Bete Amhara

Bete Amhara

Sunday, July 12, 2015

ነፃ የሚያወጣን እውነት = ቤተ-አማራ

ነፃ የሚያወጣን እውነት = ቤተ-አማራ 
------------------------------------- 
አባቶቻን አያቶቻን ቅድመ አያቶቻችን እስከ ምንዥላታችን እስከ እስከ….ድረስ እንደ አማራ ለዚች ምስኪን ሃገር ዋጋ የከፈለ የለም፡፡ ይህ ዋጋ ግን በጨቋኛ የትግራይ ብሄር ዋጋ ተነስቶት እርግማን ሆኖ የመከራ መዐት እንድንቀበል ሆነናል፡፡ አማራነት ከባህል ከእሴትና ከወግ በዘለለ አጥንትና ደም መሆኑን ያወቁ ወራሪዎች እነሆ በአማራ ላይ ሞት አውጀው መንቀሳቀስ ከጀመሩ ዘመናት አለፉ። ወዳጆቻችን እና ጎረቤቶቻችን ያልናቸው በሙሉ አጥፊዎቻን ሆነው ታሪካችንን ሰርዘው በታሪካቸው ሊተኩት በእንቅስቃሴ ላይ ናቸው፡፡
ነገር ግን ይህ የመከራ ጽዋ ሞልቶ መፍሰስ መጀመሩ እንሆ ቤተ-አማራ ተጸንሳ እንድትወለድ ግድ አለ፡፡ የምስኪኑ የጭቁኑ አማራ ልጆች ተጠራርተው ተነጋገሩ፤ ተነጋግረውም መፍትሄ የሚሉትን ፋና ወጊ ሃሳብ እንካችሁ አሉ። ይህ ዜና የአማራን ዳግም ውልደት አበሰረ። እኔም በቤተ አማራ ወንጌል ተጠምቄ ዳግም አማራ ሆኘ ተወለድኩ። ቤተ አማራም እንደግል አዳኘ ሆነች ፡፡ ከዚህ በኋላ ሌላ ቤት የለንም፤ ያው ቤታችን አንዷ ቤተ-አማራ ናት፡፡
ይህ ሃሳብ ብዙዎችን አስደንግጧል ፤ ብዙዎችን አስጩኋል፤ ብዙዎችንም አስደስቷል፡፡ ሰሞኑን በፌስ ቡክ እያየነው ያለው አርግማንና ውግዘት ለዚህ አይነተኛ ማሳያ ሊሆን ይችላል፡፡ በተለይ ደግሞ ቤተ አማራ እንደ ጠላት ሲፈረጅ መመልክት መቻላችን ትንሽም ቢሆን አስገራሚ ነገር በመሆኑ ይህንን ሃሳብ አንስቼ እንድጽፍ ምክንያት ሆኖኛል፡፡
በመጀመሪያ ግን ይህ ሃሳብ የግሌ እንጅ የማንም ግለሰብ ሆነ ማህበረሰብ አቋም ያለመሆኑ ሊታወቅ ይገባል። ይህ ከሆነ ዘንዳ ሀሳቤን ለማቅረብ ያስደፈረኝ “በአንድነት” ሃይሎች በኩል የቤተ-አማራ አጀንዳ አቀንቃኞች ላይ እየተወሰደ ያለውን ውግዘት በተመለከተ ነው፡፡ ጉዳዩን ይበልጥ የከረረ የሚያደርገው ደግሞ አመክኖዮታዊ ክርክር/ውይይት አድርጎ የሃሳብ የበላይነትንና መተማመን ደረጃ ከመምጣት ይልቅ ተራ መወነጃጀል፤ መሰዳደብ ለዚያወም አንድ መሆን በሚገባቸው አማሮች መካከል ሆኖ ሲታይ ጉዳዩን ለመረመረው የኢህአፓን የትግል ሂደቶች የሚያስታውስ ይመስላል፡፡ ስለዚህ መነጋገርን መሰረት ያደረገ ትግል በሁሉም ሃይሎች ዘንድ ሊኖር ሲገባው ወደ ተራ ስድብ ደረጃ ወርዶ የሰዎች ስብዕና ሲበሻቀጥ ማየትም መስማትም ይከብዳል። ስለሆነም ሃሳብን በሃሳብ እንጅ ስብእናን በማንቋሸሽ የሚመጣ ለውጥ ባለመኖሩ ይህ ጉዳይ ሊታሰብበት ይገባል እያልኩ የግል ሃሳቤን ለማቅረብ እሞክራለሁ፡፡
1. ቤተ-አማራነት ለምን አስፈለገ፡-
