የወልቃይት ሳምንት
============
በመጀመሪያ እባብ ወንዝ ሞላበት፡፡ በዚያም ሰው ነበረ፡፡ ሰውም ወንዙን ይሻገር ነበር፡፡ እባብም ሰውን አለው “እባክህ አሻግረኝ”፡፡ ሰውም ልቡ ራራ፡፡ እባቡንመ ራሱ ላይ ጠምጥሞ አሻገረው፡፡ ወንዙን በተሻገሩ ጊዜ ግን እባብ ከሰው አልወርድም አለ፡፡ ሰውም አለው “ውረድ እንጅ፤ ውላችን እንድትወርድ አልነበረምን?” እባብም አለው “እኔ አልወርድም” ፡፡ እባቡም ወንዝ ያሻገረውን ባለውለታውን ሰው ነድፎ ገደለው፡፡

ይህ ብሂል በቀጥታ ቤተ አማራ ላይ የደረሰ ነው፡፡ በጎንደር ሰሜንና ሰሜን ምእራብ ወልቃይትጠገዴ የሚባል ዘመን መቆጠር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የቤተ አማራ እጣ ክፍል የሆነ ምድር አለ፡፡ ይህ ምድር ሀብታም፤ ባለጸጋና ለም ነው፡፡ ሰውም ደግና ጀግና ነው፡፡ የእምነትና የእውነት አገር ነው፡፡ ወደር የለሽ ጀግንነት የባህርይው የሆነ ህዝብም ይኖርበት ነበር፡፡ ይህም ወልቃይት ተርቦም ተጠምቶም አያውቅም፡፡ በድሮው ጊዜም የምርቱን ውፍረትና ጠንካራ አምራችነቱን ለማሳየት በጥይት ይመታ ነበር፡፡ የጥይት እርሳስ ምርቱን የበሳችበት ወልቃይት እንደሰነፍ ይቆጠራል፡፡ እርሳስ ግን ምርት ውስጥ ተወሽቃ በቀረች ጊዜ ወልቃይቴው አራሽ አንደፋራሽ ጀግና ይባላል፡፡ ወልቃይት ለእንግዳ አልጋውን ለቆ መሬት ላይ የሚተኛ ህዝብ ነው፡፡ ሲቆጣ አሞራን በጥይት ከሰማይ የሚያወርድ ነው፡፡ ወልቃይት ለእመብርሀን ዝክረኛ እንጀራ ቆርሶ አይሰጥም፡፡ ነውር ነው፡፡ ለዝክረኛ ሙሉ እንጀራ ይሰጣል እንጅ፡፡ ወልቃትም ለእንግዳ ያለው እምነት ለፈጣሪው ካለው እምነት ቢተካከል እንጅ አያንስም፡፡ ይህም ወልቃይት ከጥንት የታወቀ ጀግና፤ ምድሩም እስከ ኤርትራ ምድር የሚዘልቅ፤ በምእራብም ሱዳን ብቻ የሚያዋስነው ነበር፡፡
ከዘመናትም በአንዱ ወያኔ የሚባል ወንበዴ ከትግራይ ወገን ተነሳ፡፡ ይህም ወንበዴ ትግራይን ከደርግ አገዛዝ በጉልበት ነጥቆ ነጻ ካወጣ በኋላ መላዋን ኢትዮጵያ መውረር ፈለገ፡፡ ለወረራም መሰናዶውን ካጠናቀቀ በኋላ ወደ መሀል ኢትዮጵያ ለመዝለቅ በወልቃይት ማለፍ የግድ ሆነበት፡፡ የእባብ ጸባዩንም በመቀየር በመለሳለስ ከወልቃይት ልብ ውስጥ ገባ፡፡ ሰው አማኙም ወልቃይት ለዚህ እባብ እልፍኝና አዳራሹን ወለል አድርጎ ከፍቶ አስገባው፡፡ በእባቡም ምላስ የተንኮል ንግግር ተታለለ፡፡
ይህ ወያኔ ለአመታት ወልቃይት ውስጥ በቆየባቸው ጊዜያት ሁሉ ቅን መስሎ ኖረ እንጅ እውነተኛ ጸባዩን አልገለጠም ነበር፡፡ ወልቃይትም ለዚህ ወያኔ ወተት እያጠጣ አኖረው፡፡ ከአዝርእት ፍሬውም አልለየውም፡፡ የሰባውንም እያረደ ቀለበው፡፡ ሴት ልጆቹም ውሀ እንዲቀዱለትና ማገዶ እንዲለቅሙለት አደረገ፡፡ ቁስለኛውንም እቤቱ እያስታመመ ያድን ነበር፡፡ የሞተውንም ጉድጓድ ቆፍሮ አልቅሶ ይቀብር ነበር፡፡ ከማሳውም እሸት እየቀጠፈ እንካ ብካ ይለው ነበር፡፡ የከርሞ ሰው ይበልህ ብሎም ይባርከው ነበር፡፡ እነሆ ወልቃይት ካለው ነገር ሁሉ ሰስቶ አንዳችም ነገር አላስቀረበትም፡፡ ያለውን ሁሉ ሰጠው እንጅ፡፡ በክፉ ቀን መሸሸጊያ ሆነው፡፡ በዚህም ግብሩ ደርግ ለተባለው ገዥ ሰለባ ሆነ፡፡ እንደምንድር ነው ነገሩ ቢሉ ወንበዴ ትደብቃለህ፤መንገድ ትመራለህ፤ ስንቅም ትሰጣለህ እየተባለ፡፡ ይህ ወያኔ ግን በውጭ መልካም እየመሰለ በውስጥ ክፉ ነገር ያስብበት ነበር፡፡ ማታ ማታም ቢላ ይስልለት ነበር፡፡ ይህም ወያኔ ክፉውን ቀን ሁሉ በወልቃይት ጉያ ተሸሽጎ አሳለፈ፡፡ ጎለመሰም፡፡ መላዋን ኢትዮጵያንም ተቆጣጠረ፡፡ ነገር ግን ሳይውል ሳያድር ወልቃይትን ማረድ ጀመረ፡፡ ወንድ የሆኑትን ሁሉ ገደለ፡፡ ሴት ልጆችና ሚስቶችን ለራሱ አደረገ፡፡ ጫካ እንደሚመነጠር ሁሉ ይህ ወያኔም ወልቃይትን ሁሉ መነጠረ፡፡ ወልቃይትም ባጎረስኩ እጀን ተነከስኩ አለ፡፡ ነገሩ ሁሉ እጸድቅ ብየ ባዝላት ተንጠልጥላ ቀረች እንደተባለው ሆነ፡፡ ወልቃይትም ወርቅ ባበደርኩ ጠጠር፤ እህል ባበደርኩ አፈር ተመለሰልኝ አለ፡፡ ብዙውም የወልቃት ክፍል ፈጽሞ ጠፋ፡፡ በባእዳንም ተወረረ፡፡ የተረፈው ወልቃይትም ቁጥሩ እንደዋልያ ተመናምኖ ባልሞት ባይ ተጋዳይነት ውጭ ነብስ ግቢ ነብስ ሆኖ አለ፡፡ ወያኔም እለት እለት ይገድለዋል፤ በየለቱም ያስረዋል፤ በየለቱም ይሰድበዋል፤ በየለቱም ያሳድደዋል፡፡ በውኑ ወልቃይት እንደ ቃየን ተቅበዝባዥ ሆነ፡፡ መከራውም ማለቂያ አጣ፡፡ የሚረዳውም አልተገኘም፡፡ የለደረሰበትም በደል አልተሰማለትም፡፡ ዛሬ የዚህ ወገናችን በእሳት ላይ ተጥዶ እየተጠበሰ መሆን በእውኑ ለቤተ አማራ ትልቅ ሞት ነው፡፡
መላው ቤተ አማራም እንግዲህ ይህንን ሳምንት ወልቃይትን በማሰብ፤ ስለወልቃይት በመጻፍ፤ ፎቶ በመለጠፍ፤ አይዞሀ አይዞሽ በመባባል እንዲያሳልፈው ስንል ቤተ አማሮች ይህ እዲሆን በጎ ነው ብለናል፡፡
ከዚህም በታች አገራቸውን ተቀምተው በስደት አውስትራልያ በሚገኙበት እስራኤል በስደት ዘመኑ ሁሉ ያደርግ እንደነበረው ሁሉ ወልቃይትን እያሰቡ የሚያሳይ ዘፈን ነው፡፡ እነዚህ የምታዩአቸው ቤተ አማሮች አገር የላቸውም፡፡ ከሞት መንጋጋ ያመለጡ ናቸው፡፡ ይሀች የሚዘፍኑባት አዳራሽ ብቻ ናት አገራቸው፡፡ ያንን ብሩክና ማርና ወተት የሚፈስሰውን ምድራቸውን ግን ተቀምተዋል፡፡ እነርሱም ባተዋርና መጻተኛ ናቸው እንጅ አገር የላቸውም፡፡

ድል ለቤተ አማራ!
መለክ ሐራ ከቤተ አማራ
መለክ ሐራ ከቤተ አማራ