Bete Amhara

Bete Amhara

Monday, June 15, 2015

በጌ ምድርማ አማራነት ብቻ ሳይሆን እስራኤልነትም አለበት!
===========================================
አንድ ወለፈንዲ ወያኔ ከነ ጭፍሮቹ ሰሞኑን በጌምድር አማራ አይደለም፤ አንድ አረማዊ የወንድ ብልት አምላኪ የአክሱም ንጉስ ከሜርዌና ኑብያ ማርኮ አምጥቶ ያሰፈራቸው ሱዳኖች ናቸው ብሎ ለያዥ ለገናዥ አስቸግሮ ሰንብቷል፡፡ ደጋግመን እንዳልነው ወያኔ ጎንደርን ከከጀላት ከራርሟል፡፡ አማራን አዳክሞ፤ ከፋፍሎ እና ገድሎ ማጥፋት በሚለው ዋናው አጀንዳቸው ስር የሚገኘው ያልተጻፈው እቅድ አንድ ጎንደርን ትግራይ ማድረግ ነው፡፡ ጎንደርን ትግራይ የሚያደርጓትም ህዝቡን ዘሩን በማጥፋት አንዱ መንገድ ነው፡፡ በወልቃይትና ጠገዴ እንዳደረጉት እና እያደረጉት እንዳለው፡፡ ሁለተኛው ጎንደርን አማራነቱን መግፈፍ ነው፡፡ ይሄው ከሰሞኑ ቅማንትን ከሰሞኑ እንደግራምጣ ሰንጥቀው በማውጣት እንዳሳዩት ማለት ነው፡፡ ከዚህም የተረፈውን አማራ አይደለም ገሌ መሌ በማለት ማንነቱን ማጥፋትና ብሎም በተለያዩ ስውር ደባዎች አመናምኖ መጨረስ ነው፡፡
የዚህም እርምጃ መጨረሻው ላይ የደረሱ የመስላሉ፡፡ ጎንደርን ለመዋጥ ከመቸውም በከፋ ሁኔታ መንጋጋቸውን እያፋጩ ናቸው፡፡ ቤተ አማራም ቀድሞ መንቃቱ የጥርስ ግጭት ፍጭታቸውን አቅሉን የሳተና የተወነጋገረ አድርጎታል፡፡ ሲሻቸው ጎንደርና ትግሬ አንድ ነው ይላሉ፡፡ የዚህ ንግግግ አላማ ግልጽ ነው፡፡ ጎንደርን ከሌላው ቤተ አማራ ነጥሎ ለማጥቃት እንዲመቻቸው ነው፡፡ በል ሲላቸው ወልቃይት የሚባል ልዩ ህዝብ እንዳለ ያስመስሉና ዘሩን ማጥፋታቸውን ቤተ አማራ አይመለከተውም አይነት ወሬ ያናፍሳሉ፡፡ ቁጣቸው ሲገነፍልም ሱዳን፤ ምርኮኛ ምናን ይላሉ፡፡ ሲከፋም እኛ ሴማዊ ነን ደማችን ንጹህ ነው፡፡ በጌምድርም ሆነ መላው ቤተ አማራ ንጹህ ደም የሌለው ኩሽ ነው ይላሉ፡፡ ግን ከነዚህ ጋር እስካሁን የኖርነውን ዘመን ሳስበው በጣም ያበሽቀኛል፡፡ አብረን መኖር ከማይገባን ህዝብ ጋር ነው በስህተት የኖርነው፡፡ በጣም ያሳዝናል ነገሩ፡፡ እነሱ እንግዲህ ከነሱ ውጭ ላለው ህዝብ ያላቸው አመለካከት እንዲህ ነው፡፡ ለዛም ነው ልንግባባ ያልቻልነው፡፡ ለዚህም ነው ሲያርዱን እና ሲገድሉን ምንም የማይሰማቸው፤ ለዚህም ነው ሰው እንደገደሉ የማይሰማቸው፡፡ ከሀሳባቸው እንደተረዳነው እነርሱ ሰው ሳይሆን እየገደሉ ያሉት ኩሽ የሆነና ንጹህ ደም የሌለው ፍጥረት ነው፡፡
