Bete Amhara

Bete Amhara

Friday, June 26, 2015

<<ቤተ አማራ እና ኢትዬጵያዊነት>>
ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ እንደፈለገ ከሚጫዎትባት "ኢትዬጵያ" ውስጥ አባቶቻችን የሰሯትን ኢትዬጵያ ብትፈልጓት አታገኟትም ። ያቺ ኢትዬጵያ ያለችው አማራ ሕዝብ ልብ ውስጥ ነው። የአሁኗ "ኢትዬጵያ" እየፈረጠመች ሄዴች ማለት አማራ እዬጠፋ ሄደ ማለት ነው። የጥንቷ ኢትዬጵያ አስኳል፣ የጊዬን ልጅ አማራ፣ የሌለባት ኢትዬጵያ ባዶ ቀፎ ነች። አማራ ኢትዬጵያ ውስጥ ሳይሆን ያለው ኢትዬጵያ ናት አማራ ውስጥ ያለችው። ለዛም ነው የህወሓት ሰዎች ኢትዬጵያዊነትን ለመምታት አማራን መምታት ብለው የተነሱት። እየመቱትም ያለቱ የተነሱበትን አላማ ግብ ለማድረስ ነው።
ስለዚህ ለተረዳው ሰው አማራን ማዳን፣ የምንፈልጋትን (አማራ ልብ ውስጥ ያለችውን ጊዬናዊት ኢትዬጵያን) ማዳን ማለት ነው። ኢትዬጵያዊነትን ለመምታት ኦሮሞ አልተመታም ። ትግሬ ፣ሱማሌ አልተመታም ። እርግጥ ጉራጌን የመሰሉ አንዳንድ ብሄሮች አሉ የአማራን ህዝብ ኢትዬጵያዊ ፍልስፍናን የሚያራምዱ ። በዚህም ምክንያት ነው ጉራጌ የነፍጠኞች (የአማሮች) አጋር ተብሎ በተለያዩ ዘዴዎች እዬተመታ እዬተገፋ ያለው።ህወሓት በግልፅ አማረኛ ነፍጠኛ ማለት አማሮች እና ጉራጌዎች ናቸው ብላ አስቀምጣለች
ስለዚህ አማራን አሁን ካለችው ኢትዬጵያ ገንጥሎ ለብቻው እንደ ሃገር እና እንደ ነፃ መንግስት ማቆም ማለት ኢትዬጵያን መበታተን ነው ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው።አማራን ማቆም ወደ ኢትዬጵያዊነት አስኳል መመለስ ማለት ነው። ወደ ስር መመለስ ። የማያስፈልጉ ቅርንጫፎችን መቀፍቀፍ ማለት ነው። አማራነት ውስጥ ሁሉ ነገራችን አለ። እሱን ስናተርፈው ብቻ ነው የምንድነው። እራሳችን ችለን ስንኖር የሚጎልብን አንዳች ነገር አይኖርም።የተፈጥሮ ሃብት (የእርሻ መሬት፣ታላቅ ሃይቅ፣ታላላቅ ወንዞች ፣ የከርሰ ምድር ውሃ ፣ ማእድናት ፣የተለያዩ አእዝርእት) ፣ የሰው ሃይል (የተማረ፣ገበሬ፣ነጋዴ፣ጦረኛ፣እጀ ጥበበኛ፣የኪነት ሰው) ፣ ታሪክ ፣ቋንቋ ከነ ፊደሉ ፣ሃይማኖት፣ባህል ወግ …በበቂ ሁኔታ አሉን። አማራ አባቶቻችን ኢትዬጵያዊነት ብለው ሲፈጥሩ ከሌላው ህዝብ ዘንድ ከአንድነት ውጭ የምናገኘው ጥቅም ስለነበረ አይደለም። ወደ አማራ ሃገር ከሌላው አካባቢ የሚጫንልንን ነገር ካስተዋልነው እዚህ ግባ የሚባል ነገር የለም።ለመኖር የሚያስፈልጉን መሰረታዊ ነገሮች ከራሳችን ምድር በቀላሉ የምናመርታቸው ናቸው።
ከኦሮሞው ጋር የምንኖረው ኢትዬጵያዊነትን ሲጋራን ብቻ ነው። አሁን ባለው ለወደፊቱም በሚኖረው ሁኔታ ኦሮሞ ውስጥ አማራ ፈጥሮ የጋራ እናድርጋት ያላት መተሳሰሪያችን ኢትዬጵያ የለችም አትኖርምም።እነሱ ልብ ውስጥ ያለው <<ኦሮሙማ>> ብቻ ነው። ትግራዩ ውስጥም የእኛ ኢትዮጵያ የለችም ። በአንደኛ ደረጃ ያለችው <<አደይ ትግራይ>>ስትሆን ሌላዋ ደግሞ እዬጎለበትች እንድትሄድ የምትፈለገው ፣ህወሓት እንደፈለገ የሚያሾራት ፣አማራን በየቦታው የምታፈናቅል ፣የምታርድ፣የምታንኮላሽ፣ የአማራ ልጓም የሆነችው አዲሲቷ ፀረ አማራይቱ "ኢትዬጵያ" ናት።
እናስ? እኛ እና እነሱን የምታገናኘን ኢትዬጵያ የት አለች? የለችም። ያለችው እኛ አማሮች ልብ ውስጥ ናት። ከአማራም ጋራ ነው የምትቀረው። አረንጓዴ ቢጫ ቀይዋ ሰንደቃችን (የኦሮሞ ልጆች በየቦታው የሚያቅጥሏት፣ትግራዬች ከላያቸው ገፈው ጥለው በሌላ የተኳት ) አማሮች ጋር ነው ያለችው። ያቺ አባቶቻችን ለእኩልነት ፣ ለታላቅነት ፣ለአንድነት የሰሯት በታሪክ ገናናዋ ኢትዬጵያ አሁን የለችም። የአማራ ልጅ ቁርጥህን እወቅ። ያለችው አንተ ልብ ውስጥ ብቻ ነው። አማራን መገንጠል ከሰፊዋ ግን ከልፍስፈሷ፣ ከሃይማኖት ባህል ወግ የለሿ፣ ኢትዬጵያ ወደ ጠባብዋ ግን ጠንካራዋ ፣ባለ ባህል በለ ወጓ፣ ባለ ሃይማኖተኛዋ ‪#‎ጊዬናዊት‬ኢትዬጵያ መቀየር ማለት ነው። ጠንካራ አማራን መፍጠር ። አለቀ!!
ድል ለአማራ ህዝብ!
መሳፍንት ዘ አማራ
ከ ‪#‎ቤተ‬ ‪#‎አማራ‬