Bete Amhara

Bete Amhara

Tuesday, July 7, 2015

የተቀማ ጩኸት

~-~ የተቀማ ጩኸት 

ያ ምስኪን ገበሬ ሸመቁበት አሉ
ካገር ሊያሳድዱት
ከገዳም ከደብሩ እትብቱ ካለበት
መሸመቁ ሳያንስ 
የወይኑን አፀድቅ እየነቃቀሉ
ስለ ወይን ፈንታ ቀጋ እየተከሉ
ከአባቶቹ እርስት አሳደዱት አሉ
መሰደዱ ሳያንስ
ከእትብቱ ተነቅሎ ከደብሩ ከቅየው
የምስኪኑን በደል ጩኸቱን ቀምተው
የገበሬው ስደት ከየት እስከ የት ነው
የሚል መፅሐፍ ፅፈው
ይሸጣሉ አሉ ገበያ አውጥተው
.
ኤፍሬም ስዩም