የቤተ-አማራን የኢኮኖሚ ምሰሶዎች ከአሁኑ እናስባቸው (ራስ የማነ ከቤተ-አማራ)
ቤተ አማራ - የአማራን ሕዝብ ከጭቆና አስተዳደር ማላቀቅ ብቻ ሳይሆን ከዚያም በሁዋላ ሕዝቡን በተለይ በኢኮኖሚው ዘርፍ ተጠቃሚ ማድረግ ዋና አላማው ነው። ስለዚህ በኢኮኖሚ የበለፀገ ሕብረተሰብ መፍጠር ዋና አላማችን ነው። በኢኮኖሚ የበለፀገ ሕብረተሰብ ለአምባገነኖች ለመገዛት ፍቃደኝነት በፍፁም አይኖረውም የሚል ጠንካራ እምነት አለን። በአለም ዙሪያ ያሉ ያደጉ አገሮች በሙሉ ዲሞክራቲክ መሆናቸውን ስናይ ይህ በአጋጣሚ የሆነ ነገር እንዳልሆነ አንገነዘባለን። እነዚህን አገሮች ጉልበተኛ መጥቶ ልግዛችሁ ቢላቸው እንደማይገዙ ማስተዋልም አያዳግተንም። አይ እነሱ አገሮች እኮ ዲሞክራሲ ከሆኑ በኋላ ነው ያደጉት የሚል ሰው ካለ - እውነት ነው ዲሞክራሲ እድገት ያመጣል - ሐሳቡን በነፃነት ወደ ተግባር መለወጥ የሚችል ሕዝብ መበልፀጉ ጥርጥር የለውም። እንደገናም ደግሞ የበለፀገ ሕዝብ ከዲሞክራሲ በቀር የሚመጥነው አስተዳደር እንደሌለም የታወቀ ነው።
እኛ ስለሚኖረን ኢኮኖሚ ስናስብ አሁን ካሉን ነገሮች ጀምረን በሂደት የሌሉንን ነገሮች ወደ መኖር እየቀየርናቸው እንሄዳለን። አልተጠቀምናቸውም እንጅ በጣም ብዙ ነገሮች አሉን። ችግሩ በዛሬው የፖለቲካ አሰላለፍ አማራን የሚጠቅም ነገር ከማሰብ በላይ ትልቅ ወንጀል የለም። ስለዚም መጠቀምም አንችልም።
እኛ ስለሚኖረን ኢኮኖሚ ስናስብ አሁን ካሉን ነገሮች ጀምረን በሂደት የሌሉንን ነገሮች ወደ መኖር እየቀየርናቸው እንሄዳለን። አልተጠቀምናቸውም እንጅ በጣም ብዙ ነገሮች አሉን። ችግሩ በዛሬው የፖለቲካ አሰላለፍ አማራን የሚጠቅም ነገር ከማሰብ በላይ ትልቅ ወንጀል የለም። ስለዚም መጠቀምም አንችልም።
ታዲያ ያሉንን ነገሮች በመዘርዘር እንጀምራ?
