የቤተ አምሓራ እንቅስቃሴ ለአማራ ሕዝብ የሚኖረው ጠቀሜታ
• ሁለት ጉድጓድ ያላት አይጥ አትሞትም
• እቅድ ‘ለ’ የሌለው ሰው/ሕዝብ እቅድ ‘ሀ’ ካልተሳካ መጨረሻው ውድቀት ነው።
አንድነት ሰባኪዎች ሊያውቁት የሚገባው በጣም አስፈላጊው ነጥብ ይህ ይመስላኛል። ባሁኒትዋ ኢትዮጵያ ማንም ሰው ስለ አንድነት ካወራ ከሰበከ - አማራ - የዱሮዉን ናፋቂ - ነፍጠኛ - የሚሉ ስሞች ይለጠፉለታል። ተለጣፊ ስሞችን ታግሶ መኖርን ለምደነዋል። ከዚያም አልፎ በሄድንበት ሁሉ እንደ እባብ አናት አናታችንን እየተቀጠቀጠንም ታግሰን አንድነታችንን ጠብቀን ለመኖር ስንል ብዙ ዋጋ ከፍለናል። ለዚህ ሁሉ ዋጋ መክፈልና መጠላት የሰጠነው ትንታኔ ደግሞ - ለጊዜው ነው ነገር ይለወጣል - ነገ የተሻለች አንድ ኢትዮጵያ ትመጣለች የሚል ነው። ይህ አነጋገር በብዙ ምኞቶች እና በጥቂት እውነታዎች ተንጠልጥሎ ያለና መሬት ያልረገጠ ተስፋ ነው።
ግን እስኪ ለአንድ አፍታ - እንዳሰብነው የአንድነቱ ጉዳይ ባይሳካስ መጨረሻችን ምን ይሆናል ብሎ ማሰብ ምንድን ነው ክፋቱ?
እኛ አንድነትን ስናቀነቅን የተፈጠሩ ክፍተቶች አሉ። ጥቂቶቹን ብናነሳ
• ለ24 ዓመታት እኛን በማይወዱና የሕዋሓት አሽከር በሆኑ እድገታችንም ውድቀታችንም ትርጉም በማይሰጣቸው ሰዎች ስንተዳደር ኖረናል።
• ተፈጥሮ ሳይጎዳንና የተማረ ሰው ሳናጣ ደሃ ህብረተሰብ ፈጥረናል።
• ከ 80% በላይ የሚሆነውን የአማራ ሕዝብ በ21 ኛው ክፍለ ዘመን 15ኛው ክፈለ ዘመን ይመስል የገጠር ህይወት እንዲመራ አድርገናል።
• ይህ ያነሰ ይመስል ደርጊታችንን ሳንቀይር የተለዬ ውጤት እየጠበቅን እንገኛለን። ይህ ደግሞ ጅልነት ይባላል። Doing the same things and expecting different result is the definition of insanity.
የቤተ አምሓራ ጠቀሜታ እዚህ ላይ ያለ ይመስለኛል። ኢትዮጵያዊነትን እያቀነቀንን ሕዝባችንን ከዚህ በሁዋላ እየጎዳን መቀጠል እንፈልግም የሚል ቁርጠኝነት ይዘን ተነስተናል። ኢትዮጵያን አንጠላትም፡፡ ነገር ግን የምንፈልጋት ስትፈልገን ብቻ ነው። አማራን እንደዜጎችዋ ተቀብላ እኩል እድል የምትሰጠን ከሆነ ብቻ ነው እኛም የምንቀበላት። የምንፈልገውም የማንፈልገውም ነገር ኢትዮጵያ ላይ ሊፈጠር ይችላል ብሎ እያንዳንድዋን ሁኔታ አስተውሎ ላየው ሰው የሚከተሉት ነገሮች ሊከሰቱ ይችላሉ።
• እንዳሁኑ ተከፋፍላ አማራ እንደጠላት እየተቆጠረ ልትቀጥል ትችላለች።
• ልትገነጣጠል ትችላለች። አንድነትን እየዘመርን ክልሉን ምንም ሳንሰራበት መገነጣጠል ከመጣ ድህነትን በር ከፍቶ ማስገባት ነው።
• ምናልባት በጣም ምናልባት አንድ ሆነን ልንቀጥል እንችላለን።
ማንኛውም ሁኔታ ቢከሰት ግን ቤተ አምሓራ ዝግጁነት ነው። ጠንካራ የአማራ መንግስት በመመስረት የአማራን ሕዝብ ተጠቃሚ በማድረግ ለሚመጣው ሁሉ እራሳችንን ማዘጋጀት ነው። እኛን የምትቀበለን ኢትዮጵያ ብትፈጠርም - ብትገነጣጠልም - ያሁኑ ፌድራሊዝም ቢቀጥልም - ቤተ አምሓራ ጠንካራና የበለጸገ አማራን በመፍጠር የሚመጣውን ለመቀበል መዘጋጀት ነው። ቤተ አምሓራ እቅድ ‘ለ’ ነው። ቤተ አምሓራ ሊመጣ ካለው የባሰ ጥፋት ማምለጫ ነው። አባቶቻንንስ “ሁለት ጉድጓድ ያላት አይጥ አትሞትም”አይደለም እንዴ ብለው ያስተማሩን።

ራስ የማነ ነኝ ከቤተ አምሓራ