Bete Amhara

Bete Amhara

Wednesday, June 17, 2015

የአማራው ኤሊትና የኤርትራ ጉዳይ


የአማራው ኤሊትና የኤርትራ ጉዳይ ኃይለገብርኤል አያሌው የቀድሞው የመዐህድ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሕብረት ም/ሊቅመንበርና የሞረሽ መስራች አባል ከፋሽስት ወረራ በሃላ በሃገራችን በፖለቲካ አጀንዳነት ያቆጠቆጠው የብሄረትኝነት እንቅስቃሴ በተለይ በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል የነበረው የኤርትራ ክፍለሃገር ከረጅም ዘመን የጣልያን ቅኝ አገዛዝ ነጻ ወጥቶ ከእናት ሃገሯ ጋር ከተቀላቀለች በሃላ የተከተለው የእንድነትና የራስገዝ አስተዳደር ጥያቄ ውስጥ ውስጡን ሲብላላ ቆይቶ የኤርትራን ነጻነት በሃይል ለማስመለስ ወድ ትጥቅ ትግል የገባው ጀብሃና ተከትሎት የተነሳው ሻአብያ የፖለቲካቸው የማዕዘን ድንጋይ የፀረ ቅኝ አገዛዝ ትግልና የፕሮፓጋንዳቸው መሰረት ባደረጉት የአማራው ሕዝብ ቅኝ ገዥነት ላይ በከፈቱት የሃሰት ጦርነት ይህ ነው የማይባል ስም ማጥፋትና ሰቆቃ መፈጸማቸው ታሪክ የማይዘነጋው ሃቅ ነው። በኤርትራ በርሃዎች የተጀመረው የአማራውን ስም የማጉደፍና የማጠልሸት ፕሮፓጋንዳ በግብታዊና ከጠባብ አመለካከት ተነስቶ የተጀመረ ማስረጃ አልባ ውንጀላ ቢሆንም ያለመታደል ሆኖ ይህው የመከነ እኩይ አስተሳሰብ እንደወረደ በመቀበል የአማራ ተወላጅ የሆኑት የዩንርስቲ ተማሪዎችን እንደ ዋለልኝ መኮንን ያሉ ጭምር በመመረዝ በቅጡ ባልተረዱት አመለካከት በጥራዝ ነጠቅነት ያስተጋቡት መፈክር ስጋና አጥንት አበጅቶ በኢትዮጽያ ብሔረተኞች እንዲፈጠሩ አጋዥ ከመሆኑም በላይ የኤርትራ ተገንጣይ ሃይሎች የዛሬውን የኢትዮጽያ ርዕሰ መንግስት ለመሆን የበቃው የትግራዩን ነጻ አውጪ ድርጅት ከአሮጌ ጠመንጃ ጋር ሱሪ አስታጥቆ በኢትዮዽያ ህልውና ላይ ሌላ የውክልና ጦርነት እንዲቀሰቀስ ማድረጉ አይዘነጋም። ሕወሐት ከሻብያም በላይ ተራምዶ የአማራውን ሕዝብ ለማጥፋትና ኢትዮጽያን የመበታተ አላማ አንግቦ በመነሳት ትግራይን ገንጥሎ መንግስት እመሰርታው በሚል የገባበት ሽፍትነት ሁኔታው ተለውጦ በእቅዱም በአላማውም ያልነበረውን ኢትዮጽያን ጠቅልሎ የመግዛት ዕድል በእኛው ስንፍናና ተላላነት በመቀዳጀቱ ይህው በመንግስትነት ሽፋን ዝርፊያና ዘረኝነትን አንግሶ ትውልዱን እያጠፋ እያሰረና እየገደለ ቀጥሏል። ሻምበል ዘውዱ የቀድሞው የመዐህድና የአርበኞች አመራር ሻብያ ወይም አሁን አለም ዓቀፍ እውቅና ያለው የኤርትራ መንግስት ለረጅም ዘመን ባካሄደው ትግል ውስጥ አንግቦት የነበረው አብዛኞቹ መፈክሮች በግዜ ሂደት ወይበው በሁኔታዎች ተጽዕኖ ተለውጠው በተፈጠረው አዲስ የሃይል አሰላለፍ ውስጥ ዋና የህልውናው ጠላት ሆኖ በተገኘው በትላንት ተላላኪው ሕወሓት ወያኔ ጋር የጌታና ሎሌነቱ ዘመን እብቅቶ በጦርነት ፍጥጫ ውስጥ በሚገኝበት በአሁኑ ወቅት በተፈጠረው የሃይል መሳሳብና ባለው ነባራዊ ሁኔታ አንጻር ተንተርሰው አዲስ የወዳጅነት ምዕራፍ የከፈቱት ኢትዮዽታዊ ሃይሎች አማራጭ የትግል ስልታችውን ገቢራዊ ለማድረግ ከኤርትራው መንግስት ጋር እያደረጉ ያለው ግንኙነት በኢትዮጽያውያን ዘንድ በድጋፍና ተቃርኖ መሃከል ሲዋዥቅ ቆይቶ በአሁኑ ወቅት በኢትዮዽያ ውስጥ ባለው ዘረኝነት የፖለቲካ እመቃና የነጻነት እጦት የሰላማዊ ትግሉን ምህዳር እጅግ ያጠበበው ከመሆንም በላይ በሰላማዊ መንገድ ለውጥ ይገኛል የሚለው ተስፋ ጭለማ የዋጠው በመሆኑ አብዛኛው ኢትዮዽያዊ በኤርትራ የተጀመረውን እንቅስቃሴ የመደገፍ አዝማሚያ እያሳየ ያለበት ወቅት ላይ ነን ። ይህን ታሪካዊና ወቅታዊ ሁኔታ እንዳነሳ ያስገደደኝ ባለፉት ወራት ወደ ኤርትራ ያቀኑትን የመዐሕድ/መኢአድ ወጣቶችን አስመልክቶ ያገባናል የሚሉ በቀድሞው የቅንጅት እንቅስቃሴ ዙሪያ የነበሩ ወገኖች ውስጥ ውስጡን በመሰባሰብ ወጣቱ እዛው ሃገር ውስጥ እንዲታገል እንጂ ወደ ኤርትራ መሄዱ ማስቆም አለብን በሚል በአዛኝ ቅቤ አንጓችነት እንቅስቃሴ የጀመሩ ሲሆን ይህ አላማቸው ከበስተጀርባው ያነገበው ተልዕኮ ምን እንደሆነ ለመረዳት ለግዜው ግልጽ ባይሆንም ፤ የትግሉ መርሆ ብለው የያዙት አቋም ያለምንም የውጭ ዕርዳታና የጎረቤት ሃገር ድጋፍ የትጥቅ ትግልን ጨምሮ ያሉትን ማናቸውንም መንገዶች በመከተል ሃገራችንን መታደግና ወያኔን ማስወገድ እንችላለን የሚል በጎ እቅድ በግራ እጃችው ይዘው ፤ በቀኝ እጃቸው ደግሞ ከኤርትራ በመነሳት የነጻነት ትግሉን እናካሂዳለን የሚሉትን ሃይሎች የሚቃወም መፈክር አንግበው ውዝግብ ለመፍጠር የሚያደርጉትን እቅድ አላስፈላጊነት ለማስረዳት ቢሞከርም ያለመቀበል ገታራ አተያይ ያለ በመሆኑ ድንገት የውዝግብ አጀንዳ ቢከፈት ሕዝባችን እንዳይደናገር ከወዲሁ ግንዛቤ ለመፍጠር ነው። እነዚሁ ወገኖች የጀመሩት እጅ እግር የሌለው የትውልዱን ሰቆቃዊ የህልውና አጣብቂኝ ያልተመረኮዘ በጭፍን ሃገር ወዳድነትና ቡድናዊ ፍላጎት ለማሳካት ውሃ የማይቋጥር ግብዝ አመለካከት ይዘው ሕዝብን ለማደራጀት መሞከር ትርጉም ያለው ውጤት እንደማያስገኝ ከወዲሁ መገመት ቢቻልም የሚያሳዝንው ግን በዚህ የዜጎች አንድነትና የተቃዋሚ ሃይሎች ትብብር ከመቼውም ግዜ በላይ በሚያስፈልግበት ወቅት ላይ ሆነን ቢያንስ በመሰረታዊ አስተሳሰብ እስከተገግባን ድረስ ታጋይ ሃይሎችን የማውገዝና የመኮነን