Bete Amhara

Bete Amhara

Monday, June 15, 2015

እውን አማራና ትግሬ ተዋግቶ ያውቃልን?
=========================
በማህበራዊ ሚዲያም፤ በመሸታ ቤትም፤ በመንግስት መዋቅርም፤ በግለሰቦችም ንግግር ሁልጊዜ የትግራይ ሰዎች ደጋግመው የሚናገሩት ነገር አለ፡፡ እርሱም አማራን በጦርነት ማሸነፋቸው፤ አማራ ጀግና እንዳልሆነ፤ አማራ ፈሪ እንደሆነ፤ ትግሬ ግን ጀግና እንደሆነ፤ አማራ ፉከራ ብቻ የሚዎድ እንጅ የእውነት ጀግና እንዳልሆነ፤ ትግሬ ግን በተግባር ጀግና የሆነ እና አሸናፊ ጦረኛ፤ እንዲሁም በታሪክ ሁልጊዜ አማራን ሲያሸነፍ እንደኖረ መለፈፍ ነው፡፡ ደርግን ማሸነፋቸውን ትግሬ አማራን እንዳሸነፈ አድርገው ነው የሚያወሩት፡፡ ግን ሁልጊዜ ሳስበው ግርም ይለኛል፡፡ የሚያስገርመኝ እስካሁን ሲናገሩ የሰማኋቸውና የማውቃቸው ትግሬዎች አንድ ላይ ተስማምተው የሚያምኑት እምነት መሆኑ ነው፡፡ መገረሜን እተውና ስለድንቁርናቸው ደግሞ በጣም አፍርላቸዋለሁ፡፡ እውነት እውነት እላችኋለሁ እኔ ስለነሱ ድንቁርና ሁልጊዜ ሽምቅቅ ብየ እንዳፈርኩ ነው፡፡
ድንቁርናቸው የሚጀምረው አማራና ትግሬ በታሪክ አንድም ጊዜ ነገድ ለይቶ ጦርነት ውስጥ አለመግባቱን አለማወቃቸው ነው፡፡ በመሳፍንት መካከል የነበረው የስልጣን ሽሚያ ፈጽሞ የነገድ ጦርነት አለመሆኑን ለማወቅ መማር ብቻ ሳይሆን ሰው መሆን ብቻውን በቂ ነው፡፡ ደርግን አሸነፍን ሲሉ ያው ወደሌላው ነገር ሳልገባ አሸንፍን የሚሉትን ብቻ ልውሰድላቸውና ደርግ አማራ አልነበረም፡፡ ደርግ እንዴውም አማራን በተለያዩ ምክንያቶች በጭካኔ ይጨፈጭፍ የነበረ፤ በአማራ በጣም የተጠላ ነበር፡፡ ለዚህም ደርግን ፊት ለፊት በመግጠምም ሆነ ውስጡን ቦርቡረው በመጣል የአማራ ልጆች ቀዳሚውን ሚና ይወስዳሉ፡፡ ወታደሩም ከሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ የተውጣጣ እንጅ አማራ ብቻ አልነበረም፡፡ እነ አጅሬ ግን ደርግን አማራ ነው አማራውን አሸነፍን ብለው ራሳቸውን ያታልላሉ፡፡ እውነቱ ግን አይደለም አማራ እንደአማራ ገጥሟቸው ይቅርና ጉናን እንኩዋ የጋይንት ሰው አላሳልፍ ብሉአቸው በሽማግሌና በተማጽኖ በደርግም ጅልነት ነው ያለፉት፡፡ 25 ጊዜ ማጥቃት አድርገው ከጉና ተራራ ለመውረድ ሞክረው አልቻሉም፡፡ አንድ ወረዳ የማይሞላ አማራን ማለፍ አልቻሉም ነበር፡፡
ሻዕብያ ሊውጣቸው በነበረ ጊዜ እንኳ አማራ ነው ሄዶ ተረባርቦ ያተራፈቸው፡፡ ዘመድ መስለውት፡፡ በኋላ ጀርባውን እንደሚወጉት ሳያውቅ፡፡ ባድመ፡ ጾረና፡ ዛላምበሳ ምናም ተብሎ የዘመቱት የሰፈሬ ልች እንኳ ስንቶቹ እንደቅጠል ረገፉበት፡፡ ሰፈራችን አንድ ሰሞን የለቅሶ ድንኳን ብቻ ሆኖ በሁሉም ቤት ሀዘን ነበር፡፡ ያንን አድርጎ፤ ህይወቱን ገብሮ እነሱን ያተረፈ ህዝብ ግን ዛሬ ፈሪ ሲባል መስማት ከህመም በላይ ነው፡፡ ይባስ ብሎ መሳለቂያ ሲሆን ማየት ይዘገንናል፡፡ ያኔ ትግራይ ውስጥ ውትድርና የሚሄድ ጠፍቶ አልፎ አልፎ በግዴታ ነበር እየታነቀ የሚወሰደው፡፡ አማሮች ግን አገር ተደፈረ ሲባሉ እውነት መስሏቸው የምዝገባ ጣብያውን ሁሉ አጨናንቀውት ነበር፡፡ በፈቃደንነት ሄደው ነበር እንደ ተርብ ያለቁት፡፡ ዛሬ ያ ሁሉ ተረስቶ የወያኔ ካድሬዎች ግፍንና ጡርን ተናግሮ በማያባራው አፋቸው ሲሰድቡት እና ሲገፉት ይውላሉ፡፡
