Bete Amhara

Bete Amhara

Monday, June 15, 2015

ውድ ቤተ አምሐሮች
============
አንድ አጭር መልእክት ማስተላለፍ እንወዳለን፡፡ የአማራ ራሰን ችሎ መንግስት የመሆን ሀሳብና የታየው እንቅስቃሴ በተለይም መላ አጥቶ ከነበረው የአማራ ወገን የታየው በጎ ምላሽ ወያኔዎችን በእጅጉ እንዳስደነገጠ ይታወቃል፡፡ ከዚህም የተነሳ ወያኔዎች ይህንን ሃሳብ ለመምታትና ለማዳፈን መላ ሲዘይዱ እንደሰነበቱ እናውቃለን፡፡ ከዘዴዎቻቸውም አንዱ የዚህን እንቅስቃሴ ምንጭ ወያኔ እንደሆነ ማስመሰል ነው፡፡ ለዚህም ዛሬ የመጀመሪያውን ሙከራቸውን አድርገዋል፡፡ እርሱም የወንድማችንን የመሳፍንትን የእናቱን ፎቶ አግኝተናል፤ ፎቶውም የትግሬ የፀጉር ስሬት ነው፤ ስለዚህ መሳፍንት ወያኔ ነው የሚል ነው፡፡ የፀጉር ስሬትም ለካ ወያኔ ያደርጋል፡፡ ተልካሻው የወያኔ ድንቁርናዊ እርምጃ ለራሱ ትዝብት ከማትረፍ የማይዘል መሆኑን እናውቃለን፡፡ ለዚህ የደነዙ የወያኔ ዘፈን የእኛ መልስ አጭርና ግልፅ ነው፡፡ ወይ ጎንደርን አለማወቅ የሚል፡፡ የመሳፍንት እናት እንዲህ የሚያምሩ ወይዘሮ መሆናቸውን አላውቅም ነበር፡፡ እውነትም የአበቄለሽ ጎንደር ዘር፡፡ ወይ ውበት፡፡ የጓደኛየ ሸበላነት ከየትም አልመጣም ለካ፡፡ መሴው ይመችህ የልኡላን ዘር ነህ፡፡
በአግራሞት የተዋጠው መለክ ሐራ ከቤተ አምሐራ
Messafint Ze Gojjam