እንቅስቃሴ ማካሄድ እንደ ትግሉ አካል አድርጎ መቁጠርና ይህንንም ለማስትናገድ መሞከር በሃገርና በትውልድ ስቃይ ላይ ነዳጅ እንደማርከፍከፍ የሚቆጠር ነው። ሌላው የትግል አጋሬ የነበረው አማራውን ለማደራጀት የደከመው የሞረሽ ወገኔ ሊቀመንበር አቶ ተክሌ የሻው ባለፈው ሰሞን በሺህ የሚቆጠር ታዳሚ በተገኘበት የኢትዮሲቪሊቲ የፓልቶክ ሩም በመገኘት ካቀረበው በሳል የታሪክ ትንተና ባሻገር ፤ በኤርትራ የተጀመረውን ትግልና ሻብያን አስመልክቶ ያለው አቋምና ያንጸባረቀው አስተሳሰብ እና ወዳጄ የምለው የእዲስ ድምጽ ሬድዮ ባለቤት አርቲስት አበበ በለው በዳላስ ያቀረበው ወቅቱን ያልመጠነ ፤ ነባራዊውን የአካባቢውን ጂኦ ፖለቲካና የሃይል አሰላለፍ ግምት ውስጥ ያላስገባ ስሜታዊና ግትር አመለካከት ፤ ሕዝባችን እየወሰደ ያለውን እርምጃ የሚጻረር ለነጻነቱ ለመፋልም ቆርጦ ሕይወቱን ለሞት አሳልፎ የሰጠውን ትውልድ መስዋዕትነት ዋጋ የሚያሳጣ ሃላፊንት የጎደለው አተያይ ተገቢና ወቅታዊ አለመሆኑን ለማስገንዘብ ነው ። አቶ ተክሌ ኤርትራንና በዛ ያለውን ትግል ጭቃ እየቀባ በሚያጣጥልበት በዚያን እለትና ሰዐት በሰላም ለመታገል ሕጋዊ በሆነ መልኩ እየታሰሩ እየተገረፉና እየተዋረዱም ቢሆን ታግሰው የተነሱለትን ሕዝባዊ አላማ ለማሳካት ደከመኝ ያላሉት የመኢአድ አባላትና አመራሮች በወያኔው የምርጫ ቦርድ ድርጅታቸውን ተቀምተው በጉልበት ከተባረሩ በዃላ የሰላሙ መንገድ ሲዝጋባቸው የአመጹን ትግል እንዲመርጡ በመገደዳችው ባለፉት ወራት ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ወጣቶች በቀድሞው የደርጅቱ ህዝብ ግንኙንት ሃላፊ ወጣት ተስፋሁን አለምነህ መሪነት ወደ ኤርትራ መግባታችው ዜናው እይተሰራጨ ነበር። አበበ በለው በዳላስ በኤርትራ ያለውን ትግል እያንጓጠጠ በተሳለቀብት ባለፈው ሰሞን በተቃዋሚ አባልነታችው ተጠርጥረው ከከጎንደርና ጎጃም ተይዘው መዕከላዊ የታስሩትን ወገኖች የተወለዱበት ብሔር እየተሰደበ ብልታቸ ተቀጥቅጦ መኮላሸቱን በእደባባይ በፍርድ ቤት ውስጥ ልብሳችውን እውልቅው እያሳዩ የወገን ያለህ ድረሱልን በሚሉብት በዚህ የመከራ ግዜ ቅንጡው አርቲስት ያሏለበትን ሰላማዊ ትግል ሊሰብክ እርቅና መግባባትን ሊያስትምር ሲባዝን በትዝብት ተከታትዬዋለሁ ። ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው እንዲሉ ፤ የፖለቲካው ትግል አልጋ በአልጋ በሆነበት ሰሜን አሜሪካ ተቀምጦ ትውልዱ አማራጭ የትግል መንደርደሪያ መሸሸጊያ አድርጎ ለወሳኙ ትግል የሚያድርገውን መነሳሳት ማንኳሰስና ትውልዱ ሊሰዋለት የወደደውን አላማ ማውገዝ አላዋቂነት ብቻ ሳይሆን ተራ ግብዝነትም ነው። ሞረሽ እንደ ሲቪክ ተቋም ሲመሰረት ካስቀመጣቸው መተክላዊ አቋሞችና የአሰራር መርሆች ውስጥ አንዱ በየትኛውም ተቃዋሚ ድርጅቶች ሕዝባዊና ማህበራዊ ተቋማት ውስጥ ያሉ የአማራና የሌላ ብሄር ተወላጅ ግለሰቦችን በመቅረብ አላማውን በማስተዋወቅ ወዳጅ የማብዛትና ጠላትን የመቀነስ ስልት በማንገብ የእርስ በርስ መጠላለፍን የሚያስወግድና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን በማጎልበት በሕወሀት ሴራ የተበከለውን መቃቃር ለማርገብ ጥረት ማድረግ የሚችል ሃይል ለመፈጠር ነበር። እንደ አለመታድል ትልቁን ሕዝባዊ ተልዕኮ ለማሳካት የግል ስሜትን ተቆጣጥሮ ያነገቡትን እላማ ከማስቀድም ይልቅ ትንንሽ የንትርክ ሰበዞችን መምዘዝ በሚያስቀድሙ ፤ አዲሱን ትውልድ ለማድመጥ ጆሮዋችው የተደፈነና እንቆምለታለን የሚሉትን ወገን የማይወክል ፤ጥበብ የራቀውና ዲፕሎማሲያዊ አቀራረብ የተለየው ፖለቲካ በማራመድ ተለዋዋጩን የአካባቢያችንን ሁኔታ ገምግሞ ተመጣጣኝ አቋም ይዞ መገኘት በሚያስፈልግበት ወቅት በአሮጌ የታሪክ ቡሉኮ ተጀቡኖ ዘመኑን ያልዋጀ ሃሳብ ይዞ አማራን ያህል ህዝብ አደራጃሁ ብሎ ማሰብ ቀልድ መሆኑ ሊገባችው አለመቻሉ ያስዝናልም ፤ ያሳፍራልም። በአሁኑ ወቅት ከየትኛውም የኢትዮጽያ አካባቢ ካለው ወገናችን በአማራ ክልል ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ የወጣት ሃይል በኤርትራ ያሉትን ታጣቂ ሃይሎች በመቀላቀል ላይ ይገኛል። ከዚህ ወደ ኤርትራ በርሃ ከሚያቀኑ ወጣቶች ውስጥ ከአንዳዶቹ ጋር በሃገር ቤት በሰላማዊ እንቅስቃሴ አብረን የሰራን ከመሆኑም በላይ በሰላማዊ ትግል የቆረቡ በዚህም አቋማቸው ከወያኔ ብቻ ሳይሆን ተቃዋሚ ነን ከምንለው ጭምር ተጽዕኖ የተደረገባችው ጽናተ ብርቱ ወጣቶች ለሰላማዊ ትግሉ ማድረግ ከሚጠበቅባችው በላይ ዋጋ ቢከፍሉም ያለው አገዛዝ ሊገባው የሚችል ባለመሆኑ በሚገባው ቋንቋ ሊያናግሩት ወደ ግንባር ተንቀሳቅሰዋል ይህ በእንዲህ ባለብት ሕዝባዊ እንቢተኝነቱ እየጋመ አብዮት ያዘለ የለውጥ ዳመና ባንጃበበት በዚህ ወቅት በዉጭ በዲያስፖራ ያለነው ሕዝባዊ ትግሉ ለቅልበሳ እንዳይጋለጥ ነቅተን መገኘትና የእርስ በእርስ መጠላለፍን የሚያስወግድ ቅራኔን መፍቻ ባህል ማዳበር ይኖርብናል ። በዚህ ዘመን የተፈጠረው ትውልደ ኢትዮጽያዊ ወጣት ዜጋ በሃገሩ የኢኮኖሚ የእኩልነትና የነጻነት ማጣት እንገፍግፎት ሃገሩን ለቆ እየወጣ እየደረሰበት ያለውን ቅስም ሰባሪና እዋራጅ መከራ ጽዋው ሞልቶ እየፈሰሰ ባለበት ጭለማ ውስጥ ሕልውናው በመኖርና ባለመኖር አጣብቂኝ ውስጥ በወደቀበት