የነሱ የደም ጥራት የቤተ አማራ መሳቂያ መሳለቂያ ከመሆን የዘለለ ትርጉም እንደሌለው አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን አካፋን አካፋ ካላሉት የውርቅ ማንኪያ ነኝ ይላል በሚለው ብሂል መሰረት በልካቸውና በወርዳቸው ልክ መልስ ልሰጣቸው ወድጃለሁ፡፡ ከእንግዲህ ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ፤ አገር እንዳይበተን ምናምን እየተባለ ዝም ስንል የኖርንበት ዘመን አልፏል፡፡ ኢትዮጵያ የአማራ ሸክላ ናት፡፡ ስለሸክላችን ከምንሞት ሸክላችንን እኛው እንቦጭ አድርገን ሰብረናት ራሳችንን ብናተርፍ ይሻላል፡፡ አማራ የራሱን ሸክላ ቢሰራም ቢሰብርም መብት እንዳለውም ይወቁ፡፡ በራሳችን ሸክላ ባለቤቶቹም አድራጊ ፈጣሪዎቹም እኛው ነን፡፡ እኛም ከእንግዲህ ልባችን እውነቱን እያወቀው ለአገር አንድነት ሲባል ሆድ ይፍጀው ብለን የያዝነውን ሁሉ አውጥተን ማፍረጥና ማንነታችንን ማሳየት አለብን፡፡ ከእንግዲህ እነሱ አንድ እርምጃ ሲራመዱ እኛ አስር እርምጃ እንራመዳለን፡፡ በጥፊ የመታንን በጎመድ እናዳሻለን፡፡ ማንነታችንን ሊክድ ለተነሳ የራሱን ማንነት እንዲክድ ወይም እንዲጠላው አድርገን እናፈርሰዋለን፡፡ ምክንያቱም ቤተ አማራ ልወርውር ካለ ሁሉም የሚወረወሩ እውነቶች አሉትና፡፡ በውሸት የተካበን ስድባችንን በእውነት ጠጠር ብቻ እናፈርሰዋለን፡፡
እናም በጌምድር እነሱ እንደሚጠቅሱት የአንድ ወለፈንዴ ፈረንጅ ጽሁፍ አለመሆኑን አበክሬ ነግሪያቸዋለሁ፡፡ የሰው ሀሳብ ፈጽሞ የማይገባቸው ፍጥረቶች ቢሆኑም ቅሉ፡፡ የሰጣኋቸው መልስም በጌ ምድር በትንሹ የሚታወቁ ሶስት መላምቶች ይሰነዘሩበታል፡፡ በጌ ምድር ማለትም የበግ አርቢ አገር ማለት የሚለው አንዱ ነው፡፡ ይህንንም ነባራዊ ሁኔታውን በማየት ሊያስኬድ የሚችል እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ አብዛኛው የቤተ አማራ ክፍል ደጋና ወይና ደጋማ ለበግ እርባታ ምቹ የሆነ ነው፡፡ ምንጃር የጤፍ አገር እንደምንለው ቤተ አማራ የበግ አገር የሚል አንድምታ ይሰጣል፡፡ ሁለተኛው መላምት አንድ ንጉስ (ስሙን ዘንግቸዋለሁ) አፈረ ዋናት (የዛሬው ባህርዳር እስከ ፎገራ መለስ ጎንደርና ስሜንን ያጠቃለለ) ዋና ከተማ ላይ ከተሞ ነበር፡፡ ከዛ በፊት ባደረገው ጦርነት ማሸነፉን ለማስታወስ በጄ ምድር (ምድር በእጀ ሆነች) ማለቱ ተዘግቧል፡፡ (ለዚህ ምንጭ ቤተ እስራኤል በኢትዮጵያ የምትል ትንሽ መጽሀፍ እንዳነበብኩ አስታውሳለሁ)፡፡ እናም በዚህ መላምት በጌ ምድር ማለት ምድር በእጀ የሚል ንጉሳዊ ቃል ነው፡፡ ሶስተኛው ቤጃ የሚባል ህዝብ ይኖርበት ስለነበር ከዚሁ ህዝብ ስም የመነጨ ስያሜ ነው የሚለው ነው፡፡ በተለይ ይህ ሶስተኛው መላ ምት አያስኬድም፡፡ ምክነያቱም መቸና ከየት እስከየት ለሚሉት ጥያቄዎች ምንም አይነት መልስ የሌለው በመሆኑ፡፡