ይህ ወሳኝ ጥያቄ መመለስ የነበረበት ከሃያ ምናምን አመት በፊት አማሮች ከነ ህይወታቸው ገደል ይለቀቁበት፤ ቤታቸው በላያቸው ላይ ተቆልፎ እሳት ይለቀቅባቸው በነበረበትና ከየቦታው በሚፈናቀሉበት ወቅት መሆን ቢገባውም በወራሪዋ ትግሬ ብሄር አቀናባሪነት የግፍ አይነቶች መቀበላችንና እንደ ማህበረሰብ መጥፋት ወደሚባል ሁኔታ እየገባን ያለን በመሆኑ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ በዋነኝነት እራሳችንን እንኳ እንዳንከላከል ምክንያት የነበረው አንድነትና ኢትዮጵያዊነት የሚል ያረጀና ያፈጀ ካባ ደርበን ራሳችንን ከጥቃት መከላከል ያለመቻላችንን እና የጥቃቶቹና ዘር የማጥፋት ሂደቱ በትግሬ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ብሄሮች ጭምር መቀጠሉና አማራን በጠላትነት የመፈረጅና በተገኘበት ሁሉ ለማጥቃት የሚደረጉ ድርጊቶች በግድ አፋጣኝ መልስ የሚያሻው መሰረታዊ ጥያቄ ላይ እንድናተኩር አድርጓል፡፡ ይህም ብቸኛው ራሳችንን የምነከላከልበት አማራጭ ስለሆነ ነው፡፡
2. አንድነትና ወድሟል፡-
አንድነት ወይም ኢትዮጵያዊነት በተግባር ቢፈተሹ ድራሻቸው የለም። አሁንም ኢትዮጵያ የሚባል ሃገር የሚኖረው የትግሬን ጥቅም እስካስከበረ ድረስ እንጅ በብዙ መልኩ ከተለያየን ቆይተናል። ይህ በዘር ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ ባፈቀደን እንዳንኖር፤ እንዳንሰራነና እንዳንንቀሳቀስ ከማድረጉም በላይ በተለይ አማራው ላይ ያስከተለው መከራ በቁጥር አይዘለቅም፡፡ የአማራ ቀንደኛ ጠላትም ይህ ሃሳብ ነው ብሎ መደምደም ይቻላል፡፡ ስለሆነም ጥቅሜንና እኩልነቴን ያላረጋገጠች፤ ለአማሮች ሲኦል የሆነች ኢትዮጵያ ልትኖር አይገባትም፡፡ ስለዚህ አማራ ይቅደም የሚል ማደማደሚያ ላይ እንድደርስ አድርጎኛል፡፡
3. አንጀራ ሃገር ኢትዮጵያ፡-
እች ሃገር ላንዱ ሃገር ስትሆን ለሌላው ደግሞ የእንጀራ ሃገር ሆናለች። ለዚያውም ክፉ የእንጀራ ሃገር። በተለይ የዚህ ማስረጃው አማራው ላይ የሚፈጸሙ ግፎችን አድሎዎችን መመልከት ይቻላል። ይህ ግፍ ሃገር አለን እንዳንል አድርጎናል፡፡ በማህበራዊውም ሆነ በኢኮኖሚው ዘርፍ ጭምር አማራ ላይ እየደረሰ ያለውን ማግለል መመልከት ይቻላል። እዚህ ላይ ግብር በመክፈልና በስነ ህዝብ ፖሊሲ ትግበራ አንደኛ ስንሆን በኢኮኖሚ ከአለማችን የመጨረሻው ህዝብ መሆናችን ብቻ መመልከት በቂ ነው። ታዲያ የኢኮኖሚ እድገቷ 11 በምናምን ፐርሰንት በሆነባት ሃገር እንዴት አንድ ብሄር አማራ ብቻ የአለማችን ደሃ ሆነ የሚለውን ጥያቄ ግምት ውስጥ ልታስገቡት ይገባል የሚል ምልከታ አለኝ፡፡
4. ማን ነጻ ይውጣ ማንስ ነጻ ያውጣ፡-
በመጀመሪያ ነጻነት አብሮን የተፈጠረ እንጅ ከማንም በችሮታ የምናገኘው አይደለም፡፡ ስለሆነም እንደ ግለሰብም ሆን እንደ ማህበረሰብ ነጻ መውጣት ያለብን እኛው ራሳችን ነን፡፡ ነጻ አውጭ ከየትም ሊመጣልን አይችልም። መሲህም አያስፈልገን። ስለሆነም አማራ ራሱን ነጻ ማውጣት አለበት። አማራም ብቻ ሳይሆን ተጨቆንኩ ያለ በሙሉ ራሱን ነጻ ለማውጣት መስራት ይጠበቅበታል። ነጻነት በግለሰብ ነው፤ በብሄር ነው፤ ወይንም በሃገር ደረጃ ነው የሚል ቅድመ ሁኔታ ያለ አይመስለኝም፡፡ አዋጭ የሆነውን የመምረጥ ጉዳይ እንጅ፡፡ አማራ ተደራጅቶ ራሴን