በተለያዩ ሃገራት በኢትዮጵያዊያን ላይ በተፈጠመዉ ዘግናኝ ግድያ ንቅናቂያችን ከፍተኛ ሃዘን ተሰምቶታል፡፡
ከአማራ ዴሞክራሳዊ ሃይል ንቅናቄ የተሰጠ የሀዘን መግለጫ
በሃገራችን በተከሰተዉ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ምክንት ዜጎቻችን በተለያዩ ሃገራት በስደት ቢኖሩም ከሃገራቸዉ የወያኔ ስርዓት የፈጠረዉን መከራ ለመሸሽ ቢሞክሩም በየደረሱበት እየተከተላቸዉ ፍፁም ዘግናኝ እና ለአሰቃቂ ግድያ ዳርጎቸዋል፡፡
ባለፉት 24 ዓመታት በሃገር ዉስጥ የወያኔ ስርዓት በበደኖ በጉራ ፈርዳ በጋምቤላ በመሳሰሉት ቦታዎች ወያኔ ኢትዮጵያዊያንን ከነነፍሳቸዉ ማቃጠሉ ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ፡፡ ይህን መከራ ለመሸሽ ያደርጉት ስደትም መፍትሄ አልሆነም፡፡
ይህን አረመኔ ስርዓት ማስወገድ ባለመቻላችን በሃገር ዉስጥም ሆነ በዉጭ ሃገራችን በታሪኳ አይታዉ የማታዉቅ ከፍተኛ የሆነ ብሄራዊ ዉርደት ገጥሞት እየተገላታች ትገኛለች፡፡ የእኛ መከራ እና ስቃይ ዕልቆ መሳፍርት እየሆነ ቀጣይነት እንዲኖረዉ ሌት ተቀን ተግቶ የሚታገለዉ የወያኔ ስርዓት እስከ አልተወገደ ድርስ አሁንም ከብሄራዊ ዉርደታችን መዉጣት አንችልም፡፡
በየመን በደቡብ አፍሪቃ በሊቢያ የደረሰብን አሰቃቂ ዉርደት ብሄራዊ ሃዘን በመቀመጥ ብቻ ልንወጣዉ አንችልም፡፡ ህልዉናችን ልናረጋግጥ የምንችለዉ እና ከብሄራዊ ዉርደት መዉጣት የምንችለዉ የወያኔን ስርዓት ብሄራዊ መነቃነቅ በመፍጠር መደምሰስ ስንችል ብቻ እና ብቻ መሆኑን ንቅናቄችን ማስገንዘብ ይወዳል፡፡
ንቅናቂችን ለደረሰብን መከራ ቀጥተኛ ተጠያቂ የወያኔን ስርዓት ያደርጋል፡፡ ለዚህም በቅርብ ቀን በተጠናከረ እና የወያኔን ስርዓት የሚያሽመደምድ አፀፋዊ እርምጃ ይወስዳል፡፡
ንቅናቄችን ለተከሰተብን ከፍተኛ ብሄራዊ ሃዘን የተሰማዉን ጥልቅ ሃዘን ለመላዉ ኢትዮጵያዊያን ይገልፃል፡፡
የአማራ ዴሞክራሳዊ ሃይል ንቅናቄ የአማራን ህዝብ ህልዉና መታደግ ኢትዮጵያን መታደግ ነዉ ብሎ በፅኑ ያምናል፡፡ ትናት በጉራፈርዳ በጋምቤላ በበደኖ ህፃናት እና ነፍሰ ጡሮች ሳይቀር በወያኔ ሲጨፈጨፉ እና በቁማቸዉ ሲቃጠሉ በወያኔ እና በጋሻ አዣግሬዎች አማራዎች ብቻ ናቸዉ በሚል ሲሳለቁብን የነበሩት ዛሬ በወያኔ መዘዝ መከራና ግፍ በተለያዩ ሃገራት እተቀበልን ያለነዉ በኢትዮጵያዊነታችን ብቻ መሆኑን ማወቅ ይገባችኋል፡፡
ለዚህ ነዉ ንቅናቂያችን ደግሞ ደጋግሞ አማራን መታደግ ኢትዮጵያን መታደግ ነዉ እያለ አጥብቆ የሚናገረዉ፡፡
ንቅናቂያችን ለዚህ ከፍተኛ ለሆነ የልብ ስብራት እና ብሄራዊ ዉርደት የዳረገንን የወያኔ ስርዓት ከምንጩ ለማድረቅ ሌት ተቀን በየበረሃዉ የሚከራተተዉ፡፡ በመሆኑም ዛሬም ነገም እስከ መጨረሻዉ የወያኔን ስርዓት ለማሰወገድ ማንኛዉንም መስዋትነት ንቅናቂያችን በመክፈል ለድል ይበቃል፡፡
በመጨረሻም ለመላዉ ኢትዮጵያዊያን መፅናናትን እንመኛለን፡፡
የአማራ ሕዝብ ትግል ያሸንፋል፡፡