Bete Amhara

Bete Amhara

Monday, June 15, 2015

አማራን በመንፈሳዊ እይታ ሳየው የእግዚአብሔር ህዝብ እንደሆነ ይሰማኛል
___________________________________________
ታሪኬን ዳሰስኩ፡፡ የንቡረ እድ ኤርምስን ንግግር ሰማሁ (ከመልከ ጼዴቅ ካህን እስከ አእዛን ያለው ቢላል ድረስ አማሮች ናቸው ይላሉ)፡፡ አማራን አሰብኩት፡፡ ከመንፈሳዊ ህይወቱ አንጻር ቃኘሁት፡፡ አማራ ጥንት ከኦሪት በፊት የታወቀው የግዮን ምድር ነዋሪ ነው፡፡ ግዮንም ገነትን የሚያጠጣው ወንዝ ነው፡፡ እና ቤተ አማራን አንዳች የቅድስና ነገር፤ ምስጢራዊ ነገር እንዳለው መረመርሁ፡፡ ብዙዎች ነገሮች እውነትም የአምላክ ህዝብ እንደሆነ እንዳምን አደረጉኝ፡፡
እኔ የማውቀው አማራ ባህርያትም የሚከተሉት ናቸው፡፡ ተመችቶትም ተቸግሮም ጸሎት፡ ጾምና ምጽዋት አይረሳም፡፡ ማታ ማታ ለልጆቹ ስለወዲያኛው አለም ከማስተማር አይቦዝንም፡፡ ወደ መለኮታዊ ቦታ ለመሄድም አይሰንፍም፡፡ ምድሪቷንም ገዳማትና የምናኔና ስውር ቤተ ጸሎት አድርጓታል፡፡ ራሱ ጨፈቃ ውስጥ እየኖረ የአምላኩን ቤት አስጊጦ ይሰራል፡፡ ልጆቹን እያስራበ እንኳ የእግዜር እንግዳ ብሎ ያስተናግዳል፡፡ ቤት ለእንግዳ ብሎ አልጋውን ለቆ መሬት ላይ ወይም በረንዳ ላይ ይተኛል፡፡ ሲጸልይ አገሩን አማን ቀየውን ሰላም አድርግልን፤ ወንዞችን እስከገደፋቸው ምላልን ይላል፡፡ የጽድቅን መንገድ አጥብቆ ይሻል፡፡ እየተበደለ እንኳ በቀልን ለአምላኩ ይተዋል፡፡ ይውጋህ ሲሉት ይማርህ ይላል፡፡ ሲረግሙት ይመርቃል፡፡ ልግስናን ለልጆቹ ያስተምራል፤ ራሱም ይኖረዋል፡፡
አቡነ ተክለ ኃይማኖት የተባሉ ቅዱስ ሰው አለው፡፡ በምድር ላይ የሚመለክ ኃይለ ሥላሴ የተባለ ሰው አለው፡፡ ከ150 አመታት በፊት የዛሬውን ሁኔታ በትንቢት ሳይዛነፍ ያስቀመጡት ሸህ ሁሴን ጅብሪል የተባሉ ሰው አለው፡፡ አንዳንድ በሽታዎችን ፈጽሞ የሚያድኑ ጥበባት አሉት፡፡ ብቻ አማራ ለአምላክ ቅርብ እንደሆነ የሚያሳዩ ብዙ ነገሮች አሉት፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ በአለም ላይ በከፊል እንኳ በማንም ቅኝ ገዥ ያልወደቀ ጥቁር ህዝብ ነው፡፡ ጥቁር ላይ አድሎ በሚደረግባቸው ቦታዎች ሁሉ አማራ ራሱንና ሌላውን ጥቁር ያስከብራል፡፡ ለምሳሌ የአሜሪካ ቤተ መንገስት ለመጀመሪያ ጊዜ የገባ ጥቁር መሪ አማራ ነው፡፡ ከድንቅ የአለም ሰዎች ንግግሮች የተመዘገበ የአማራ ነው፡፡ ክብሩን በሀይሉ ያስከበረ አማራ ነው፡፡
እና ይህ ህዝብ ፈተና ይበዛበታል፡፡ የአምላክ ህዝብ ደግሞ ፈተና ይበዛበታል፤ የሚፈታተነው ነገር አያሌ ነው፡፡ ለዛሬ መንፈሳዊ ጽሁፍ ጻፍኩ…ራሱ የአማራ መንፈስ በል በል አለኝ፡፡ እምነት የሌላችሁ ቤተ አማሮች እንዳትቀየሙኝ አስቀድሜ ይቅርታ እጠይቃችኋለሁ፡፡ይቅርታ፡፡ የራሴ ግላዊ አቋም ነው፤ የቤተ አማራ አይደለም፡፡
የትንታጎቹ አገር ወልቃይት ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ!
ድል ለቤተ አማራ
መለክ ሐራ ከቤተ አማራ