ከመጥፋት እከላከላለሁ ማለት በምንም ሚዛን ስህተት ሊሆን አይችልም፡፡ ይህኮ የመኖርና ያለመኖር ጥያቄ እንጅ ተራ የመብት ጥያቄ አይደለም ። ሰው የወተት ዋጋ ረከሰ ብሎ ሰላማዊ ሰልፍ በሚወጣበት ዓለም እየጠፋሁ ነው ብሎ መታገል ችግሩ ምንድነው? ስለዚህ አማራ ነጻ አውጭ አያስፈልገውም፤ ራሱን ነጻ ያወጣል፤ አማራ የወላድ መካን አይደለም፤ ደሙን እሚመልሱ ትንታግ ልጆች አሉት፡፡ በአቋራጭ የሚመጣ ነጻት የለም፡፡
5. የወያኔ ውድቀትና የኢትዮጵያ አንድነት፡-
የዚች ሃገር ችግርም ሆነ በተለየ ደግሞ የአማራ ችግር ወያኔ በመውደቁ ብቻ እሚፈታ የሚመስላቸው ሰዎች ብዙ እንደሆኑ መገመት አያዳግትም፡፡ እስኪ በጽሞና አስቡትና ይህ ችግር ወያኔ በመውደቁ ብቻ እሚቆም ይመስላችኋል? የቆመልን የጥላቻ ሃውልት ተመልከቱ፡፡ በአማራነታችን የተሰጠን ስም አስቡ ። ይህ ችግር ላለመቀጠሉ ማረጋገጫችን ምንድነው? ሌሎች ኢትዮጵያዊ የምትሏቸው ስለኛ ያላቸውን አስተያየት እስኪ አስተውሉ። ምኑ ነው ከሌላው ጋር ሊያኖረን የሚችለው? ከዚህስ በሁዋላ ከገደሉን፤ ካቃጠሉን፤ ካባረሩን ጋር በሰላም የምንኖርበት ሁኔታ እንዴት ተመልሶ ሊመጣ ይችላል? ይህ ጉዳይ መልስ ያሻዋል፡፡
6. የ"አንድነት" ሀይሎችን የጎሪጥ፡-
ሲጀመር መሰረቱ የአማራ ወጣት ቢሆንም አማራን ጥሎ አማርኛ ተናጋሪዎችን ብቻ የተቀበለና ስለ አማራ ህልውና አንዳችም ሲል የማይሰማ ነው፡፡ እናም የጎሪጥ እመለከተዋለሁ። ስለሆነም ይህ ቡድን በመጀመሪያ አማራነቴን፤ ከዚያም ኢትዮጵያዊነቴን መቀበል ግድ ይለዋል ። አማራነቴን ነጥቆ ኢትዮጵያዊ ለማድረግ መሞከር ቂልነት ነው። ለዚህ ሃሳብ ብቻ በግልጽ አቋሙን እስካላሳወቀ ድረስ መጠርጠሬ አይቀርም። ነጻ አውጭህ ነው በዚያ ላይ የጠላትህ ወያኔ ጠላት በመሆኑ ምናምን የሚል ሂሳብ አይሰራም። የለህም ብሎኝ ሲያበቃ ነጻ ሊያወጣኝ አይችልም። የሌለ ነገር ነጻ አይወጣማ። አስፈላጊም ከሆነ የራሳችሁን ታገሉ። የቤተ አማራን ጉዳይ ለሚመለከተው አማራ ተውት።
7. እውነቱ፡-
ይህ መላው አማራን ነጻ የሚያወጣ፤ የተጣለበትን ቀንበር ሰብሮ ወጥቶ ወደቀደመው ክብሩ የሚመልሰው፤ ታሪኩን ወግ፤ ባህሉንና እንዲሁም ማንነቱን አስጠብቆ እንዲኖር የሚያደርገው ሃቅ ነው፡፡ ይህ አማራ በራሱ ልጆች የሚመራበት የማንም ባንዳና ሆዳም መጫወቻ የማይሆንበት፤ እንደ መዥገር ላዩ ላይ ተጣብቀው የሚቦጠቡጡትን ተባይ ሁላ ከራሱ አራግፎ የተባረከችውን ምድሩን በረከት የሚቋደስበት እውነት ነው፡፡ ይህ አማራ አማራ በመሆኑ ብቻ ይደርስበት ከነበረው ግፍ ራሱን ነጻ አውጥቶ አማራ አማራ የሚሆንበት ሚስጥር ነው፡፡ ይህ እውነት በአንድነትና በኢትዮጵያውነት እሳቤ ተሸሽጎ የነበር ዛሬ በአማራ ውድ ልጆች ተፈልጎና ተፈንቅሎ የወጣ ሃቅ ነው፡፡ ቤተ-አማራ እውነት ነው ለዚያውም ነጻ የሚያወጣን እውነት፡፡
አማራነቴን (እውነተኛ ማንነቴን) ትቸ ከንቱ በነበርኩበት ጊዜ ከእንቅልፌ ቀስቅሳችሁ ላነቃችሁኝ በሙሉ ረዥም እድሜና ጸጋ ይስጥልኝ፡፡
ድል ለአማራ ህዝብ!!!!

‪#‎Solomon_Haile‬ እንደጻፈው