Bete Amhara

Bete Amhara

Monday, June 15, 2015

የ15 አመት ህጻን እንዲህ ይቀኛል፡፡ እናንት መንዜ እናትና አባቶች አዲስ አበባ ውስጥ የወለዳችሁትን ብላቴና መንዜ አድርጋችሁ ስላሳደጋችሁልኝ አመሰግናለሁ፡፡
==============================================
ቀበቶ ፍታ
--------------
በሥልጣን ላይ ገብቶ:
ሥልጣን ከጭቁኖች መሐል ወጥቶ:
አፈር ቅሞ ያገኛትን የሹምነቱን ቀበቶ:
እንኳን ሊሰጥ ቀርቶ ፈቶ∷
ላጠለቃትም ሳስቶላት:
አስሬ ፈቶ ሲያጠብቃት∷
ያላዋቂ ሆነና…..
በክብር ያገኛትን ቀበቶ በጭሱ በላብ አጠባት፡
በርሀብ በንባ እየቀጣ ላይ ላዩን አሸበረቃት፡
ቴክኖሎጂውን አስፋፍቶ እህሉዋን ሰብሉዋን ነጠቃት፡፡
ግና ዛሬ ሕዝብ ነቃ፡
ሹመትህን መልስ አለ ቀበቶህን አውልቅ በቃ፡፡
በቃ የህዝብ ቁጣ ተነሳ፡
ውሃ የጠጣው ፈረሱ አሳተ ገሞራ አገሳ ።