በታሪክ ትግሬ አማራን አሸነፈ የሚሉት ተረትም ከመመጻደቅ እንደማያልፍ ብናውቅም በእነሱ ማፈራችን አልቀረም፡፡ እውነት ለመናገር ከአክሱም ውድቀት በኋላ ትግሬ የሀይል የበላይነት ወስዶ የመንግስትን ስልጣን መያዝ የቻለው እንኳ ሁለት ጊዜ ብቻ ነው፡፡ አጼ ዮሐንስ 4ኛ እና አሁን ወያኔ፡፡ ከአክሱም ውድቀት በፊት የነበረው መንግሰትም የትግሬ ስለመሆኑ መተማመኛ የለም፡፡ ዛሬ እዛ አካባቢ ላይ ትግሬ መኖሩ ጥንት ገዥ መደቡ ወይም ነገስታቱ ትግሬ ነበሩ ማለት ሊሆን አይችልም፡፡ ከአክሱም ውድቀት በፊት የነበረው መንግስት የትግሬ ነበር ብለን ብንወስድ እንኳ ከዛ በሁዋላ ባለው 1300 አመታት ገደማ ውስጥ ትግሬ የመንገስት ስልጣን ያያዘው እንደተጠቀሰው ሁለት ጊዜ ብቻ ነው፡፡ የአገውና የአማራን የግዛት ዘመን አንድ ላይ እንደምረዋለን፡፡ እርሱም የቤተ አማራ የስልጣን ዘመን ስለሆነ አንድ ላይ ነው የሚቆጠረው፡፡ ከዚህ 1300 የቤተ አማራ ዘመን ላይ 17 አመት የአጼ ዮሐንስ 4ኛ እና 23 አመት የወያኔን አመት ደምረን እንቀንሳለን፡፡ 1300-40 = 1260 አመት ልዩነት ያመጣል፡፡ ስለዚህ 40/1260 = 0.03 ንጽጽር ያመጣል፡፡ ይህ ቁጥር ከትልቁ 1260 አመት አንጻር ምንም ዋጋ የሌለው አቅራቢያ-ዜሮ ነው፡፡ ስለዚህ የወያኔ ካድሬዎች ኩራት ከንቱ ቅዠት ነው፡፡ የማይወዳደር ነገር ይዘው ነው የሚንጦለጠሉት፡፡ (ቁጥሩን ግን በገደምዳሜው ከ 7ኛው ክፍለ ዘመን ብየ ነው የወሰድኩት፡፡ ትክክለናውን አክሱም የወደቀችበትን ወርና አመት ምህረት የሚያወቅ ሊተባበረኝ ይችላል)፡፡
ምንም እንኳ አማራና ትግሬ በታሪኩ ተዋግቶ ባያውቅም አሁን ግን ሆነ ብለው እየቆሰቆሱት እንደሆነ እያስተዋልን ነው፡፡ ጥንቃቄ ቢያደርጉ ይበጃቸዋል፡፡ ይህንንም ንግግራችንን እንደ አጉል ፉከራ ነው የሚቆጥሩት፡፡ አማራ በማንም ላይ ፎክሮ አያውቅም፡፡ በአስተሳሰቡም ግለሰቦችን እንጅ የሚጣላው ቡድኖችን ተጣልቶ አያውቅም፡፡ የዳበረ ባህላዊ የፍትህ ስርአት የታደለ በመሆኑ በደል የፈጸሙበትን ነጥሎ ለፍርድ ያስቀምጣል እንጅ እንደሌላው ሁሉ ቡድናዊ ጠላት አለኝ ብሎ አስቦ አያውቅም፡፡ አሁንም የወያነ ካድሬዎች በጸባያባችን የሌለውን ቡድንን ጠላት ብሎ የማሰብ በሽታ እኛ ላይ ልትጭኑብን አትሞክሩ፡፡ እዛው ራሳችሁ ተሸክማችሁት ዙሩ፡፡ ሁሉን እንወዳለን፡፡ ይህ ግልጽ ነው፡፡ ለይተን የምንጠላው ቡድን የለም፡፡ ለይተን የምንጠላውና ለፍርድ የምናስቀምጠው ግለሰብ ግን ይኖራል፡፡ ይህም ግልጽ ነው፡፡
መለክ ሐራ ከቤተ አማራ