Bete Amhara

Bete Amhara

Wednesday, June 17, 2015



ለአማራ ልጆች እንደማሳሰቢያ
በእውነትና በንጹህ ስሜት እናገራለሁ፡፡ ዛሬ መኖርን የከለከለን ወያኔ የበቀለው ከትግራይ እንደመሆኑ መጠን በአማራ ላይ ያላውን ጥላቻ ለመመርመር ብዙ ጣርኩ፡፡ አማራ በእውነት አብረን እንኑር አለ እንጅ ብቻየን ልኑር አላለም፡፡ ሀብት እንኳ ባይኖራችሁ ኑ አብረን እንኑር አለ እንጅ የራሳችሁ ጉዳይ አላለም፡፡ ከትግራይ አንድ ኩባያ እህል ወደአማራ አልመጣም፡፡ ምንም የተነካባቸው ነገር የለም፡፡ ሳስበው ሳስበው አማራ መልካም እንጅ ክፉ አድርጎባቸው አያውቅም፡፡ በጎው ነገር ነው ወደክፋትነት የተመነዘረው፡፡ እየሆነብን ያለውን ሳስብ ምነው ቢቀርብን፤ ምንም ላናተርፍ አገር አገር ባልን እንዲህ የምንጠበሰው ስለምንድነው እላለሁ፡፡ ቢቀርብንስ፤ ተወልደን አድገን በሰላም በራሳችን ቤት ብንኖር ምንድነው ክፋቱ እላለሁ፡፡ ህዝባችን ሳይሰደብ፤ ሳይታሰር፤ሳይሸማቀቅ፤ ሳይዘረፍ፤ ሳይዘለፍ፤ ሳይገደል በሰላም በቤቱ ውሎ ቢገባ ይሻላል፡፡ በሰላም አምልኮቱን እያከናወነ ቢኖር ይሻላል፡፡ ሰፊዋ ኢትዮጵያ ቀርታበት በሸዋ፤ በጎንደር፤ በጎጃምና በወሎ እየተንቀሳቀሰ ቢኖር ይበጃል፡፡ በሰላም መኖርን ቀላል ያደርጋል ሰው፡፡ ውሀን ከቀለብ ጤናን ከእድሜ የሚቆጥረው የለም ይላል አባቴ፡፡ አባቴ እውነትክን ነው፤ ትልቅ ኢትዮጵያ እያልን ስናልም ጭራሽ መኖርም ብርቅ ሆኖብን አረፈው፡፡ ባለንበት በሰላም መኖር ለካ ከአጉል የትልቅነት ምኞታችን በስንት ጣእሙ ይሻል ኖሮአል፡፡
ለማንኛውም ከዚህ በኋላ ማድረግ የሚገባንን ልጠቁም፡፡ ሰላማዊ ትግል ማለት ንቁ አማሮችን ለእርድ አቅራቢ ነው፡፡ በሰላማዊ ትግል ሰበብ ንቁ የሆኑ እስር ቤት ገብተው ፍዳቸውን ያያሉ፡ ይገደላሉም፡፡ እስካሁን ተመንጥረው የተያዙት የአማራ ልጆች አብዛኞች ከመንገድ ላይ የታፈሱ ሳይሆኑ በሰላማዊ ትግል ሰበብ ተመልምለው ለአራጆች የተላለፉ ናቸው፡፡ ምርጫ የሚባለው ነገር ፈጽሞ ሊሰራ የማይችል መሆኑን አለማወቅ ራሱ የዋህነት ነው፡፡ ሰላማዊ ትግል አደርጋለሁ ባዩ ነው ሞኝ እንጅ ወያኔዎች በግልጽ ተናግረዋል፡፡ በደም መስዋእት ብቻ እንደሚወርዱ፡፡ እነሱ እያካሄዱት ያሉት በዘመናዊ አለም የጥንቱን ስርወመንግስታዊ ስርአት ማራመድ ነው፡፡ አሁንም የትግራይ ስርወ መንግስት ጠባቂዎች