Bete Amhara

Bete Amhara

Friday, June 26, 2015

Messafint Ze Amhara
ትንሽ ስለ ጎንደር አማሮች ከኢኮኖሚ ጨዋታ ውጭነት። ከአማሮች ምድር ሁሉ ህወሓት በከፍተኛ ሁኔታ የጨፈረችበት ምድር የጎንደርን ምድር ነው ። ጎንደር ላይ መላው አማራን የሚመግብ ሃብት ነበር ። የሰጡትን የሚያበቅል ለም መሬት አለን። ህዝቧም ከመስራት ቦዝኖ አያውቅም።ሩዝ፣ ሰሊጥ ፣ጥጥ፣ ጤፍ፣ሽንብራ፣አተር ፣ኑግ፣ባቄላ፣ነጭ አዝሙድ ፣ጥቁር አዝሙድ፣ ጓያ፣በርበሬ፣ዳጉሳ፣በቆሎ፣ማሽላ፣ዘንጋዳ፣ወደሃክር፣ገብስ፣ ስንዴ ፣ዱራኛ ፣ ሽንኩርት ……በበቂ ሁኔታ ጎንደሮች ያበቅላሉ እንዲሁም ብዛት ያላቸው የቀንድ ከብቶችንም ያረባሉ።ከፍተኛ የአሳ ምርትን አለ። የማር ምርትም እንዲሁ ሞልቷል። ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኘው ገንዘብ ከዲያስፖራ የሚላከውም ወደዚች ምድር ነው።ታድያ ምን ዋጋ አለው! ይህን ሁሉ ሃብት በህወሓት የትግራይ ነጋዴዎች በየቀኑ እንዘረፋል።
ሰዎቹ ከጎንደር የሚያገኙትን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ጎንደር ላይ አንዲት የረባች ፋብሪካ እንኳ ሊከፍቱባት አልፈለጉም። እንደዛ ካደረጉ ህዝቡ ፋብሪካቸው ውስጥ እዬተቀጠረም ቢሆን በመጠኑ በኢኮኖሚ ማደግ ስለሚችል እንደዛ አያደርጉም። ቀን ከሌት ኢኮኖሚያችን ያለተቀናቃኝ ያልቡታል።ወተቱን ወይ ወደ ትግራይ ወይ ወደ ሌላ ቦታ ይወስዱታል። አለቀ።
የህወሓት ሰዎች ከጎንደር ገበሬዎች ከፍተኛ ሰሊጥ እና ጥጥ አምራች መሬት እንደቀሙ ይታወቃል።አሁን ሰሞኑን ደግሞ በጣም ሰፊ ለም መሬት በቋራ እና በአርማጭሆ በኩል ያለውን ለሱዳን መስጠታቸው ተረጋግጧል። ከመሬታችን ጠብታ ነገር እንኳ እንዳናገኝ ተደርገናል። አማራን ማደህየት በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራባት ያለች ምድር ጎንደር የመይሳው እናት ናት።
ዛሬ ደግሞ የሰማሁት ዜና እንዲህ ይላል: -
"ጎንደርን ከ ሜትሮፖሊታን ዝርዝር ለምን ተሰረዘች????????????
ጎንደርን ከሜተሮፖሊታን ከተሞች ዝርዝር ህዉሃት መሰረዙን የዉስጥ ምንጮች ገልፀዋል፡፡ ከተማዋ ከ አ/አ በመቀጠል በዝርዝሩ የተቀመጡትን መስፈቶች ለምሳሌ የህዝብ ብዛት፤ የቱሪዝም መዳረሻነትን፤ የከተማ የገቢ ምንጭን፤ ለኑሮ ተስማሚነትትና የመሳስሉትን ብታሟላም ያለምንም ምክኒያት ከሜተሮፖሊታን ዝርዝር እንድትሰረዝ ተደርጓል፡፡
ከተማዋ ከመንግስትና ከአለም አቀፍ የከተሞች ልማት ፈንድ የምታገኘዉን ገንዘብ ከመከልከሉም በላይ ከተማዋ ለምንም አይነት ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት የቴክኒክና የገንዘብ ድጋፍ እንደማይደረግላት ታዉቋል፡፡ ከተማዋ ኢንዱስትሪ ዞን የሚባል ነገርም አይኖራትም፡፡ ከተመረጡት ከተሞች መካከል መቀሌ፤አክሱም፤ አዲስ አበባ፤ ናዝሬት፤አዳማ፤ጅማ፤አዋሳ፤በህርዳር፤ደሴና ኮምቦልቻና ንዝሬት ይገኙበታል፡፡
ይህም ሆነ ተብሎ የታቀደና ከተማዋን ለመግደል ያለመ የህዉሀት ስትራቴጅ መሆኑን ከራሳቸዉ ከፍተኛ የደህንነት ምንጮች ለመገንዘብ ችያለሁ፡፡ ……"
እንግዲህ ተመልከቱ ከአማራ ክልል በትልቅነቷ እና በንግድ እንቅስቃሴዋ አንደኛ የሆነችው ምድራችን ይህ እድል ተነፈጋት። አማራን ሲያደኸዩ እንዲህ ነው። ሁሉ ነገር ያማል!! የአማራ ልጆች በሙሉ ይህ ነገር ሊስቆጫችሁ እና እልህ ውስጥ ሊከታችሁ ፣ሊያናድዳችሁ ይገባል።
አሁንም የጎንደርን ጉዳይ እመለስበታለሁ…