Bete Amhara

Bete Amhara

Wednesday, June 17, 2015

አማራን ባህሉንም ራሱንም የማጥፋት ዘመቻ
አማራን ማጥፋት የወያኔ መርህ ነው---ተደጋግሞ እንደተባለውና በሰፊው እንደሚታወቀው፡፡ አማራ ላይ የሚደረገው ጥፋት ጀርመን በናሚቢያ ላያ ያደረገችውን ይመስላል፡፡ በቅኝ ግዛት ዘመን ጀርመን የናሚቢያን የተወሰነ ጎሳ ክፍል አንድ ላይ ሰብስቦ ጨፈጨፈ፡፡ እስከዛሬ አጽማቸው ይጎበኛል፡፡ ይህም ወያኔ አማራና ኦሮሞን ለማጋጨት በሚል ሰይጣናዊ ተልእኮ ከአንዳንድ ኦነጎች ጋር በማበር በተለያዩ ቦታዎች የጨረሳቸውን አማሮች ሁኔታ ያስታውሰናል፡፡ እንግሊዞች ቀድሞ በአውስትራሊያ ይኖሩ የነበሩ ነባር ህዝቦችን በተለያየ መንገድ አጥፍተው የራሳቸው አገር አደረጓት፡፡ በተመሳሳይ አሜሪካኖች ነባር ህዝቦችን ጨፍጭፈው አጠፉ፡፡ ስፔኖችና ፖርቱጋሎችም በደቡብ አሜሪካ ይኖሩ የነበሩ ብዙ ጎሳዎችን አጠፉ፡፡ ከትግራይ የበቀለውና ገና ከጅምሩ አማራን ካላጠፋሁ ሞቸ እገኛለሁ ያለው ወያኔ በተመሳሳይ መንገድ አማራን ማጥፋቱን ሆነ ብሎ ተያይዞታል፡፡ አማራ ካልነቃና አሁን በያዘው የማያዋጣ ኢትዮጵያዊነት ስሜት የሚቀጥል ከሆነ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ከላይ እንደተገለጹት ህዝቦች ይጠፋል፡፡ ፈጽሞ ባይጠፋ እንኳ አናሳ እዚህ ግባ የማይባል ተጽእኖ አልባ ጎሳ ይሆናል፡፡ አንድን ህዝብ ማጥፋት ከባድ አይደለም፡፡ በጣም ቀላል ነው፡፡ ወያኔ አማራን በሚቀጥሉት 30 አመታት ውስጥ አጥፍቶ ይጨርሳል ስንል ከመሬት ተነስተን ሳይሆን በተመሳሳይ ሁኔታ የውሀ ሽታ ሆነው የቀሩ ህዝቦችን ዋቢ በማድረግ ነው፡፡ ማንም እንደጠፋው አማራም ይጠፋል፡፡ እና አሁን የገጠመን የማንነተችን የመጥፋት አደጋ ብቻ ሳይሆን ራሳችንም የመጥፋት ችግር ነው፡፡
ወያኔ ሲነሳ አንደኛ እቅዱ አማራን ማጥፋት ሲሆን ሁለተኛ እቅዱ ትግራይን ማልማት ወይም ነጻ አገር ማድረግ ነበር፡፡ ልብ በሉ፡- ትግራይ የምትመሰረተው በአማራ መቃብር እንጅ አማራ ሳይቀበር ትግራይን ማሳደግ ይቻላል አላሉም፡፡ ስለዚህ እቅዳቸው ሲጨመቅ መጀመሪያ አማራን ማጥፋት፤ ቀጥሎ ትግራይን መገንባት ነው፡፡ አማራው ያልገባው ነገር ወያኔዎች ለአማራ ያላቸው ስር የሰደደ ጥላቻ ነው፡፡ አሁንም የጥላቻቸውን መጠን ካላወቅን ቀስ በቀስ ወደተረትነት ማምራታችን እርግጥ ነው የሚሆነው፡፡
በስነልቡና ረገድ አማራ ላለፉት አርባ አመታት ከፍተኛ ዘመቻ ሲካሄድበት ነው የቆየው፡፡ የአማራን ስነልቡናዊ ዋጋ ለማጥፋት ያልተደረገ ሙከራ የለም፡፡ የበታችነት እንዲሰማው፤ በታሪክ በተደረጉ ነገሮች ጥፋተኝነት እንዲሰማው፤ አማራ ነኝ ብሎ መናገርን አሳፋሪ ነገር አድርጎ እንዲያይ ማድረግ፤ በአማራነቱ የሚደርስበትን ግፍ እነዳያይና እንዲደነዝዝ ማድረግ፤ እና የመሳሰሉት ሲፈጸሙበት ቆይተዋል፤ አሁንም ተባብሶ ቀጥሏል፡፡ ይህም ሁሉ የሚደረገው በአማራ የስነልቡና መቃብር ላይ የትግሬን የስነልቡና የበላይነት ለመገንባት ታልሞ ነው፡፡
አማራ ባለታሪክ ህዝብ እንደሆነ አለም ራስዋ ምስክር ናት፡፡ አማራ በግንባር ቀደምትነት የጥቁርን ህዝብ ታሪክ የቀየረ ነው፡፡ ጥቁር ሰው መሆኑን በጊዜው የበላይ ነን ለሚሉ ነጮች በተረገጥ ያሳየ ብቸኛው የአለማችን ጥቁር ህዝብ ነው፡፡ አማራ ታሪክ ለመስራት የተፈጠረ ህዝብ ነው፡፡ ራሱን ለማስከበር ባደረገው ተጋድሎ የአለምን ድንቅ ታሪክ በጉልህ ቀለም የጻፈ ነው፡፡ ከሞላ ጎደል የግድፈት ታሪክ የሌለው ታማኝ ህዝብ ነው፡፡ ይህ ግን አማራን ከደሙ ለሚጠላው ወያኔ የሚዋጥ አልሆነም፡፡ የአማራ የሆነን ታሪክ ሁሉ በአደባባይ ለስኳር መጠቅለያ ከማደል እስከ ቅርስ መዝረፍና ማቃጠል የዘለቀ ዘመቻ ከፍቶ ቆይቷል፡፡ የአማራን ታሪክ ማጥላላት፤ የአማራን ታሪክ ሰሪ ሰዎች ማጥላላትና መስደብ እንዲሁም ሰድቦ ለሰዳቢ መስጠት እና የተለያየ ጥላሸት መቀባት የመሳሰሉት ዋና የወያኔ ስራዎች ናቸው፡፡ ታሪኩን ምታ ጥንካሬው ይሟሽሻል የሚል ብሂል በመከተል ይህ ነው የማይባል ጉዳት አደረሱበት፡፡ የሚጨበጡና የማይጨበጡ የአማራ ታሪክ ፈርጦችን ሆነ ብለው በማጥፋት ስራ ተጠምደው መቆየታቸው የሚታወቅ ነው፡፡
አማራ የሀይማኖት ህዝብ መሆኑ በራሱ ጠላትነትን ነው ያተረፈለት፡፡ በሀይማኖት ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ቅዱስ ቦታዎችን ከማራከስ ጀመሮ በአደባባይ በእምነት ቦታዎች ላይ መረሸን በአገራችን በጣልያን ጊዜ ብቻ የታየ ክስተት ነው፡፡ ከአረመኔም የአረመኔ ስራ ተሰራበት በአማራው ላይ፡፡ ደጀ ሰላም ላይ በጥይት ብዙ ጊዜ ተረፈረፈ፡፡ የጎንደርን እና የቅርቡን የባህርዳርን ጭፍጨፋ ዋቢ ማድረግ ይቻላል፡፡
በአጠቃላይ አማራ ላለፉት አርባ አመታት ከፍተኛ የጥፋት ዘመቻ ታውጆበት ይገኛል፡፡ ጥፋቱም እንደ ህዝብ እና እንደ ባህል ነው፡፡ አማራን ራሱን ማጥፋት እና የአማራን ባህል እንዲሁም ታሪክና ስነልቡና ማጥፋት ዋነኛ አጀንዳወች ናቸው፡፡
ወገን ንቃ ራስክን ከትፋ ታደግ---አንተ ተኝተህ ስትጠፋ ማም አይደርስልህም!
Mesafint Ze Amhara