የፈተና ግዜ እንደ ሞረሽና ፥ እንዳንድ የአማራው ተቆርቋሪ ነን የሚሉ ወገኖች ዘሩ እንዲጠፋ ቀን ከሌት መቃብር የሚቆፈርለትን ታላቁን የአማራ ሕዝብ እታደጋለሁ ብሎ የተነሳ ቡድን በእንዲህ ያለ ግዜ ሊረዳው የፈቀደውን የመርዳት ፍላጎት እያሳየ ያለን አንድ የጎረቤት ሃገርና መንግስት ፈቃደኝነቱን በይበልጥ እንዲያጠናክር ወደ ላቀ ደረጃ እንዲያሸጋግር ብልህነት ያለው አያያዝን መጠቀም ተገቢም አስፈላጊም መሆን ሲገባው ፤ አለያም የህዝባችንን ስሜት ግምት በማስገባትና ሞትን አምልጦ የኮበለለውን ወገን ሲባል ፤ ገለልተኛና ዲፕሎማሲያዊ ዘዴን እንደመከተል ብል የበላው የታሪክ ድሪቶ እየጎተቱ እዛ ላይ ችክ ማለት የፖለቲካ ብስለት የጎደለውና ሃላፊነትን የዘነጋ አካሄድ ነው። እንዳለመታደል ፖለቲካችን የትችትና ሂስ የማስትናገድ ባህል ስለሌለው እድገቱ እንዲገታና ባልቴታዊ የስማ በለው የአሉባልታ ባህል እንዲዳብር በማድረጉ ሠፊና ጥልቅ ማህበራዊ ጉዳት አስከትላል ። ከዚህም አንጻር የአቶ ተክሌም ሆነ የወዳጄን አበበ እና የሌሎችን ሃሳብን በነጻነት መግለጻችው ዲሞክራሲያዊ መብት በመሆኑ ባከብርም ፤ በዚህ የጭለማ ግዜ ጥያቄያችን ወርዶ ወርዶ እንደ ሕዝብ የመኖርና ያለመኖር ደረጃ አዘቅት ውስጥ በወደቀበት ሁኔታ ላይ እያለ ዳር ቆሞ መመጻደቅና ጸጉር መሰንጠቅ ተገቢ ካለመሆኑም በላይ ይህ የኔ ትውልድ የሆነው በዘመናችን ለፖለቲካ ተሳትፎ አደባባይ ብቅ ያለውና በትግሉ ሜዳ የተገኘው ወጣት በለጋ እድሜው ብልቱ እየተኮላሸ ጥፍሩ እየተነቀለ ኑሮውን በእስር እንዲያሳልፍ ተፈርዶበት ፤ በነገስው ዘረኝነት ሃገሪቷ ልትፈርስ ጠርዝ በደረስችብት በዚህ ክፉ ግዜ ሕልውናውን ለማቆየት ማንን ነው የሚጠጋው ወዴትስ ነው የሚሰደደው ፤ ሱዳን አንስቶ ያስረክበዋል ፤ የኬንያ ፖሊስ በገንዘብ ይለውጠዋል ፤ ሱማሌ ያርደናል ፤ ከቶስ በሃቅ እንነጋገር ከትባለ ከኤርትራ የተሻል መሸሸጊያ ለዚህ ትውልድ አለን? በተለይ በምዕራቡ ዓለም ተቀምጦ ሳይደራጅ የግል ዝናን ለመገንባት ጥቅሙን ለማስተጠብቅና ከጠባብ ቡድናዊ ፍላጎት በመነሳት ለራሱ የሚመቸውን እቅድና ስትራቴጂ ልቀይስ የሚለው ወገን መገንዘብ ያለበት ሃገራችን ያለችብት አደገኛ ሁኔታ ጊዜ የማይሰጥ በመሆኑ በቅንነት በጋራ ቆመን ለተሻለ ለውጥ ብንቀሳቀስ የመከራውን መነገድ እንደሚያጥር መረዳት ይኖርብናል። የጠላትን ጠላትነቱን ያለመርሳት መርሕ የለም እንጂ የሚኖር ቢሆን ኢትዮዽያችን ከጥንት እስከዛሬ ያደሟትን የቅርብና የሩቅ ጠላቶቻችንን ብንቆጥር በእርግጥ ከማን ጋር ቆመን ልንገኝ ነበር። በይቅርታ ከማልፍ ይልቅ ስንቱን አጥፍተን ስንቱን ልንቀጣ ፤ ከስንቱስ ተኳርፈን እንዘልቀው