እስኪ ካደጋችሁበት አካባቢ አልተጠቀምንበትም እንጂ ይሄን እኮ እንዲህ ብንሰራበት ኖሮ ስንቱን ሰው ይመግብ ነበር የምትሉትን አስቡት። በcomment section ላይ በአንድ አንቀጽ ይጻፉት - የት አንደሚገኝ - ምን ሊሰራበት እንደሚችል ይንገሩን። ካሁኑ እቅድ ውስጥ ይገባል። አስቀድሞ የታቀደ ደግሞ አፈፃፀሙ የድርስ ድርስ ስለማይሆን ፍፃሜው ያምራል። ጠቀሜታውም ከፍ ያለ ይሆናል።
የሚከተሉትን የኢኮኖሚ ምሰሶዎች በሚቀጥሉት ተከታታይ ጽሁፎች ይዘን እንመጣለን።

1. ከምንም በላይ ዋናው ምሰሶአችን ሕዝባችን ነው። ትልቅ ደረጃ የደረሱ የተማሩ የተመራመሩ ሰዎች ቢኖሩንም አብዛኛው ሕዝባችን የገጠር ነዋሪ ነው። ሕዝቡ ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚሆኑ መሰረታዊ ትምህርቶችንና ስልጠናዎችን እየወሰደ በከፍተኛ ፍጥነትና ሁኔታ ይከትማል (ወደ ከተማ ይገባል)። ከ70 - 80% በላይ የገጠር ሕዝብ ይዘን ማደግ የቀን ቅዠት ነው። ትንታኔውን በቅርብ ቀን።
2. ምስራቅ አፍሪካን መመገብ የሚችሉ ለም መሬቶቻችን። ከላይ በቁጥር አንድ እንደጠቀስነው ሕዝቡን እያስተማሩ ወደ ከተማ በማስገባት የእርሻ መሬቶቻችን አሁን ካሉን በላይ እንዲሰፉ ማድረግና የመጨረሻውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ምርታችንን በብዙ እጥፍ ማሳደግ። ትንታኔውን በቅርብ ቀን።
3. ጣና እና ሌሎች ሐይቆቻችን። ከእኛ ተርፎ የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኝ የዓሳ ምርት። እንዴት? ትንታኔውን በቅርብ ቀን።
4. ተራሮቻችንና ለእርሻ የማይሆኑ መሬቶቻችን በደን ሙሉ በሙሉ ይሸፈናሉ። በአውሮፓ ሰማይ ላይ ሲበር በደኖች የቀና ቤተ-አማራ ካለ በእኛ ይደሰታል። ምን አይነት የዛፍ አይነቶችና መሬትን ከመሸፈን በተጨማሪ ምን አይነት ጥቅም ሊኖራቸው ይችላል? ትንታኔውን በቅርብ ቀን።
5. የቱሪስት መስህቦቻችን። የበለጠ እንዲታወቁና እንዲጎበኙ ምን ማድረግ አለብን? ትንታኔውን በቅርብ ቀን።
6. የኢንዱስትሪ መንደር ምስረታዎች ይጧጧፋሉ። በተለይም ለእርሻ የማይሆኑና የከርሰ ምድር ውሃ የሌላቸው አካባቢዎች ወደ ኢንዱስትሪነት ይቀየራሉ። ከገጠር ወደ ከተማ የሚገባው ሕዝብ ተጨማሪ የስራ እድሎች በኢንዱስትሪው ምክኒያት ይፈጠሩለታል። የግል ክፍሉ በሰፊው እንዲሳተፍ አስፈላጊው ማበረታቻ ይደረጋል። የቤተ-አማራ መንግስትም በተመረጡና አስፈላጊ በሆኑ ዘርፎች ኢንዱስትሪውን ያስፋፋል። ትንታኔውን በቅርብ ቀን።
7. የአገልግሎት ክፍሉ በአይነቱና በጥራቱ ይስፋፋል። የግል ክፍሉ በሰፊው እንዲሳተፍ አስፈላጊው ማበረታቻ ይደረጋል። ጉቦና የተንዛዛ አሰራር በውድ ቤተ-አማራዎት የባለቤትነት ስሜትና በመንግስታችን ጥረት ይወገዳል። የገዛ ቤቱን ቆሞ የሚያዘርፍ ሰው የለም። ቤተ-አማራም ቤቱን ከኢኮኖሚ ጠላቶች እዲጠብቅ የባለቤትነት መብትና ቁልፉን በእጁ ይረከባል።
ይህ ውድ የቤተ-አማራ ሕዝብን ወደ ትልቅ ኢኮኖሚ ኃይልነት ለመቀየር ለሚደረገው ያልተቆጠበ ጥረት እቅድ መያዣ ነው። ሃሳብ ይመነጫል። እቅድ ይወጣለትና ገና ሳይሰራ ፍፃሜው ይታያል። በእቅዱና በንድፈ-ሃሳቡ መሰረት ወደ አካልነት ይቀየራል። ቤተ አማራ እንዲዚህ ነው የሚሰራው። የረጅም ርቀት ጉዞ በአንድ እርምጃ ይጀምራል። ወደ ነፃነትና ወደ ብልፅግና ጉዞ እንኳን ደህና መጣችሁ።