አማራን አከርካሪውን ሰብረነዋል ሲሉ
------------------------------------
አማራን አጥፍቶ ትግራይን መገንባት የሚለው መርህ አርባ አመታትን ያለምንም ለውጥ ተሻግሮ እዚህ ደርሷል፡፡ የወያኔ ዋና ዋና ጸረ አማራ ቃላትም ማዳከም፤ አከርካሪውን መስበር፤ እንዳያንሰራራ አድርጎ መቅበር፤ ቅስሙን መስበር፤ ማሽመድመድ፤ ማሸማቀቅ….. ናቸው፡፡ በሁሉም ዘርፍ ለአርባ አመታት እንዲህ ነው ሲደረግብን የቆየው፡፡ አሁንማ በተለይ ብሶበታል፡፡
------------------------------------
አማራን አጥፍቶ ትግራይን መገንባት የሚለው መርህ አርባ አመታትን ያለምንም ለውጥ ተሻግሮ እዚህ ደርሷል፡፡ የወያኔ ዋና ዋና ጸረ አማራ ቃላትም ማዳከም፤ አከርካሪውን መስበር፤ እንዳያንሰራራ አድርጎ መቅበር፤ ቅስሙን መስበር፤ ማሽመድመድ፤ ማሸማቀቅ….. ናቸው፡፡ በሁሉም ዘርፍ ለአርባ አመታት እንዲህ ነው ሲደረግብን የቆየው፡፡ አሁንማ በተለይ ብሶበታል፡፡
የአማራን አከርካሪ መስበር ብዙ ዘርፎች አሉት፡፡ የመጀመሪያው ወታደራዊ እርምጃ ነው፡፡ ወያኔ አማራ ብሎ የሚጠራውን ደርግን በወታደራዊ ጦርነት አሸንፎአል፡፡ በደርግ ሰበብም አማራ ደህና ወታደር እንዳይኖረው አደረገ፡፡ ከደርግ የተረፉትን በሰበብ አስባቡ አዳክሞ ጨረሳቸው፡፡ በራሱ ሰራዊት ውስጥ መልምሎ ያስገባቸውን አማሮች ወደላይ እንዳያድጉ የአፓርታይድ ጣሪያ ደፋባቸው፡፡ በዚህም አማራ በአገሩ ወታደራዊ መስክ የተገለለ ብሎም አከርካሪው የተሰበረ ሆነ፡፡ በፖሊስና ደህንነት ክፍልም እዲሁ፡፡ አማራ ፖለቲካዊ ደህንነት ውስጥ ድርሽ እንደማይል ይታወቃል፡፡ የማይጠቅሙም የማይጎዱም የኢኮኖሚና መሰል ደህንነት ስራዎች ብቻ ውስጥ ይሳተፋሉ--ለዛውም በጆሮ ጠቢነት ደረጃ፡፡ በዚህም አማራ ለአገሩ ጥቅም የማያበረክት እና ከአገሩም የማይጠቀም ሆነ፡፡ ወያኔ በወታደራዊ፡ ፖሊስና ደህንነት ዘርፎች ውስጥ በዚህ መልክ አማራን ከጨዋታ ውጭ አድርጎ ሁሉንም አጋፍፎ ያዘ፡፡ በዚህም አማራው አከርካሪው የተሰበረ ሆነ፡፡
በመቀጠልም ፖለቲካዊ አከርካሪ ሰበራ ውስጥ ተገባ፡፡ እንደሚታወቀው ከአማራ መካከል ተፈልገው ወደቡችልነት የሚመጡት ማሰብም ሆነ መናገር የማይችሉት ተረፈ ህዝብ ናቸው፡፡ አንድ ነገር ከወያኔ የምታደንቅለት ብትሉኝ ሆድ ተኮርና አይሞቄ አይበርዴ ሰዎችን የማግኘት ጥበቡ ነው፡፡ ወያኔዎች የሆነ ከንቱ አነፍናፊ መሳሪያ ሁሉ ያላቸው ይመስለኛል፡፡ እስኪ በቡችልነት የሚያገለግሉትን ሰዎች ልብ ብላችሁ እዩአቸው፡፡ አንድ እናት የወለደቻቸው ነውኮ የሚመስሉት፡፡ እና ወያኔ ለህዝባቸው የሚቆረቆሩትን፤ ችግርን በፍጥነት ተገንዝበው መፍትሔ የሚያበጁትን፤ የወገናቸው ፍቅር የሚያንገበግባቸውን፤ ከሆድ በላይ ህሊናና ክብር አለ ብለው የሚያስቡትን፤ እውቀትን የሚወዱትን፤ ለራሳቸው ሳይሆን