ነበር ፤ ቱርክን፤ ግብጽን ፤ እንግሊዝን፤ ጣሊያንን ፤ ሱዳንን የዚያድባሬን ሱማሌ ወዘት… የትኛውስ ሃገር ነው አፋችንን ሞልተን ወዳጅ የምንልው አልነበረም ወደፊትም አይኖርም ፥ ያለንበት ዘመን ፖለቲካ ይህን እይነት ደረቅ የስብስቴ ጊዜ አስተምህሮ የሚያስተናግድ ሳይሆን ከነአባባሉም ዘላቂ ጥቅምን እንጂ ዘላቂ ወዳጅነትም ሆነ ጠላትነት በፖለቲካው አለም የለም ። ዛሬ የሃገራችንና የህዝባችን ህልውና ጠላት የሆነው የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር በዝርፊያና ቅሚያ ራሱንና ግብረዐበሮቹ በመጥቀም አንድ ትውልድ በስደት፤ በጎዳና አዳሪነት በረሃብና ድንቁርና እንዲጠፋ ፈርዶበት በዓለም የመጨረሻው የውርደት ጠርዝ ላይ አስቀምጦን መከራችንን እያየን በምንቃትትበት ሁኔታ ውስጥ ያሉትን የጭላንጭል የተስፋ የትግል ብልጭታዎች ለማምከን ቂመኛና ቅንጡ የፖለቲካ አጀንዳ ማራገብ ተቀባይነት የለውም። ይህን ስል ችግሮች የሉም ማለት አይደልም ብዙ በማስርጃ የተደገፉ እንከኖችን በግል አውቃለሁ ፤ አሁንም በኤርትራ በርሃ የመሸጉና ከትግሉም ተለይተው ወደ ሌላ ሃገር የተሰደዱ የቀድሞ ወጣት ጓደኞቼና ልባዊ ወዳጄና የትግል አጋሬ የነበሩት በሰላማዊው ትግል ይህ ቀረሽ ተጋድሎ ያደረጉትና በሗላም ወደ በርሃ ወርደው አርበኞች ግንባርን በመቀላቀልና አመራር በመስጠት የደከሙት ጀግናው ሻንበል ዘውዱ ያሳለፉትን ውጣ ውረድ በተወሰነ ደረጃ ተገንዝቤያለሁ። ነገር ግን በኤርትራ መንግስትና በተቀረው ኢትዮጽያዊ ተቃዋሚ ሃይሎች መካከል የተዘራው ያለመተማመንን ለማስወገድ ከሁለቱም በኩል ያሉ ወገኖች የሚደረጉትን በጎ ጥረት በበቂ ያለማገዝና ፤ ከዛም በላይ በተለይ ድጋፍና ዕገዛ ከምንፈልገው ሕልውናችን ሊከስም ጠርዝ የደረሰው ኢትዮጽያዊ ወገኖች ዙሪያ የሚታይው ቅደም ተከተሉን የሳተ ፍላጎት ግልብና ሃላፊነት የጎደለው ፕሮፓጋንዳ በኤርትራ በኩል የምንልፈገውን ድጋፍ ለማግኘት ሳንካ ሊሆንብን እንደሚችል መረዳት ይኖርብናል። በዓለማችን ካሉ ሃገሮች በድህነት በችጋርና ስደት ከተዋረድነው በላይ በሃገራችን የተሻለ መጠነኛ መብትና ቢያንስ የኛ የምንለው መንግስት አጥተን ከከፋው የስደት መከራ ሃገራችን ለመመለስ እንኳ የማንችልበት ሃገር አልባዎች የሆንበት ደረጃ ደርሰን በቀን ጨለማ ተውጠን በምንቃትትብት በዚህ ክፉ ቀን በሚቻልውና በማንኛውም መንገድ ተንቀሳቅሰን ከብራችንን ማስመለስ ሲገባ የትግልና የሜዳ ምርጫ ላይ መነታረክ በሃገርና በትውልድ ላይ መቀለድ ነው። ከዚህም በላይ ለነጻነት በሚደርግው ትግል ዙሪያ ያለን የመርህ የጽናትና የትብብር ሁኔታ አለመጠናከሩና እርስ በእርሱ የሚጋጭ ሆኖ በመቆየቱ በኤርትራ ከተጀምረ የቆየው የብረት ትግል ያለ ተጨባጭ ውጤት ቢቆይም ከቅርብ ግዜ ጀምሮ ይህን ሁኔታ በመለወጥ የተሻልና ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ እየጎለበተ በመምጣቱ ከአውሮፓና ከአሜሪካ ትግሉን ለመቀላቀ የተጓዙትን በሃገር ውስጥ በሰላም የመንቀሳቀስ እድል ያጡ ወጣቶች በገፍ ወደ ትጥቁ ጎራ በመትመም ለለውጥ የሚደረገውን ትግል ወደ ወሳኝ ምዕራፍ ለማሽጋገር እያደረጉ ያሉትን የመስዋትነት ሰልፍ በሞራልና በገንዘብ የመደገፍ ገዴታ ያለብን በውጭ ያለነው ወገኖች ቢያንስ መደገፍ ባንችል እንኳ ላለመስማማት ተስማምተን የሌሎችን እንቅስቃሴ ላለማደናቀፍ መሞከሩ አስተዋይነት ነው። እንደ እንድ ነጻንቱን እንደሚሻ ዜጋ ባልፉት 24 እምታት ውስጥ ለዲሞክራሲ ለዕኩልንትና ለሕዝቦች ዘላቂ ሰላምና አንድነት በሚደረገው ትግል ውስጥ ማድረግ የሚጠብቅብኝን ያህል እስተዋዕጾ አለማድረጌ ቢጸጽተኝም በ1997 ምርጫ ሕዝባዊ ድላችንን እስነጥቀን ትግሉንም ለቅልበሳ ተዳርጎ ለስደት ከበቃው በኋላ ዘውትር እረፍት የሚነሳኝ በቅንነት ሃገርና ወገንን ብለው የተሰውት በእስር ያሉት ለአስከፊ ስደት የተዳረጉት ጓዶቼ ስቃይ አንሶ ዛሬም የወግኖቼ ስቆቃ ከመቀነስ ይልቅ እየባሰ ሄዶ ሄዶ አሁን ያለንብት ወቅት ላይ ብንድርስም ፤ ይህ ግፍና መከራ ተሰምቶት ወገኑን ለመታደግ በስፋትና በጥራት ተደራጅቶ መገኘት ከነበረብት የዲያስፖራው ማህበረስብ ዘወትር አደባባይ የሚገኘው ቁጥሩ አነስተኛ ከመሆኑም በላይ ላለምስማማት የተደገመብት እስኪምስል ድርስ ማለቂያ በሌለው እጅግ ጥቃቅን ልዩነቶች ተተብትቦ ቆምኩለት የሚለውን ዓላማ በተገቢ መልኩ ከመግፋት ይልቅ በሌሎች እንቅስቃሴ ላይ ሳንካ በመፍጠር በሚፈጠርው ትርምስ ከግዜ ወደ ግዜ የዴሞክራሲው ሃይል እየሳሳ እንዲሄድ ከፍ ያለ እስተዋጽኦ ማድረጉ ሃዘናችንን ከፍ እንዲል እድርጓል ። በሃገር ቤት እንኳን የተቃዋሚ እባል ሆኖ እይደለም ከሆነ ሰው ጋር እንኳ እብሮ መታየት ዋጋ በሚያስከፍልበት የፖለቲካ ድባብ ውስጥ ጥረት የሚያድርጉትን ወግኖች ለማክበርና እውቅና ለመስጠት የምንቸገር ባለንበት ፤ በእንጻሩ እንድ ሰልፍ ላይ ያውም በስካርብና በባርኔጣ ተከልለን በመገኘታችን የምንኩራራ የዋሆች በበረከትንበት የምዕራቡ ዓለም የነጻንት ሕይውት ውስጥ እየኖርን በምን የሞራል ሚዛን ላይ ሆነን እንድሆነ በሚቸግር መልኩ በረሃ የወረዱትን የቀን ሃሩር የሌሊት ቁር መራብ መጠማትን ፤ መውደቅ መንሳትን ፤ ከዚያም በላይ መተኪያ የማይገኝለትን እንድያ ሕይውታችውን ለመስዋት ያቀርቡትን ደፋሮች የኔ ብጤው ተቃዋሚ ነኝ ባይ ባልተገራ ቃላት ማብጠልጠል ምን የሚሉት ሞራል የጎደለው የፖለቲካ ባህል ነው። እንዳርጋችውን የመሰለ የእድሜ ልክ ፖለቲከኛና ምሁር እንቦቃቅላ ሕጻናቱን ቤት እስቀምጦ በርሃ ሲወርድ ጝራና ቀኙን ሳያይ ይመስለናል ፤ ሻቢያን ሲያሞካሽና ኢሳያስን ሲያዳንቅ ያለፈ ታሪካቸውንና የወድፊት ዕቅዳችውን ሳያቅ ቅርቶ ይመስለናል ፤ አይደለም ትግሉ የሚፈልገው አቀራረብ በመሆኑ ነው። ፖለቲካ ራሱን የቻለ ጥበብ ነው ፤ ፍላጎትን ከእቅርቦት ትላንትን ሳይሆን ዛሬን ጀብደኝነትን ሳይሆን ፤ ዲፕሎማሲን ፤ ሰጥቶ መቀበልን ፤ እካባቢያዊ ሁኔታንና የሃይል አሰላለፍን ማወቅ መተንትን በስከነ ሁኔታ መመልከትን የሚጠይቅ በዕውቀትና በችሎታ የሚስራ ሙያ እንጂ የኔ ብጤ ሳይሞቅ ፈላ በስሜት እውታር የሚጀምረው ተግባር አይደልም። በእኔ እምነት የሃግራችን ችግር በጠረጼዛ ዙሪያ ሰላማዊ መፍትሄ ቢገኝ ደስተኛ ነኝ ፤ እርቅና መግባባት ተፍጥሮ ትላንትን ለታሪክ ትተን ነገን ወደ ተሻለ ቀን ለመለውጥ የሚያስች መፍትሄ ፈጣሪ ቢያድለን የዘወትር ጸሎቴ ነው ፤ ነገር ግን ቀኝህን ሲመታህ ግራህን ስጠው የሚለውን መለኮታዊ ትዕዛዝ በመፈጸም የተገኘው የሰላማዊው ትግል ውጤት ቢኖር በጥፊ ፋንታ ብልትን ማኮላሸትና ጥፍርን መንቀል ከማክብር ይልቅ መናቅ መገፋትን በመሆኑ እበው ወተት እንኳ ይሸፍታል እንዲሉ በሃገራችን ውስጥ የተንሰራፋውን ሰው በላና ፋሽስታዊ የአፓርታይድ እገዛዝ ለማስወገድ በሚቻለውና በማንኛውም መንገድ የሚካሄደውን ሁለገብ ትግል የማገዝ ሃገራዊና ወገናዊ ግዴታ ያለብን ከመሆን ጎን ለጎን የሰልጠነ የፖለቲካ ባህል ለመላበስ እንደ እርግብ የዋህ እንደ እባብ ብልህ ሁን የሚለውን የመጽሃፍ ቃል በልባችን እኑረን ሃይላችንን ሃገርንና ህዝብን ለመታድግ ላይ በማድረግ ብቅ ብቅ እያለ ያለውን የንትርክ ፋይል በግዜ ዘግተን በፈቅድንውና ያዋጣል በምንለው የትግል መስክ ለመሰማራት እግዚያብሔር ይርዳን። በመጨረሻም ላስተላልፍ የምፈልገው መልዕክት ቢኖር ሃገራችንንና ህዝባችንን ለመታደግ ግዜያችንን እውቀታችንንና ሕይውታችንን ጭምር ላቀረብን ወግኖች ያለኝን ከፍ ያለ አክብሮት እይገለጽሁ ፤ በሰላም ይሁን በሃይል ፤ ከሃገር ውስጥ ይሁን ከኤርትራ ፤ በምርጫ ይሁን በሦስተኛ አማራጭ ፤ በጸሎት ይሁን በዲፕሎማሲ ብቻ ለወገን ይበጃል በምንለው በሚቻለውና በማንኛውም መንገድ የሚደርገውን ትግል ቢቻል በመደጋገፍ ካልሆነም በመከባበር የየራሳችንን ዓላማ ለማሳካት ከመትጋት ባሻግር በማይመለከተን በሌሎች እንቅስቃሴ ውስጥ ጣልቃ ከመግባት በመቆጥብ ለትውልድና ለታሪክ የሚቆይ አሻራ ለማኖር እንድንችል በዚህ መከረኛ ትውልድ ስም አደራ ለማለት እፈልጋልሁ ።