ወለፈንዴ ወያኔዎች ያመጡት የዚህ የሶስተኛው መላምት ተያያዥነት ያለው አራተኛ መላምት ደግሞ ጎንደር ወይም የድሮው በጌ ምድር አንድ የአክሱም ንጉስ ከሱዳን ሜርዌና ኑብያ ማርኮ ያመጣቸው 12 ሰውች ነበሩ መጀመሪያ የሰፈሩት የሚል ነው፡፡ ይህ እውነት ቢሆን በጣም ደስ የሚል እድል ነው በእውነቱ፡፡ ምክንያቱም ሜርዌና ኑብያ በጣም ስልጡን ህዝቦች ነበሩና፡፡ ዘላን የሆነው ቅድመ ክርስትና የአክሰም ንጉስ እንዳጠፋቸው ይታወቃል፡፡ ይህም የዚህን የወያኔዎችን አካባቢ ህዝብ ከጥንት ጀምሮ የኖረ ጸረ ስልጣኔ ባህርይ የሚያሳይ ነው፡፡ ከዛ አካባቢ የሚመነጩ ኤሊቶች ሁልጊዜም የኢትዮጵያን ስልጣኔ አውዳሚነታቸው ከዛ የሚመነጭ በሽታ ይመስላል፡፡ ለምሳሌ በጎንደር መንግስትን ጥለው እንዴት አገር መምራት እንዳለባቸው ምንም እውቀቱ ስላልነበራቸው ዘመነ መሳፍንትን ማምጣታቸው፤ በአጼ ቴዎድሮስ የተጀመረውን የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ አብዮት የውጭ ጠላት መርተው በማምጣት ማጨናገፋቸው፤ በጠብ መንጃና መጋረጃ በመታለል ለውጭ ጠላት በር እየከፈቱ በየዘመኑ ማስገባታቸው፤ አሁን አለም የት በደረሰበት ጊዜ ኢትዮጵያን ከእንስሳ በሚያንስ ለሰው ልጅ ስልጣኔ ፍጹም ስድብ የሆነ ስርአት ውስጥ መክተታቸው እና ሌሎቹም ጸረ ስልጣኔ ባህልና ባህርያቸውን ያሳያል፡፡ በጠቅላላው የጎሳዊ ስሜት በስልጣኔ ኋላ መቅረትን የሚያመለክት ነው፡፡ ዛሬም ስልጡን ከሆነው ምክንያታዊ የሰው ልጅ ባህርይ ይልቅ ለስሜታዊ ህላዌ በማድላታቸው የዚህ ያለመስልጠን ባህርይ ሰለባዎች እንደሆኑ ማረጋገጫ ነው፡፡ እናም ይህ የምርኮኛ ቲዎሪያቸው ትክክል ከሆነ ቀድሞም ስልጣኔያችንን ያጠፉት እነሱ መሆናቸውን ያረጋግጣልናል፡፡ እጅግ ስልጡን ከሆኑት ዘሮች መምጣታችንም ያኮራናል፡፡ አልገባቸውም እንጅ እነዛ ቤተ አማራን ለመስደብ የጠሯቸው የዛሬዎቹ ሱዳኖች የግብጽ ስልጣኔ ባለቤቶች ናቸው፡፡
ስለነሱ ረብ የለሽ መላምት ይሁንን ካልኩ ዘንዳ አንድ የሚጎረብጣቸውን እውነት ልሰንግላቸው፡፡ መቸም ቤተ አማራ የአይሁድ ደም አለብን ብንል በትህትና የምንናገረው እንጅ የምንመካበት አይደለም፡፡ ተመክተንበትም አናውቅም፡፡ ለክርስትናችን ስንል ደብቀን ያስቀመጥነው ነገር ግን በጣም እውነት የሆነው ነገር በደማችን ውስጥ የእስራኤላዊያ ደም መኖሩን ነው፡፡ ቤተ አማራ ከጥንት ጀምሮ ከእስራኤላዊያን ጋር ጥብቅ ግንኙነት ነበረው፡፡ በተለያዩ መዛግብት እንደሚገለጸው እስራኤላዊያን በቤተ አማራ ምድር ሁሉ በስፋት ነበሩ፡፡ በኋላ ሀይማኖታቸውን ወደክርስትና እስከቀየሩበት ጊዜ ድረስ፡፡ ይልማ ደሬሳ በጻፈው የኢትዮጵያ ታሪክ በ16ኛው ክፍለ ዘመን ከሚለው መጽሀፍ ውስጥ በጌምድር ላይ በተለይም ስሜን ላይ ቤተ እስራኤላዊያን መንግስት መስርተው እንደነበር ይገልጻል፡፡ ያም መንግስታቸው በአጼ አምደ ጽዮን ተደመሰሰባቸው፤ እነርሱም ወደክርስትና እምነት እንዲቀየሩ ሆነ፡፡ ከታች ከጠቀስኩት መጽሀፍ ደግሞ ቀድሞ በ6ኘው ክፍለዘመን በዚሁ አካባቢ መንግስት መስርተው እንደነበር ይተርካል፡፡ የዮዲትንም ሁኔታ ማወቅ ያሻል፡፡ አይሁዳዊት ነው ትክክለኛ ስሟ፡፡ እርሷም የቤተ እስራኤሎች ንግስት ነበረች፡፡ ይህ በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነው፡፡ እና ቤተ አማራ አብዛኛው በሀይልም በውድም ወደክርስቲያን የተቀየረ ህዝብ ነው፡፡ በደሙም ውስጥ የእስራኤላዊያ ደም አለበት፡፡ ይህንን የምለው እውነትን ስለመናገር እና ወለፈንዴዎችን ስለማሳፈር እንጅ በእውነት አማራነታችንን ለማረጋገጥ ማዶ መሻገር አስፈላጊ ሆኖ አይደለም፡፡ አማራነታችን ከበቂም በላይ እንደሆነ ሁላችንም እናውቀዋለን፡፡ የሩቅም የቅርብም ጎሮሮውን ይተናነቀው እንጅ ሀቋን ያውቃታል፡፡ መጀመሪያ እንደጠቀስኳት መጽሀፍ ቤተ እስራኤሎች ነበሩበት የተባሉት ቦታዎች ሁሉም (ከሽሬ በቀር) ቤተ አማራ ውስጥ ናቸው፡፡ እንዴውም ያንን ያየ ቤተ አማራ በሙሉ ለማለት በሚያስችል ሁኔታ እስራኤላዊያን ሰፍረውበት እንደሆነ ይረዳል፡፡ ይህም የቤተ አማራን እና የእስራኤላዊያንን መቀላቀል የሚያስረዳ ነው፡፡
ከዚህም በመነሳት ይመስላል የሀይማኖት አባቶች እኛ እስራኤል ዘነፍስ ነን፤ እነዛኞቹ እስራኤላዊያን እስራኤል ዘስጋ ናቸው የሚሉት፡፡ ይህንም ሲሉ እኛ ክርስትያን ሆነናል፡፡ ስለዚህ በነፍስ እስራኤል ነን፡፡ ይላሉ፡፡ የነብዩን ኤርምያስን “እናንተስ እስራኤላዊያ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያዊያን አይደላችሁምን” የሚለውንም ከዚህ ጋር ማያያዝ ይቻላል፡፡ ኢትዮጵያ ሲል በአመዛኙ ቤተ አማራ ማለቱ እንደሆነም ይታወቃል፡፡ ለዚህም አእምሮ ንጉሴ የተባሉ ሰው ቅራት በተባለው መጽሀፋቸው ወሎ ገዳማት ውስጥ የሚገኙ የብራና መጽሀፍትን በመጥቀስ ሙሴ ወሎ ውስጥ አሁንም መደጊም ተብላ የምትታወቅ ቦታ እንደኖረ፤ ካህኑ ራጉኤል (ዮቶርም) የዛ አካባቢ ሰው እንደሆነ ይጠቁማል፡፡ ይህችም መደጊም የምትባል ቦታ የነገደ ምድያም መታሰቢያ ናት፤ ምድያም የሚለው ስምና መኖሪያ ከዚሁ ጋር ትይይዝ አለው ብለዋል፡፡ ይህና መሰል ምንጮች ቤተ አማራ ቀድሞውንም ከእስራኤላዊያን ጋር (ከነሱ በፊትም ሊሆን ይችላል፡፡ ጠለቅ ያለ ነገር አለው እዚህ ላይ ሌላ ጊዜ ልናገረው የምችለው) ግንኙነት እንዳለው ነው፡፡
እናም ምንም ቢሆን አንኮራበትም፤ አማራ ታይታ አይወድም፤ በልቡ ትሁት ነው እንጅ፤ እንናገር ካልን ሌላም ብዙ አለ፡፡ በጌምድር ወይም መላው ቤተ አማራ የአማራ ብቻ ደም ሳይሀን የእስራኤልም ደም በውስጡ አለበት፡፡ አማራ ሲደመር እስራኤል ማለት ነው፡፡ የዚህ ሀሳብ መነሳትም ፋይዳው የቤተ አማራን የኩሽና ሴማዊ ድብልቅነት ለማስረዳት ነው፡፡ ባለፈው ይህ ህዝብ መለኮታዊ ቀረቤታ አለው ስልም ይህንን ሁሉ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ነው፡፡ የአምላክ ህዝብ ነው ብየ መጻፌም በዚህ እና ለወደፊት በምናገረው ምክንያት ነው፡፡ የወለፈንዴዎቹ ምድር ግን እስራኤላዊያ እንዳልነበሩብ፤ ይልቅም ንጉሱ ካሌብ በቤተ አማራ ላይ እንዲሰፍሩ እንዳደረጋቸው ከታች ያለው የእንግሊዝኛ ጽሁፍ ይጠቅሳል፡፡ በእርግጥ የአክሱም ነገስታት ራሳቸው አማሮች ነበሩ፡፡ ከዛም ቀደም ብሎ ከእስራኤላዊያን ጋር ግንኙነት ነበራቸው፡፡ ይህ ክፍል የአሁኑ ትግሬ ከአክሱም ስልጣኔ ጋር ግንኙነት ሊኖረው እንደማይችል በሌላ ጽሁፍ ስመለስ የምዳስሰው ይሆናል፡፡
ለናሙና ያህል አንድ ወለፈንዴዎች የሚያምኑትን የፈረንጅ አፍ ማስረጃ አስቀመጫለሁ፡፡ ከላይ ያልኩትን የሚያጠናክር ሀሳብ ነው የያዘው መጽሀፉ፡፡ ሌላም ብዙ ማስረጃ እንጠቅሳለን-እንዳስፈላጊነቱ፡፡ ለዛሬው ከ (Ben-Rafael and Yochanan (2005), “Is Israel One? Religion, Nationalism, and Multiculturalism Confounded.” Vol. 5. BRILL: Leiden.) መጽሀፍ የሚከተለውን አንቀጽ ጀባ ብለናል፡፡
These authors document that: “Latter, Jews who retreated from the coastal areas of Ethiopia established an independent state in the Lake Tana region. In the sixth century, Jews also settled in the Semyen region by order of King Kaleb. In the thirteenth and fourteenth centuries, Beta Israel lost its independence and many Jews were forced to convert Christianity” (p.150). They also mapped the location of the Bet Israel: “Most of Beta Israel lived in the north of Ethiopia, between the Takkaze River to the north, Lake Tana to the east, the Blue Nile to the south, and the border of Sudan to the west. They inhabited villages of their own, the most important and best known of which were near the town of Gondar” (p.152).
ማሳሰቢያ ለሙስሊም ቤተአማራ፡- ይህ ጽሁፍ ሀይማኖታዊ ይዘት የለውም፡፡ ለመልስ ብቻ የተዘጋጀ ነው፡፡ ከአሁኑ የቤተ አማራ አጀንዳ ጋር አንዳች ግንኙነት የለውም፡፡ ለወለፈንዴዎች ስንመልስ እንዲህ አይነተ ነገር ውስጥ ስንገባ ቅር አንዳትሰኙብን በቤተ አማራ ስም ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ ይቅርታ፡፡
መለክ ሐራ ከቤተ አማራ