ለህዝባቸው የሚኖሩትን ብርቅየ የአማራ ልጆች ወደአመራርነትም ሆነ ወደፖለቲካው መስክ ድርሽ እንዳይሉ ሌት ተቀን ይሰራል፡፡ በምትኩ በእነዚህ ድኩማን ፍጥረቶች እነዛን ብርቅየዎችን ይደቁሳቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀሱትን አማሮች የተለያየ የሽብር ክስ በመጠምጠም ያስራል፤ ያሰቃያል፤ ይገድላል፤ ያሰድዳል፤ ያሳድዳል…..በዛም አለ በዚህ አማራ ከአገሪቱ ፖለቲካዊ ህይወት ውስጥ ሰባራ አስተዋጽኦ በማያደርግበት ሁኔታ አከርካሪው ተሰብሯል፡፡ ይህም ማለት የኢትዮጵያ ፖለቲካ አማራን እዲያገል ወይም ድርሽ እንዳያደርግ ሆኖ ነው የተሰራው ማለት ነው፡፡ ወያኔ ይህንን አማራን የማግለል እና ፖለቲካዊ አከርካሪውን የመስበሩን ጥረት ቀጥሎበት ይገኛል፡፡ ባጭር ቃልም ወያኔ ፖለቲካዊ አከርካሪ ሰበራ ጦርነት ላይ ነው ያለው ማለት ነው፡፡
ወያኔ የሁሉም መሰረት የሆነውን የአማራውን የኢኮኖሚ አከርካሪ በተሳካ ሁኔታ መስበር ችሏል፤ አሁንም ይህንን ኢኮኖሚያዊ አከርካሪ ሰበራ በሀይል ተያይዞት ይገኛል፡፡ አማራን ሊጠቅሙ ይችላሉ፤ ሀብት እንዲኖረው ያስችላሉ የተባሉ ነገሮች በሙሉ ተዘመተባቸው እና በአማራ ምትክ የትግራይ ከበርቴዎች እንዲወለዱበት ሆነ፡፡ የመጀመሪያው ከወሎ እና ጎንደር ለም መሬቶችን መውሰድ ነው፡፡ እነዛ መሬቶች ለወያኔ ሁለት ጥቅም አላቸው፡፡ የትግራይን የቆዳ ስፋት በመጨመር እና ሀብቷን ማደርጀት እና በተቃራኒው አማራውን መሬቱን መሸብሸብ እና የኢኮኖሚ አቅሙን ማዳከም ናቸው፡፡ ትግራይ እየሰፋች እና እየጎለበተች በሄደች ቁጥር አማራ እያነሰና እየተዳከመ ይሄዳል፡፡ ይህም በትክክል ተግባር ላይ ውሏል፡፡ ገናም ወደፊት ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ አማራን ፈጽሞ ማጥፋት እውን እስኪሆን ድረስ….. የሰው መሬት ወስደው እንዴት በኋላ መልሱ መባላቸው ሳይታያቸው ቀረ ብላችሁ ለምታስቡ መልሱ ወዲህ ነው፡፡ ቀስ በቀስ አማራን እያዳከሙ፤ መሬቱን ደረጃ በደረጃ እየወረሩ፤ ህዝቡን በልዩ ልዩ ሰበብ እያስደዱና እየገደሉ መላ አማራን ይውጧታል፡፡ በዚህም ስኬት የድንበር ይገባኛል ጥያቄ ተደመደመ ማለት ነው፡፡ በዚህ ከቀጠለ አማራን ማጥፋቱ የጥቂት አመታት ብቻ ጥረት ስለሚሆን እንኳን ድንበሩን መሀሉን የሚጠይቃቸው የለም፡፡ እናም የሰው መሬት በየጊዜው ሲወስዱ በመጨረሻ ጠያቂ እንደማይኖራው እርግጠኞች ስለሆኑ ነው፡፡ የአምናው መሀል የዘንድሮው ድንበር፤ የዘንድሮው መሀል የከርሞው ድንበር እያለ እያለ ይቀጥልና አንድ ቀን የአሁኑ ኦሮሚያ ድንበር ይደርሳሉ፡፡ ያኔ ደግሞ ምን እንደሚገጥማቸው ወይም ምን መላ እንደሚዘይዱ አላውቅም፡፡
