Bete Amhara

Bete Amhara

Friday, June 26, 2015

ስለ ባህር ዳር ቴክስታይል ሰራተኞች እና ልጆች መበተን እና በአዲስ ወራሪ መያዝ

ስለ ባህር ዳር ቴክስታይል ሰራተኞች እና ልጆች መበተን እና በአዲስ ወራሪ መያዝ
_________________________________________________
መለክ እንደምን አለህ? ይህ ሳምንት አማሮች ምን ያህል ከኢኮኖሚ ውጭ እንደሆንን የምናይበት ሳምንት እንደሆነ ገልፀሃል፡፡ እኔም የማውቀውን በደል ልንገርህ፡፡ ያው መለክየ እኔ እያወራሁህ ያለሁት እስካሁንም ብቸኛ ስለሆነውና በ1953ዓ.ም ጣሊያኖች ለአያቶቻችን የደም ካሳ ይሆን ዘንድ በስጦታ ስለተከፈተው የባህር ዳር ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ የተመለከተ ነው፡፡ መለክ አብዛኛው የባህር ዳር ልጆች ወይ የቴክስታይል ያልያም የመምህር ልጆች ነን፡፡ አሁን እንዲህ ከመቀያየጣችን በፊት 75 ፐርሰንቱ የባህር ዳር ነዋሪ ወይ ቴክስታይል ይሰራል ወይ ቴክስታይል የሚሰራ ቤተሰብ አባል ነው፡፡ እኔም አንዱ ነኝ፡፡ እናልህ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ቴክስታይል ማለት የባህር ዳር ነዋሪ አዋጥቶ የገነባው የሁላችንም የግል ሃብት ይመስለኝ ነበር፡፡ ለምን መሰለኝ፡- አዎ ድሮ እኛ ሰራተኞች ልጆች የፋብሪካው ጊቢ በኛ ቁጥጥር ስር ነበር:: ከፈለግን ኳስ በፊርማ አውጥተን ከጧት እስከ ማታ የዛሬን አያድርገውና በሚያምረው የግቢው ሜዳ ላይ ያለከልካይ እንጫወት ነበር(አሁን የአሕያ ጋጣ መስሏል ምናለብት በስርዓት እንኳን ቢይዙት)፡፡ የመዋኛ ገንዳው ላይ አንዴ ቢራቢሮ ፣ አንዴ ቀዘፋ አንዴ ፣ ለንግላል (በጀርባ)፣ አንዴ … በነፃ አስፈቅደን እንዋኝበት ነበር፡፡ እናቶቻችን በሰጡን ኩፖን መዝናኛ ክበቡ ገብተን ሻይ በዳቦችንን እንቆርጥበት ነበር… በቃ ምን ልበልህ ቴክስታይል ማለት የኔ ነበር፡፡ በወቅቱ የሚገርመኝ ነገር ቢኖር ድርጅቱ ያን ያህል ሃብታም እያለ ለቤተሰቦቻችን የሚከፍለው ክፍያ ግን ድሮም ዝቅተኛ መሆኑ ነበር ፡፡ ለዛ ነው ስንቱ አዲስ ሰፈር የተሻለ የመኖርያ ሰፈር ሲሆን የኛ ነባር ቀበሌዎች በዋናነት ቀበሌ 7፣8፣9 እና 10 የደንገል ቤት ቅርስ አስመዝጋቢ ሆነን የቀረነው፡፡ የኛ ቤተሰቦች ላባቸውን ጠብ አድርገው ሰርተው በየ2 ሣምንቱ 128.00 ብር ብቻ ነብር የሚከፈላቸው፤ ያንም በደጉ ዘመን፡፡