ናቸው፡፡ የድሮው መሳፍንታዊ አገዛዝ ነው አሁን ያለው--ሌላ ነገር የለውም፡፡ ልዩነታቸው የድሮዎች በበቅሎና ፈረስ ይጓዛሉ፤ የአሁኖቹ በመኪናና አውሮፕላነ፡፡ የድሮዎቹ ጋቢና ካባ ይለብሱ ነበር፤ የአሁኖቹ ሙሉ ልብስና ዘመናዊ ጫማ ያደርጋሉ፡፡ የድሮዎቹ በጋሻና ጦር እንዲሁም በቆመህ ጠብቀኝ ይዋጉ ነበር፡ የአሁኖቹ በታንክ፡ ጀትና ሞርታር ይዋጋሉ፡፡ በዚህም የቅርጽ እንጅ የይዘት ለውጥ የላቸውም እንላለን፡፡ በይዘት የትግራይ መሳፍንት ከሆኑ ዘንዳ የሚወርዱት በሰይፍ ብቻ ነው፡፡ በምርጫ የወረደ መሳፍንታዊ አገዛዝ ታይቶም ተሰምቶም አያውቅም፡፡ ስለዚህ የአማራ ልጅ ምርጫ በሚባል መመልመያ አጋፋሪ እየገባ ሰለባ መሆን የለበትም፡፡ የቻለ መዋጋት፡፡ ያልቻለ ዝም ብሎ በሰላም መኖር፡፡
ነጻ ጋዜጣ የሚባሉትም እንዲሁ ንቁ አማራ መመልመያ እና ወደ እርድ ማቅረቢያ ሆኑ እንጅ እስካሁን ምንም አልፈየዱም፡፡ ስለዚህ በማናቸውም ሜዲያ መጸፍ የለብንም፡፡ ፌስቡክ ላይ ራሱ በእውነተኛ አካውንታችሁ በግልጽ የምትጽፉ ልጆችም ራሳችሁን ለእርድ ምልመላ እያቀረባችሁ እንደሆነ እወቁ፡፡ ድፍረትና ግልጽነታችንን እንዋጋው ዘንድ ግድ ነው፡፡ አማራ ዋና ጠላቱ ድፍረቱ መሆኑነ ማወቅ ያሻል፡፡ ከእንግዲህ ደፍረን ፊት ለፊት መናገር ራሳችንን ለእርድ ከማቅረብ በቀር አንዳች ነገር እንደማይፈይድልን እንወቅ፡፡ ለእነሱ ራሳችንን አሳልፈን አንስጥ፡፡ መፍትሔውም እባብ መሆን ነው፡፡ ምንም ሳንናገር፡ በግልጽ ሳንጽፍ፤ እና ሰላማዊ ትግል ብለን ራሳችንን ሳናጋልጥ መኖር አለብን፡፡ የሚቃወም በስውር ይቃወም፡፡ እንደእባብ እየተጥመዘመዘ የልቡን ይስራ፡፡ ይህ ያቃተው ደግሞ ዝም ይበል፡፡ በንግግራችን እና በጽሁፋችን ግልጽነት የመጥፊያ መንገዳችንን አናፋጥን፡፡ ራሳችን ለእነሱ ሰለባ አናድርግ፡፡ ድፍረት ሞኝነት እንጅ ብልሀት አይደለም፡፡ ድፍረታችንን በብልሀት ካላገዝነው ምንም ፋይዳ የለውም፡፡ ዘዴው ዝም ብሎ ራስን ሳያሳውቁ በድብቅ ስራን መስራት ነው፡፡ ድፍረት ፊት ለፊት የሚገጥምህን ልትታገልበት ትችላለህ፡፡ አጥቂህ ወያኔ ግን የሰርዶ እባብ ነው፡፡ እንደእባብ ነው በተንኮል የሚነድፍ እንጅ እንደ ጀግና ፊት ለፊት የሚገጥም አይደለም፡፡ ድፍረትህ እየገነፈለ ቢያስችግርህም አምቀህ ያዘው፤ የሚያገለግልበት ጊዜ ሲመጣ ትጠቀምበታለህ፡፡
ድል ለአማራ
Melke Hara