የዚህ አማራን በኢኮኖሚ የመስበር እርምጃ በመሬት ዘረፋ ብቻ አያቆምም፡፡ አማራን ፈጽሞ ማደህየት የሚለው ቀጣይ እርምጃ አለ፡፡ አማራ እንደሚታወቀው ምድር ላይ ካሉ ህዝቦች ቁጥር አንዱ ደሀ ነው፡፡ ይህ የተደረገው ደግሞ በወያኔ አማራን የማዳከም መርህ መሰረት ሆነ ተብሎ ስለተሰራበት ነው፡፡ የአማራ ነጋዴዎች በሰበብ አስባቡ ከውድድር ውጭ ይደረጋሉ፡፡ የተጋነነ ታክስ ይጣልባቸዋል፡፡ ገደብ የለሽ እገዛ ከሚደረግላቸው የወያኔ ነጋዴ ተብየዎች ጋር እዲወዳደሩ ይደረጋሉ፡፡ ያ ራሱ ብቻውን ድኩማን ያደርጋቸውና በመጨረሻም ከገበያ ያስወጣቸዋል፡፡ በአማራ አገርም ውስጥም ሆነ በሌላ አካባቢዎች አማራን ከጨዋታ ውጭ በማድረግ በትግሬ ባለሀብቶች እንዲያዙ አድርገዋል፤ እያደረጉም ናቸው፡፡ ዛሬ በአብዛኛው የአማራ ከተሞች እንኳን ትልልቆቹ የንግድ እንቅስቃሴዎች ትንንሾቹም በትግሬ የተያዙ ናቸው፡፡ በዚህም አማራው አከርካሪው መሰበር ብቻ ሳይሆን እግር ከወርች እደታሰረ እንገነዘባለን፡፡
በአማራ አገር የሚበቅሉ የአዝርእት አይነቶች እና እንስሳት ወደመሀል አገር ሲገቡም ሆነ ወደ ውጭ ሲላኩ በትግሬ ተማኝነት ነው እንጅ በትክክለኛ ዋጋቸው አምራቹን አማራ በሚጠቅም መንገድ አይደለም፡፡ በዚህም ስውር የሆነ የእዝ ኢኮኖሚ በአማራው ላይ እየተተገበረ እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ እንደሰሊጥና ጥጥ የመሳሰሉ ምርቶች በተለይ አምራቹን አማራ ሳይጠቅሙ በተመን በትግሬ ከበርቴዎች ይጋዛሉ፡፡
አማራን በእንስሳት ሀብት ማራቆት ዋናና እና እጅግ አደገኛው እርምጃ ነው፡፡ ይህ በተለይ ይዋል ይደር የማይባል ችግር እና በቻልነው ሁሉ ተረባርበን ልናስቆመው የሚገባ ነው፡፡ እንደሚታወቀው የአማራ የህይወት ምሰሶዎች መሬትና ከብት ናቸው፡፡ ይሁንና ወያኔ ገበሬውን በቀላሉ ለማስደድ እና አማራን የማጥፋት ህልሙን እንዲያፋጥንለት በሚል መነሻ ዛሬ ማንም ከሁለት ወይም ሶስት ከብቶች በላይ እንዳይኖሩት ደንግጓል፡፡ የወል የግጦሽ ቦታውችንም በመከልከል ማንኛውም ገበሬ ከብቶቹን እቤቱ አስሮ እንዲያስቀምጥ አድርገዋል፡፡ የከብቶች ቁጥር እንዲያንስ መደረግ በሚሞቱት ምትክ ያለማዋለድን መጣል፡፡ ያ ማለት ደግሞ ጥገቶች እና በሬዎች አይኖሩም ማለት ነው፡፡ የአማራ መሬት ደግሞ ያለበሬ በእንጨት ጫር ጫር ተደርጎ የሚታረስ ባለመሆኑ ገበሬው በቀጥታ ስደተኛ ነው የሚሆነው፡፡ ይህ በእውነቱ የአማራን አከርካሪ ከመስበርም ያለፈ ከባድ ችግር ነው፡፡
