በአማራው ላይ የሚደርሰው የዘር ማጥፋት፣ የዘር ማጽዳት ይቁም። አማራዉን ከዚህ ጥቃት ለማዳን ሶስት የተለያየ ጥረቶች የተሞከሩ እና በሙከራ ላይ ያሉ ብሎ መክፈል ይቻላል።
በዘመነ ወያኔ ብዙ የአማራ ልጆች ተገለዋል፣ አካል ጉዳተኛ ሆነዋል፣ ተወልደው ካደጉበት፣ ሀብት ንብረት ካፈሩበት ቀየ እና መንደር አገራችሑ አይደለም ውጡ ተብለው ተባረዋል። ብዙ እጅግ ብዙ አማሮች የሚዘገንን ግፍ ተፈጽሞባቸዋል። በእስር ቤት ውስጥ ወንዶች የዘር ፍሬአቸውን አማራ ብቻ ስለሆኑ ይቀጠቀጣሉ፣ በግልጽ እየተነገራቸው። ትናንት በካንጋሮው የወያኔ ፍርድ ቤት አንድ ወንድማችን ሀፍረተ ስጋውን አውልቆ እያሳየ አንተ አማራ እያሉ እንደቀጠቀጡት አሳይቷል። ከዚህ በፊትም ብዙ እነዚህን የመሰሉ ነገሮችን አይተናል። ግን ሰሚ የለም፣ መስሚያቸው ተደፍኗል። አውቆ የተኛ ቢጠሩት አይሰማም። የአማራው ለቅሶ የአዞ እንባ እየሆነ ነው በወያኔ ቤት። እነ ፕሮፌሰር አስራት እንዴት በግፍ እንደተገደሉ ማስታወስ በቂ ነው። በ 2007 በተደረገው ህዝብና ቤት ቆጠራ እራሳቸው ያመኑት ነገር ነው፣ ከሁለት ሚሊዮን አማራ ጉድለት አሳይቷል። ሴቶች እንዳይወልዱ ሆን ተብሎ አማራ ክልል ብቻ የሚያመክን ክትባት ይወጋሉ። የማጅራት ገትር በሚል ክትባት ሰበብ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህጻናት ይገለላሉ።
አማራዉን ከዚህ ጥቃት ለማዳን ሶስት የተለያየ ጥረቶች የተሞከሩ እና በሙከራ ላይ ያሉ ብሎ መክፈል ይቻላል። እነዚህም ባጭሩ በእኔ አረዳድ እንደሚከተለው ይቀርባሉ።
1. የመጀመሪያው ለብዙ ዘመናት አማራው እየሞተም የኢትዮጵያዊነትን ስሜት ሲያቀነቅን ነበር። በዚህ በኢትዮጵያዊነት ስሜቱ ብዙ ተሰድቧል፣ ተገሏል፣ ተፈናቅሏል፣ ብዙ መከራዎችን ተቀብሏል። ይሄንን የኢትዮጵያዊነትን እምነቱን ትምክተኛ በሚል እምነት ለማጣጣል ብዙ ጥረት ተደርጓል።
2. ሁለተኛው ደግሞ፣ ወያኔ ባወጣው የመደራጀት መስፈርት፣ በአማራ ስም ሲደራጁ ወዲያውኑ ድርጅቶች እንዲፈርሱ ይደረጋል። ለማሳሌ መኢአድን ሌሎችም በአማራ ስም የተነሱ ብዙ ድርጅቶች ስም አጠራራቸው እንዲጠፋ ተደርጓል። እነ ሞረሽ ወገኔም መቀመጫቸውን በአብዛናው ውጭ ስላደረጉ እስካሁን አሉ።
3. ሶስተኛው በቅርቡ የአማራ ወጣቶች ቤተ አምሀራን እንመስርት የሚል አዲስ እሳቤ ይዘው ብቅ ብለዋል። በስፋትም ቤተ አምሀራ አገራቸውን ባህላቸውን እና ማንነታቸውን ለማስተዋወቅ ጥረት እያደረጉ ነው። እነዚህም ከትችት እና ከዘለፋ አላመለጡም። ብዙዎቹ በስመ አምሀራ የሚመጡ ሰዎች አብዝተው ይኮንኗቸዋል።
አምሀራ እንደ ኢትዮጵያዊ ሲቆም ትምክተኛ እና የድርውን ስርአት ናፋቂ፤ በብሔር ልደራጅ ሲል፣ አይ አይ አማራ ብሔር ተኮር አስተሳሰብ አይገባውም እና በአንዳንዶች ዘንድ እነዚህ ስብስቦች የወያኔን አላማ ደጋፊ ይባላሉ። ሶስተኛው ተገንጥለን በተ አምሀራን የራሳችንን ማረፊያ ጎጆ እንቀልስ ሲባል፣ የማንም ለሀጫም እየተነሳ ዘረኛ፣ ጠባብ ወዘተ የሚል ስያሜ ተሰጣቸው።
ስለዚህ አማራ ምን ይሁን? ምንስ ያድርግ?? እስኪ እናንተ ሀሳባችሑን ስጡን።