አሁን ፋብሪካው ምን ሆነ? ከባህር ዳር ብሎም ከአማራ ህዝብ ሃብትነት ወጥቶ ለቻይና ተሸጠ ተባለ ፡፡ እውነቱ እነ ሃብቶም ፣ ጎይቶም ገቡበት፤ እስካሁን በርቀትም ቢሆን አንድ ቻይና አላየንም፡፡ ከ5000 ሰራተኛ እነሱን ጨምሮ ወደ 1300 ሰራተኛ ወረደ፤ 3700 በላይ ሰራተኞች ተባረሩ፡፡ የከተማዋ ግማሽ ህዝቦች አብረን ከህይወት መስመር ተባረርን፡፡ ሰራተኛው የት ደረሰ? ከልጂነቱ ጀምሮ ያባዘተውን ጥጥ ፀጉሩ ላይ ነስንሶ በዝቅተኛው የመንግስት ጡሮታ(ለምግብ እህል መግዣ ሳይሆን ለማስፈጫ የማይሆን ክፍያ) ይዞ ተሰናበተ፡፡ እኛ የሰራተኛው ልጆች ኳስ እንጫወትበት ከነበረ ሜዳ በዱላ ተብለን ተባረርን በርቀት ነጭ የለበሱት በፍተሻ ሲገቡ አየን፡፡ በነፃ እንዋኝበት የነበረ ገንዳ አባቶቻችን በቀን ከሚከፈላቸው ክፍያ በላይ በሆነ መግቢያ ነጭ ለባሾቹ ያላባቶቻቸው ይሞላጠፉበታል፡፡ እኛ ምን አደረግን? ሜዳውን ለመጫወቻ ስንከለከል እናቶቻችንን ቆሎ አስቆልተን ገዥ ፍለጋ መንገድ ላይ እንውላለን፡፡ መዋኛ ገንዳውን ቢነሱን አባይ ከአዞ ጋር ታግለን ሰውነታችንን ፣ ሃሞታችንን ፣ ንዴታችንን… በቀዝቃዛ ውሃ እንታጠባለን፡፡ እናቶቻችን ምን ጠየቁ? የፋብሪካው መዝናኛ ክበብ የመዋኛ ገንዳውን ጨምሮ አሁን ስሙን ረሳሁት(ምን ላድርግ በጎ ነገር ያደረጉልኝን እንዳልይዝበት ጭንቅላቴን በጠላትነት የሞሉት የዚህ ትውልድ አባል ነኝ) በአንድ ደግ ሰው ለሰራተኞች በስጦታ ከረጅም አመት በፊት የተበረከተ ነው፡፡ በነገራችን ላይ የሰውየው ሃውልቱ ግቢ ውስጥ አሁን ድረስ አለ፡፡ እና እናቶቻችን ምን ጠየቁ? የሰራተኛው መዝናኛ ክበብ ተሰጥቶን ተደራጅተን እንስራበት:: ወቅትያ ምን አለ--ይሄ ሰራተኛ ክበብ የባንዳዎቹ ልጆች የነ ዘረዓይ ነው አለ፡፡ ወይኔ አያቶቼ ……. ብሞትም አባቶቼማ አልልም ጭራሽ ከ40 አመት በላይ ያለሰው ….. ከዛስ ቤተሰቦቻችን ምን ሆኑ? ትንሽ መታከሚያ አቅም ያላቸውን አማኑኤል ሆስፒታል የሰርተፊኬት ማስረጃ ዝርዝርን ተመልከታ፡፡ ለሌሎቹ … ኧረ ይቅርብህ ይህን ሁሉ ፀበል ቤትስ አላዞርህም፡፡ ብቻ ግን አንድ ነገር ልንገርህ የያዝከው መንገድ ቀጥተኛ እና ብቸኛ አማራጭ ነው!!!!!!!!!!!! እነ ጎይቶም ምን አደረጉ; ከነሱ ጋር ተደምሮ 1300 ሰራተኛ ቀጠርን ብለው የሰው ደም እየመጠጡ 18908 ሜ2 መሬት ይዘው ይንደላቀቃሉ፡፡ የኛ አያቶች በደማቸው አስተከሉልን ፡፡ የኛ አባቶች ………………………… የባንዳዎች ልጆች …………………. እኛ ……………. ለሁሉም መለክ Google ላይ ግባና Bahir Dar Textile Mills Share Company ብለህ ሰርች አድርግ በራሳቸው የተፃፈውን ታገኛለህ