እንደሚታወቀው በአገሪቱ አብዛኛው ሲቪል ሰርቪስ ሰራተኛ አገልጋይ አማራ ነው፡፡ እስካሁን ሰው ሁሉ ያልተገነዘበው የሲቪል ሰርቪስ ፖሊሲ አማራን ለማደህየት ሆነ ተብሎ የታቀደ መሆኑን ነው፡፡ ሲቪል ሰርቪሱን ማሽመድመድ በቀጥታ አማራን ማሽመድመድ ማለት ነው፡፡ የሌላ ብሔረሰብ ሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች በጎንዮሽ መሬትም፤ ሌላም ጥቅማጥቅም እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡ ላላደጉ ክልሎች ተብሎ የሚደረገው ማበረታቻ እና የብሔረሰብ ተዋጽኦ የሚሉት ፈሊጦች የዚህ ከአማራ ጋር ሊወቀጥ ለነበረ ሲቪል ሰርቪስ ሰራተኛ የጎንዮሽ ካሳዎች ናቸው፡፡ በብሄረሰብ ተዋጽኦ ሰበብ ብዙ የፖለቲካ ስብስብም ለሌሎች ብሔረሰቦች ስለሚሰጥ በተዘዋዋሪ የዚህ እድል ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ አማራ ግን እዳይኖርም እንዳይሞትም በሚያደርግ ስውር ደባ ውስጥ እንዲኖር ይደረጋል፡፡ ለዛውም ሲቀጠር በስንት አድሎ፤ በስራው ላይ ለመቆየትም ስንት መከራ እየጠበቀው፤ እየተባባረና እድገት እየተከለከለ ወዘተ ነው የሚኖረው፡፡ ዛሬ በዚህ ስውር ደባ የተነሳ ሲቪል ሰርቪስ አገልጋይ የሆነው አብዛኛው አማራ ከባርነት በማይሻል ኑሮ ውስጥ ይኖራል፡፡ ሀብት፤ መሬት፤ ቤትና ሰላም የለውም፡፡ ይህም የረቀቀ አማራን አከርካሪውን የመስበር ዘመቻ ነው፡፡ በዚህም አማራ እየሰራ የሚራብ የ“መንግስት” አገልጋይ ሆነ፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ የሚነሳው ትምህርት የሚያስገኘው ጥቅም እና ከአማራ ጋር ያለው ግንኙነት ነው፡፡
በታሪክ አጋጣሚም ይሁን በሌላ አማራው ትምህርትን የሙጥኝ ይላል፡፡ በትምህርት ዝግጅት ልክ የስራ እድልና የገቢ ከፍ ማለት የተባለው ልማዳዊ አሰራር ታዲያ አማራን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነበር፡፡ ይሁን እንጅ አማራን ለማዳከም ባለው መሰሪ ተንኮል የተነሳ ወያኔ የትምህርትን ዋጋ ከስኳር ቸርቻሪ ባለሱቅ አሳነሰው፡፡ ይህም በረጅም ጊዜ የትምህርትን ዋጋ አፈር በማብላት ትምህርት ጠል አማራ መፍጠር እና የመጨረሻውን አማራን አደህይቶ ብቻ ሳይሆን አደንቆሮ መግዛትና ማጥፋት ለሚለው እቅዱ ማመቻቸት ነው፡፡ በዚህም አማራው በትክክል አከርካሪው ተሰብሯል ብለን እንደመድማለን፡፡
ጠቅለል ተደርጎ ሲታይ ወያኔ የተያያዘው አማራን ሞራሉን መስበር፤ ማዳከም፤ መሬቱን መንጠቅ፤ ማሰደድ፤ ማደህየት፤ ማደንቆር፤ አከርካሪውን መስበር፤ አንገቱን መቁረጥ፤ መቅበር…..ነው፡፡ በአማራ መቃብር ላይ አዲሲቷን እና ታላቋን የትግራይ ሪፑብሊክ መገንባት ነው፡፡
አንተ የኔ ወንድም--የእናቴና የአባቴ ዘር ተኛ፡ ምክንያታዊ ነኝ እያልክ እኛን ተከራከር፤ ዘረኛ አይደለሁም እያልክ አይንህን ጨፍን፤ በምትጣልልህ ኩርማን እንጀራ ተደለል፤ ከወንድሞችህ ጋር አትተባበር፤ ዳር ላይ ሆነህ ተመልከት…. ከዛም መቃብርህ ላይ ሌላ አገር ተገንብቶበት ታገኛለህ፡፡ በስጋህ ያልደነቀህ በነፍስህ ይደንቅህ ይሆን….?
ድል ለአማራ
መለክ ሐራ ከቤተ አማራ
መለክ ሐራ ከቤተ አማራ