀ አካሄድ ሂድ፡፡
አንተንም እኔንም ሊያጠፉ ይችላሉ፡፡ ሀሳቡን ግን ሊያጠፉት አይችሉም፡፡ የመጣው ሀሳብ የማይጠፋ ሀሳብ ነው፡፡ እገሌ ጠፋ፤ እነ እገሌ ጠፉ ተብሎ የሚጠፋ ሀሳብ አይለም የመጣው ሀሳብ፡፡ ከእንግዲህ ይህን አሁን የተዘራውን ሀሳብ የሚያስቀጥለው አማራ በእየለቱ እየበዛና እያየለ ነው የሚመጣው፡፡ ከአንተና ከእኔ የሚበልጡ እሳት የላሱ አማሮች አሁን ይመጣሉ፡፡ እነሱ ሲመጡ ቦታውን ለእነሱ መልቀቅ ነው፡፡ ለምን በአንድ ጊዜ ሃሳቡን አልተቀበሉትም አትበል፡፡ አንተና እኔ ራሳችን ከወራት በፊት ጭልጥ ያልን ኢትዮጵያዊያን ነበርን፡፡ ኢትዮጵያወነት በደማችን ያለ ነገር ነው፡፡ ግን ከመጥፋት መኖር ይሻላል እና ቀስ በቀስ እየገባን መጣ፡፡ አሁንም ብዙው ሰው በቅርቡ ይመጣል፡፡ ራሳችን ችለን ሳንጠፋ የመኖርን ያህል ትልቅ ነገር የለም፡፡ ያንን ደግሞ ሁሉም ይቀበለዋል፡፡ማወቅ ያለብህ እየሰበርን ያለነው የ2000 አመታት አመለካከና አስተሳሰብ ነው፡፡ እንደቀላል አትየው፡፡ ከባድ ነገር ነው እየሰበርን ያለነው፡፡ እና ለምን አልሰሙኝም ብለህ አትፍረድ፡፡ ቀስ ብሎ ሁሉም ይገባዋል፡፡
አሁን ያሉት ገዥዎች አማራን ምን ያህል እንደሚጠሉት አማራው አለማወቁ ነው ትልቁ ችግር፡፡ አንድ ነገር ልንገርህ፡፡ እኔ አብሬያቸው ነው ያደግኩት፡፡ በተለይ በስደት ጅቡቲ ላይ አብሪያቸው እኖር ነበር፡፡ ቋንቋቸውን ስለምችል አማራ አልመስላቸውም ነበር፡፡ ማንነቴንም አልነግራቸውም ነበር፡፡ የሚገርምህ ግን ከአማራ ጋር አብረው ክርስትና እየተነሳሱ፤ ቤተክርስቲያን እየተሳለሙ፤ ማህበር እየጠጡ ብቻቸውን ሲሆኑ የሚያጸባርቁትን ጥላቻ ማመን ይከብዳል፡፡ አብረውት ሲበሉ የዋሉትን አማራ ወይኔ ሳንገድለው ያንን አማራ ብለው በንዴት ያወሩኛል፡፡ በጣም አዝን ነበር፡፡ ይሄንን ግን ለአማራው ብትነግረው አንተን ነው የሚጣላህ፡፡ የአማራው ችግር እነሱን በራሱ አስተሳሰብ እንደራሱ አድርጎ ማሰቡ ነው፡፡ እንደራሱ አድር በራሱ ባህርይ ነው የሚስላቸው፡፡ ግን ስህተት ነው፡፡ አብሯቸው ያልኖረና ያላደገ ሰው በእርግጥ ያላቸውን ክፋትና ጥላቻ ሊረዳው አይችልም፡፡ ይህንን ከ30 አመት በፊት ጀምሮ የማውቀውን ጥላቻቸውን ሳስብ ለአማራ ሁሌ እንዳዘንኩ ነበር፡፡ በኋላ አዲስ አበባን መቆጣጠራቸውን ስሰማ ለስድስት ቀን ቤት ዘግቸ አለቀስኩ፡፡ አማራ ላይ ያላቸውን ጥላቻ ስለማውቀው የሚያደርሱትን መከራ አሰብኩት እና ከሰው ሳልገናኝ ለስድስት ቀን ቤቴን ዘግቸ አለቀስኩ፡፡ የፈራሁትም አልቀረ፡፡ ማናቸውንም የጭካኔ ስራ አማራው ላይ ሰሩ፡፡ አሁንም እየሰሩ ናቸው፡፡ ገናም የባሰ ይሰራሉ፡፡
እና አሁን እንበርታ፡፡ የስራህን ተጽእኖ ዛሬውኑ ካላየሁት አትበል፡፡ ላንተ አይታወቅም ምን አይነት ለውጥ እየተካሄደ እንዳለ፡፡ አሁን አማራው ገብቶታል፡፡ የሚያስደስት ነው፡፡ አንተ የቻልከውን ያህል ስራ፤ ሌላውም የቻለውን ያህል ይሰራል፡፡ በመጨረሻ የቤተ አማራ ነጻ መንግስት እውን ይሆናል፡፡ አንድ ፈላስፋ ያለውን ልንገርህ፡፡ አንድን ዛፍ ሰዎች ተሰብስበው ከቆረጡት በሁዋላ ማንኛው እንደቆረጠው ጠየቃቸው፡፡ ግማሾቹ መጀመሪያ በምሳር የመታው ነው አሉ፤ ሌሎቹ ደግሞ ዛፉ ሊወድቅ ሲል በመጨረሻ የመታው ነው አሉ፡፡ እርሱ ግን የመጀመሪያውም የመጨረሻውም አይደሉም የቆረጡት፤ ዛፉን የቆረጡት ሁሉም በምሳር የመቱት ናቸው፤ ሽህ ሰው የየድርሻውን ቢመታው ያን ዛፍ የቆረጠው ሽህው ሰው ነው አላቸው፡፡
በየለቱ ከትልልቅ አማሮች እንዲህ እማራለሁ፡፡
ቤተ አማራ ወደፊት!
እንቅፋት ወደኋላ